3 Aug 2026, 11:44 UTC619 views9 reactionsread 8 August 2026 በዜሮ የተባዛው አገልግሎት!
አንድ ንጉስ አስር አመት ሙሉ በታማኝነት ያገለገለው አገልጋዩ እንዲት ስህተት ስለሰራ ብቻ ቅጣትን አስተላለፈበት፡፡
በንጉሱ ሕግ መሰረት ማንኛውም ስህተት የሰራ አገልጋይ በኃይለኛነታቸውና በተናካሽነታቸው የታወቁት የንጉሱ ውሾች ወደሚኖሩበት ግቢ ለቅጣት ታልፎ ይሰጣል፡፡
ይህንን የንጉሱን ውሳኔ የሰማው ታማኝ አገልጋይ በሁኔታው በጣም አዘነ፡፡ እሱን ያሳዘነው የተላለፈው ቅጣት ሳይሆን፣ ለአስር አመታት ካለምንም ስህተት አገልግሎ፣ አንዲት ስህተት ብቻ ስለተገኘችበት የንጉሱ መጨከን ነው፡፡
ይህ አገልጋይ ቁጭ ብሎ፣ “ይህንን ቅጣት አስቀረሁትም፣ አላስቀረሁት ንጉሱ ግን ይህንን ጥሩ ያልሆነ ልምምድ የሚያቆምበትን አንዲት ትምህርት ባስ…
❤7👍1🔥1
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
29 Jul 2026, 11:44 UTC926 views5 reactionsread 8 August 2026 #ፍቅር_ተስፋ_አይቆርጥም
"በዓለም ውስጥ ከእውነተኛ የፍቅር ኃይል የበለጠ ኃያል የለም።
ፍቅር በስርቅርቅ ዜማ ብዙ ተዚሞለታል። በሚያማልል ድርሰት ብዙ ተፅፎለታል። ጨካኞችን ሳይቀር በኃይሉ አንበርክኳል።
ይህ እውነተኛው የፍቅር ኃይል የሚገኘው ደግሞ ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ አስተሳሰብ ተግባር ውስጥ ነው። ፍቅር የተፈጥሮ ጉዳይ ብቻ አይደለም።
ይልቁንም ከፍተኛ ትዕግስትን፣ ትህትናን፣ ትኩረትን፣ እምነትንና እንክብካቤን ይጠይቃል።
ፍቅር ስሜት ሳይሆን ተግባር ነው።
በሕይወታችን ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር ፍቅርን በተግባር እንዴት መስጠት እንደሚቻል መማር እና ወደ ውስጣችን እንዲገባ መፍቀድ ነው።
ፍቅር ምንም አይነት እንቅፋት ቢፈጠር መሰናክሎችን…
❤4👍1
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
26 Jul 2026, 05:33 UTC991 views7 reactionsread 8 August 2026 #ድረሱልኝ!
📗 አንድ አባት ልጁን እንዲህ ሲል አዘዛት ''ልጄ ዛሬ ደስ ስላለኝ ድግስ አዘጋጂ፤ ወዳጅ ጎረቤቶቻችን ዘመዶቻችንን ሁሉ ጥሪያቸው፤ እኔ ከስራ ስመለስ አብረን እንሆናለን እስከዛ ከእነሱ ጋር ተደሰቺ '' በማለት ወደ ስራው ሄደ። ብልሁዋ ልጅም ከቤት ወጣችና እንዲህ ስትል ጩኸት አሰማች፡፡
''እባካችሁ እርዱን ቤታችን ውስጥ እሳት ነዷል አባቴን ከእሳቱ አውጡት እባካችሁ።''
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ዘመድ እና ጎረቤት የሆኑ ሰዎች መጡ። ነገር ግን የድረሱልን ጥሪዋን እንዳልሰሙ ሆነው አለፉ።
ነገር ግን የማታውቃቸው አንዳንድ ሰዎች የድረሱልኝ ጥሪዋን ሰምተው አባቷን ለማዳን ወደ ቤቱ ዘለው ገቡ። ያጋጠማቸው ግን ባማረ ሁኔታ የተዘጋጀ መብል እና መ…
👍4❤3
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
17 Jul 2026, 07:10 UTC≈1,320 views16 reactionsread 8 August 2026 ጽንአት!!!
“አንድ ሰው የሚያልቅለት ሲሸነፍ አይደለም፤ የሚያልቅለት በበቃኝ ሲያቆም ነው” - Richard M. Nixon
በሕወትህ በአንድ ባመንክበትና ትክክል በሆነ ዓላማ እስከመጨረሻው ከመጽናት ውጪ ምንም ቁም ነገር ልታከናውን አትችልም፡፡ ዛሬ ይህንና ያንን እየጀመርክ እስከጥጉ ሳታደርሳቸው ነገ ደግሞ ወደሌላ ነገር ዘወር የማለት ለማድ ካለህ በተቻለህ ፍጥነት ይህንን ዘይቤ መቀየር እንዳለብህ ትመከራለህ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድን የጀመርነውን ነገር እስከጥጉ የማንወስድበት ዋነኛ ምክንያት ስንወድቅ ወይም ያልተሳካልን ሲመስለን ነው፡፡ ሆኖም፣ ውድቀት፣ አለመሳካት፣ እንቅፋትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች በማንኛውም አንድን መልካም አላማ ይዞ በሚራመድ ሰው ሕይወት …
❤9👍7
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
10 Jul 2026, 04:38 UTC≈1,310 views4 reactionsread 8 August 2026 #ደስታ_የሚመጣው_ችግሮችን_በመፍታት_ነው
በሕይወት ውስጥ ሁልጊዜም ችግሮች አሉ፡፡
አንድ ነገር ለማድረግ ስትሞክር ሌሎች ችግሮች መፈጠራቸው አይቀርም። ለምሳሌ፣ የጤና ችግርህን ስፖርት በመስራት ልትፈታው ስትወስን ጂም በጊዜ ለመድረስ በጊዜ መነሳት፣ በጣም እንዲያልብህ በርትተህ መስራትና ወደ ስራ ስትገባ በመጥፎ ጠረን ቢሮውን እንዳትበክል የግድ መታጠብ ስለሚያስፈልግህ ሌላ አዳዲስ ችግሮች ትፈጥራለህ፡፡
ከሴት ጓደኛህ ጋር በቂ ጊዜ ያለማሳለፍ ችግርህን ለመቅረፍ ማክሰኞ ምሽትን ሁልጊዜ የምትገናኙበት ጊዜ አድርገህ ስትመርጥ ሁለታችሁም እንዳይሰለቻችሁ ለማድረግና አሪፍ ራት መብላት ስላለባችሁ በዚያ ቀን የግድ በቂ ገንዘብ የመፈለግ ችግር ትፈጥራለህ፡፡
ችግሮች…
❤4
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
3 Jul 2026, 07:39 UTC≈1,500 views11 reactionsread 8 August 2026 የዓላማና የተስፋ ግንኙነት
በአንድ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ታራሚዎች በቂ የሆነና የተሟላ የምግብ አቅርቦት ነበራቸው፡፡ ከተወሰነ የማረሚያ ቤት ቆይታቸው በኋላ እርስ በርሳቸው ስለተላመዱ በተለያዩ ጨዋታዎች እየተደሰቱና አንዳንድ ሞያ ነክ ነገሮችንም እየሰሩ መረጋጋት ጀምረዋል፡፡
ብዙም ሳይቆዩ ግን ሁሉንም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተጫጫናቸው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ተስፈኛ ሆነው የመቆየት አቅማቸውንም አጡ፡፡
የሆነው ነገር ይህ ነው፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ሲነሱ በማረሚያ ቤቱ ግቢ አንድ ጥግ ላይ የተከመሩ አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ነበሩና እነዚህን ጆንያዎች ካሉበት በማንሳት ወደሌላው የማረሚያ ቤቱ ግቢ ጥግ እንዲወ…
❤11
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
30 Jun 2026, 07:59 UTC≈1,510 views7 reactionsread 8 August 2026 #ውድቀትን_አትፍሩ
"በፕላኔታችን ውስጥ ሁለቱንም እጆቹን በኪሱ ውስጥ ከትቶ የስኬት መሰላልን የወጣ አንዳች ሰው የለም። ስኬት በአብዛኛው ጊዜ የምትመጣው በሥራ ተወጥረው ትዝ እንኳን ወደማትላቸው ሰዎች ነው።
ፈጣሪ ሕይወትን በስጦታ መልክ ሰጥቶናል፤ የተመቻቸና በስኬት የታጀበ ሕይወት መኖርን ግን እኛ ለራሳችን የምንሰጠው ልዩ ስጦታ ነው። ምንጊዜም አንድ እርምጃ ወደፊት ለመራመድ ጉዞ ስንጀምር ጉዟችን የሚፈታተን አንድ እንቅፋት ይኖራል። እንቅፋቱን ፈርተን ጉዟችን ከገታን የተለየ ነገር ለማየት ምንም አይነት ዕድል አይኖረንም። ህልማችን እውን ለማድረግ የሚገድበን ትልቁ መሰናክል ቢኖር ዛሬ ላይ የከበበን የስጋት ቆፈን ነው።
ውድቀትን አትፍሩ፤ ውድ…
❤7
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
26 Jun 2026, 05:05 UTC≈1,610 views12 reactionsread 8 August 2026 እረፍት ከሚያሳጡን ነገሮች አንዱ!
እረፍት ከሚነሱን ነገሮች አንዱ፣ የእኛ ያልሆነውን ነገር የእኛ ለማድረግ የምናደርገው ከንቱ ትግል ነው፡፡
በአካባቢያችን ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑ ሰዎች የእነሱ ለመሆን ያልፈለጉ ሰዎችን የእነሱ ለማድረግ ሲታገሉ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ይህ ደግሞ እረፍት የሚያሳጣ ጉዳይ ነው፡፡
ሰዎች ከእኛ ጋር ሊኖራቸው የሚፈልጉትን የግንኙነት አይነት የመወሰን መብት አላቸው፡፡ ስለሆነም እነዚህ ሰዎች የግድ የእኛ ጓደኞች፣ አጋሮች፣ ፍቅረኞች . . . እንዲሆኑ ስለፈለግን ብቻ እንደዚያ የመሆን ፍላጎቱ ይኖራቸዋል ማለት አይደለም፡፡
ከማሕበራዊ ግንኙነት በተጨማሪ ለጊዜውም ሆነ እስከወዲያኛው በፍጹም የእኛ ሊሆኑ የማይችሉ ሁኔታዎችንም ሆነ ነገ…
❤10👍2
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
20 Jun 2026, 07:50 UTC≈1,620 views16 reactionsread 8 August 2026 ሁለቱ የችግር ቀን ስህተቶች!
ሁላችንም ቢሆን እንደማንኛውም ሰው በጣም አስቸጋሪ በሆነና እጅግ በሚሞግተን ሁኔታ ውስጥ እናልፋለን፡፡ ምናልባት በእድሜያችሁ ገና ወጣት ከሆናችሁና ይህች አለም ለሁላችንም ጊዜዋን እየጠበቀች የምታቀብለንን የሕይወት ውጣውረድ ብዙም ካልቀመሳችሁ፣ በሰው ጥላ ስር ከመኖር ወጣ ብላችሁ የራሳችሁን ውሳኔ እየወሰናችሁ የራሳችሁን ኑሮ መምራት ስትጀምሩ ትደርሱበታላችሁ፡፡
በአሁን ጊዜ ከባድ በሆነ ሁኔታው ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁ፣ እነዚህን ሁለት የችግር ቀን ስህተቶች ከመስራት ራሳችሁን እንድትጠብቁ ልምከራችሁ፡፡
የመጀመሪያው ስህተት አሁን ያለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ በእኛ ላይ ብቻ እንደደረሰ ወይም የእኛ ሁኔታ ከሌለው ለየት ያለና የከ…
❤8👍8
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
15 Jun 2026, 21:45 UTC≈1,620 views14 reactionsread 8 August 2026 #ህልመኛ_እና_እብድ_ሁን!
ዴል ካርኒጌ እንዳለው ''ለሰው ልጅ አስቸጋሪ ወይም መጥፎ ጊዜ የሚባለው፣ አንድ ሰው የተሻለ አቅም እንዳለው አውቆ ነገር ግን አጠቃቀሙን ሳያውቅ ሲቀር ነው። ''
ይሄን ከራስህ ህይወት ጋር አያይዘህ አስበው...
የህይወትህ የመጨረሻ ቀን ላይ እንዳለህ ሲሰማህ እና ደግሞ ማድረግ የነበረብህን አሁን ልታደርገው እንደማትችል ስታውቅ።
ያኔ ልታደርገው ያልቻልክበት ምክንያት ጓደኞችህ ሀሳብህን ሰምተው እንደ #እብድ ስለቆጠሩህ ይሆን?
ቤተሰቦችህን ህልምህን አውቀው ''እሺ ህልመኛው ' እያሉ #ስላፌዙብህ ይሆን?
የህይወትህ የመጨረሻ ቀን ላይ ይሄ ሁሉ የሰዎች ማጣጣል ምንም ሆኖ ቁጭት ከሚሆንብህ በፊት፣ አሁን #እብድ እና #ህልመኛ ተ…
❤14
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
15 Jun 2026, 21:43 UTC≈1,420 views10 reactionsread 8 August 2026 #ማር_ከፈለግክ_የንብ_ቀፎውን_አትምታ!
🏌️♂️ስኬት ማለት የምትፈልገውን ማግኘት ሲሆን ደስታ ደግሞ፣ ባለህ ነገር ላይ ፍላጎት ወይም ምስጋና ሲኖርህ የሚሰማህ ሰላም ነው።
🧗♂️ ፍርሃትህን ማሸነፍ የምትፈልግ ከሆነ፣ ቤት ተቀምጠህ አታብሰልስለው! ይልቁንም ከቤትህ ውጣና ራስህን በስራ ጥመድ!
🎭 ሊያጠቁህ የሚፈልጉ ጠላቶችህን መፍራት የለብህም። ይልቁንስ እጅግ የሚያወድሱህ፣ ያልተገባ ሙገሳ የሚቸሩህ ጓደኞች ካሉህ እነሱን ፍራ።
🚴♂️ ስኬታማ ሰው ከስህተቶቹ ትርፍ ያገኛል። ማለትም ቀድሞ የሞከረበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን በመረዳት በአዲስ መልክ ይሞክረዋል።
🎲 ማር የምትፈልግ ከሆነ የንብ ቀፎውን መምታት አይኖርብህም። እንዲሁም አንዳንድ የህይወት …
❤10
Signed ⒶⓨⒸⒽⒺ🎶🎻
15 Jun 2026, 06:07 UTC≈1,280 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
የተለያዩ
➠ አስገራሚ አስተማሪ እንዲሁም አዝናኝ ታሪኮችን
➠ የፍልስፍና ፅሁፎችን
➠ Motivation Quotes
➠ መፅሀፍትን በPDF
➠ ግጥም
የሚያገኙባቸው ቻናሎች
❤1
Signed Some body
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Ab_book. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.