23 Sept 2025, 05:07 UTC≈3,480 views22 reactionsread 3 September 2026 ቅዱስ እግዚአብሔርን እንኳን ለመታየት አይደለም በአንደበቱ ቢናገር የእውቀቱና የጥበቡን ልክ ማንም ሊደርስበትና ሊረዳው አይችልም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት ቆሞ መከራከር የሚችል አንድም ጻድቅ የለም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገር “ ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን ይችላል? ከእርሱ ጋር ይከራከር ዘንድ ቢወድድ፥ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም።” ተብሎ ተጽፏል።(ኢዮብ 9፥2) ከጌታ ፊት ቆመህ ልትከራከር አትችልም፤ ምክንያቱም እርሱ ከሁሉ በላይ የሆነ ጌታ ነው የተናገረውን የእውቀቱን እና የጥበቡን ልክ ተረድተህ ልትናገር አትችልም ሰማያትን ባጸኑ አንደበቶቹ ቢያናግርህ ችለህ እንዴት ልትመልስ ትችላለህ ወዳጄ?
ለጻድቁ ኢዮብ በዐውሎ ነፋስ እግዚአብሔር…
❤19🔥2👍1
21 Sept 2025, 04:44 UTC≈3,100 views8 reactionsread 3 September 2026 “እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ #የቁርበትን #ልብስ አደረገላቸው፥ #አለበሳቸውም።”
— ዘፍጥረት 3፥21
“እግዚአብሔርም እርሱን አለው፦ እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል። እግዚአብሔርም #ቃየንን #ያገኘው ሁሉ #እንዳይገድለው #ምልክት #አደረገለት።”
— ዘፍጥረት 4፥15
“እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ #ምድርን #ዳግመኛ ስለ ሰው #አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት #ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና #አልመታም።”
— ዘፍጥረት 8፥21
እግዚአብሔር ሁልጊዜ መልካም ነው።
ሠናይ ሰንበተ ክርስቲያን ይሁንልን🙏
❤8
19 Sept 2025, 15:32 UTC≈2,770 views13 reactionsread 3 September 2026 ጌታ ከጠላት ጋር ስንታገል እንደሚመለከተን ዘወትር ልናስታውስ ይገባል፤ ስለዚህም ከቶ ልንፈራ አይገባንም። ሲኦል ሁሉ በላያችን ቢወድቅ እንኳ ጽኑዓን ልንሆን ይገባል።"
የአቶሱ ቅዱስ ሲልዋን እንደ ተናገረው።
❤10🫡3
18 Sept 2025, 18:55 UTC≈2,400 views10 reactionsread 3 September 2026 ነገር ግን 'ቃልም ሥጋ ሆነ' [ዮሐ. 1:14] የሚለው ኃይለ ቃል፣ እርሱ እንደኛ ሥጋና ደምን ከመካፈሉ በቀር ሌላ ትርጉም ሊኖረው አይችልም፤ ሥጋችንን ገንዘቡ አደረገ፤ ከሴትም ሰው ሆኖ ተወለደ። ይህን ሲያደርግ አምላክ ሆኖ መኖሩን ወይም ከአብ መወለዱን አልተወም፤ ነገር ግን ሥጋን ለራሱ በወሰደ ጊዜ እንኳ የነበረውን ሳይለቅ እንደሆነ ጸንቷል። ይህንን በየትኛውም ስፍራ የቀናች ሃይማኖት አዋጅ ያስተምራል። ይህ የቅዱሳን አባቶች እምነት ነበር፤ በዚህም ምክንያት ቅድስት ድንግልን 'ወላዲተ አምላክ' ብለው ለመጥራት ደፍረዋል። ይህን ያሉት የቃል ባሕርይው ወይም መለኮቱ ከቅድስት ድንግል ተጀመረ ለማለት ያህል አይደለም፤ ነገር ግን ከእርሷ ያ ቅዱስ ሥጋ ከለባዊት ነ…
❤8🥰2
14 Sept 2025, 09:32 UTC≈2,200 views13 reactionsread 3 September 2026 ነፍስ በዓመፅ ስትኖር፣ ያ ሞቷ ነው፤ እንደገናም ጻድቅ ስትሆን፣ ራሷ ካልሆነው የሌላ ሕይወት ተካፋይ ትሆናለች፤ ይህም ወደ እግዚአብሔር በመቅረብና ከእርሱ ጋር በመጣበቅ ከእርሱ ዘንድ ትጸድቃለች። እንዲህ ተብሏልና፦ “ለዚያም ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።” (ሮሜ 4:5)። እግዚአብሔርን በመተው ዓመጸኛ ትሆናለች፤ ወደ እርሱ በመምጣት ጻድቅ ትሆናለች። ይህ ነገር፣ ወደ እሳት ሲቀርብ የሚሞቅ፣ ከእሳት ሲርቅ ደግሞ የሚቀዘቅዝ የቀዘቀዘ ነገር አይመስላችሁምን? ወደ ብርሃን ሲቀርብ የሚበራ፣ ከብርሃን ሲርቅ ደግሞ የሚጨልም ጨለማ ነገር? ነፍስ እንዲህ ያለች ነገር ናት፤ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም።
ቅዱስ አውግስጢኖስ- "…
❤10❤🔥2👍1
11 Sept 2025, 05:43 UTC≈2,720 views17 reactionsread 3 September 2026 “አንተሰ አንተ ክመ ወዓመቲከኒ ዘኢየኀልቅ" «አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።»
— መዝሙር 102፥27
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
ቸርነቱን ለሚታመኑበት እንደ ሰማይ ጠል ያዘንብላቸዋል ምህረቱ ለዘለዓለም ናት በእርሱ ባይሆን ኖሮ አንዷም ምሽት አታልፍም ነበር ይህች ቀን የቀናት መለዋወጥ ሳትሆን የምሕረቱ ባለጠግነት ውጤት ብቻ ናት ዛሬን በምህረቱ ያሳየን አምላክ በማይመጥኑት ቃላት እናመሰግነዋለን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገንልን።
እንኳን ለ2018 ዐዲስ ዐመት በሰላም አደረሰን 🙏
❤14👏2🔥1
7 Sept 2025, 07:06 UTC≈1,900 views11 reactionsread 3 September 2026 “ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።”
— ራእይ 1፥8
❤11
22 Aug 2025, 14:11 UTC≈2,320 views16 reactionsread 3 September 2026 Photo
እኛስ ኃጢአታችንን ለማስተስረይ በሥጋ እንደ ታመመ እንደ ሞተ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ሥጋውን እንደ ገነዙ ከሙታንም ተለይቶ በእውነት እንደ ተነሣ ከተነሣም በኋላ በእውነት እንደ በላ ወደ ሰማይም እንደ ዐረገ እናምናለን።
ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም-ሃይ አበው 52:11
@Apostolic_Council
❤16
12 Aug 2025, 05:11 UTC≈2,090 views7 reactionsread 3 September 2026 ክርስትና በሰብእ (በሰው) ቢመሰል ልቡ እና እስትንፋሱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ነው በህልውና የመኖሩ ልኬት ትንፋሹ ነውና የክርስትናም ሕልውና ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! ውድቀተ ዓለምን ለመሻርና ለመደምሰስ በአካላዊ ልብ ኄር (ቸር) በሚሆን አብ የተወጠነው የድኅነተ ዓለም ውጥን በአካላዊ ቃል ወልደ አብ ተፈጸመ ይኸውም የዕብራውያን ጸሐፊ ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን ያለው ነው ይህም መልእክት ማሕየዊ [3] (ሕይወት ሰጪ) የሚሆን መንፈስ ቅዱስ ለዓለሙ ሁሉ ሲገልጠው ይኖራል የእግዚአብሔር ጥበብ ክርስቶስ የሚብራራው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና።[4] የእግዚአብሔር የመጨረሻው መልእክቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለዚህም ነው ታላቅ መደ…
❤7
10 Aug 2025, 05:50 UTC≈1,930 views11 reactionsread 3 September 2026 ከኪሩቤል ወይም ከሱራፌል አንዳች ነገር ለመማር ብትፈልግ፥ የቅድስናውን ምሥጢራዊ ዝማሬ ትሰማለህ፤ እንዲሁም ሰማይና ምድር በክብሩ መሞላታቸውን [ትሰማለህ]። ከፍ ያሉትን ኃይላት ብትመረምርም፥ ብቸኛ ተግባራቸው እግዚአብሔርን ማመስገን መሆኑን ብቻ ታገኛለህ።
─────────────────
𝐉𝐨𝐡𝐧 𝐂𝐡𝐫𝐲𝐬𝐨𝐬𝐭𝐨𝐦, 𝐇𝐨𝐦𝐢𝐥𝐢𝐞𝐬
𝐨𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐆𝐨𝐬𝐩𝐞𝐥 𝐨𝐟 𝐉𝐨𝐡𝐧 15.1 (𝐍𝐏𝐍𝐅1, 14)
መልካም ሰንበተ ክርስቲያን ይሁንልን 🙏
❤11
6 Aug 2025, 05:20 UTC≈2,030 views15 reactionsread 3 September 2026 « ዳርቻ የለህም፣ ፍጻሜም ይለህም፣ ያገኘህ የለም፣ የሚያገኝህም የለም።የሚያውቅህ የለም አንተን ማየት የሚችል የለም ራስህን አንተ ታውቃለህ። መንግሥትህ አያልቅም ኃይልህም አይሻርም ገናንነትህም አይጨረስም ጌትነትህ አይሠወርም፤ አንተ ከሁሉ የተሠወርህ ነህ፣ ላንተ ግን ሁሉ የተገለጠ ነው፤ጥንት የለህም አንተ ግን ለሁሉ ፍጻሜን ትሰጣለህ።
ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቍ 4-6
መልካም ቀን🙏
❤14👏1
4 Aug 2025, 15:32 UTC≈2,360 views2 reactionsread 3 September 2026 “እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።”
— ዕብራውያን 4፥13
አንድ ጊዜ ላይ፣ ሶርያዊው ኤፍሬም መንገድ ላይ ሳለ አንዲት ዝሙት አዳሪ ሴት፣ ወደ አሳፋሪ ግብር ባትመራው እንኳ፣ ቢያንስ ለማስቆጣት በማባበያ ቃላቶቿ ሞከረች። ምክንያቱም ማንም ሰው ተቆጥቶ አይቶት አያውቅም ነበርና። እርሱም «ተከተይኝ» አላት።
እጅግ በሕዝብ የተጨናነቀ ቦታ ሲደርሱ፣ «በዚህ ቦታ፣ ነይ፣ የምትፈልጊውን አድርጊ» አላት። እርሷ ግን ሕዝቡን አይታ፣ «ሳናፍር፣ እንዲህ ባለ ብዙ ሕዝብ ፊት የምንፈልገውን እንዴት ማድረግ እንችላለን?» አለችው።
እርሱም መለሰላት፦ «አንቺ በሰው ፊት የምታፍሪ ከሆነ፣ …
❤2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Apostolic_Council. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.