7 Sept 2026, 04:28 UTC371 views4 reactionsread 7 September 2026 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ስንክሳር ዘወርኀ ጳጒሜን ፩ †
=>አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተባረከ የጳጒሜን ወር ባተ። በዚች ቀን ጳጒሜን አንድ የወንጌላዊ ዮሐንስ ረድእ ሐዋርያና ሰማዕት የከበረ ዑቲኮስ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ወንጌላዊ ዮሐንስን ሲያገለግለውና ሲታዘዘው ኖረ። ከዚያም ከሐዋርያ ጳውሎስ ጋራ ሔደ እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰም እንዲሰብክ አዘዘው በአረማውያንና በዮናናውያንም መካከል ሰበከ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ወደማወቅ ብዙዎችን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው።
የጣዖታት ቤቶችን አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ።…
❤4
Signed Ermias Adane
6 Sept 2026, 13:30 UTC200 views1 reactionsread 7 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤1
Signed sale Desale
6 Sept 2026, 13:30 UTC211 viewsread 7 September 2026 “በታቦት የሚያድረው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል ብቻ ነው። በቅዱሳን ስም የሚሰየመው ለቅዱሳን መታሰቢያ እንዲሆን ነው።”
30/12/2018 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ዶ/ር የሦስቱ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ።
Signed sale Desale
5 Sept 2026, 06:32 UTC159 viewsread 7 September 2026 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፴ †
=> አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሠላሳ በዚች ቀን ከዐሥራ ስድስቱ ነቢያት አንዱ ታላቅ ነቢይ ሚልክያስ አረፈ። ይህም ነቢይ የእስራኤል ልጆች ከተሰደዱበት ከባቢሎን ሀገር በተመለሱ ጊዜ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፋቸው ገሥጿቸዋል።
ሁለተኛም ነቋር ስለሆነ መሥዋዕት ስለ አሥራትና በኵራት ገሥጿቸዋል በዚህ ነቢይ አንደበት እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና ርኅራኄ አድርጋችሁ ምጽዋትን መጽውቱ፣ ዐሥራቴንና በኵራቴንም አስገቡና እስቲ ፈትኑኝ እኔ ከሰማይ ዝናሙን ባላወርድላችሁ በረከትንም አስቲበቃችሁ ባልጨምርላችሁ የምድራችሁንም …
Signed Ermias Adane
5 Sept 2026, 06:32 UTC238 viewsread 7 September 2026 እሊህ ሦስቱ አባቶችም የካህናት አለቆችና እኛ ወደ አለንበት ከቅርጺቱ ሥዕል ጋር መጥተው ወቀሷቸው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነም ነገሩአቸው።
ከዚህም በኋላ ጌታችን አባቶችን ወደቦታችሁ ሒዱ አላቸው ወዲያው ተመለሱ ቅርጺቱንም ወደቦታሽ ተመለሽ አላት እርሷም ወደ ቀደመው አኗኗርዋ ተመለሰች ይህንንም አይተው የካህናት አለቆች አላመኑም ሌላም ብዙ አለ ብነግርህ መወሰን አትችልም ነገር ግን ለብልህ ጥቂት ቃል ትበቃዋለች ለሰነፍ ግን ቢነግሩት በቁም ነገር ላይ አይታመንም።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ማነጋገሩን ገታ ራሱንም እንደሚያንቀላፋ አደረገ እንድርያስም አንቀላፋ እንድርያስንና ደቀ መዛሙርቱን እንዲሸከሙአቸውና ሊገቡበት ወደሚሹት አገር በውጭ እንዲአኖሩዋቸው መላእክት…
Signed Ermias Adane
4 Sept 2026, 07:39 UTC139 viewsread 7 September 2026 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፳፱ †
=>አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ለመወለዱ መታሰቢያ በዓል ሆነ ለእርሱም ምስጋና ክብር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
† ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት †
፨፨፨
ሰላም ለልደትከ ዘተለዓለ አቅሙ፡፡ ወልደተ ጻድቃን ደኀርት ወእለ ቀደሙ፡፡ በይቡስ ጌጋይ እስመ አባላትየ ሐሙ፡፡ ይትከዐው በአሥራውየ በትምህርትከ ዝናሙ፡፡ ወበአምትንትየ ለገቦከ ደሙ፡፡
፨፨፨
=> በዚችም ቀን ኤጲስቆጶስ …
Signed Ermias Adane
4 Sept 2026, 07:39 UTC164 views1 reactionsread 7 September 2026 =>ነሐሴ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር (ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱሳን ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ (ሰማዕታት)
4.አባ ባስልዮስ ጻድቅ (ዘትግራይ)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)
7. ቅዱስ ላሊበላ
=>+"+ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ። +"+ (ሉቃ. 17፥10)
፨፨፨፨
ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ…
👍1
Signed Ermias Adane
2 Sept 2026, 15:40 UTC173 views1 reactionsread 7 September 2026 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፳፯†
=>አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ሰባት በዚች ቀን ሰብሲር ከሚባል አገር ብንያሚንና እኅቱ አውዶክስያ በሰማዕትነት ሞቱ።
የእነዚህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው እንግዳና መጻተኛን የሚወዱ ደጎች ክርስቲያኖች ናቸው ደግሞ ለክርስቲያኖች በሚገባ በበጎ ሥራ ሁሉ የተጠመዱ ቅድስና ያላቸው ናቸው። እሊህንም ቅዱሳን በወለዱዋቸውና በአሳደጓቸው ጊዜ ክርስቲያናዊት ትምህርትን አስተማሩአቸው።
ከዚህም በኋላ ወደዚያች አገር ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ብንያሚንም በሰማ ጊዜ የክብር ባለቤት ስለሆነ ክርስቶስ ደሙን ያፈስ ዘንድ ወደደ። በመኰንኑም ፊት ቁሞ…
❤1
Signed Ermias Adane
1 Sept 2026, 03:46 UTC159 viewsread 7 September 2026 ( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)
ወስብሐት ለእግዚ…
Signed Ermias Adane
1 Sept 2026, 03:46 UTC163 viewsread 7 September 2026 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፳፮ †
=>አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚች ቀን የከበረ አባ ሞይስስና እኅቱ ሣራ በሰማዕትነት ሞቱ።
የእሊህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው ደጎች እጅግም ባለጸጎች ናቸው። የከበረ ሞይስስ ወላጆቹ ከአረፉ በኋላ እኅቱ ሣራን ሊአጋባትና ወላጆቹ የተዉትን ገንዘብም ሊሰጣት እርሱም ወደ ገዳም ሒዶ ሊመነኵስ አሰበ።
ይህን አሳቡንም በነገራት ጊዜ እንዲህ ብላ መለሰችለት እኔን ልታጋባኝ ከወደድክ አስቀድሞ አንተ አግባ አርሱም እንዲህ አላት እኔ ብዙ ኃጢአት ሠርቻለሁ ስለዚህ ኃጢአቴን ለመደምሰስ እመነኵስ ዘንድ እሻለሁ ማግባት አይቻለኝም የ…
Signed Ermias Adane
30 Aug 2026, 08:53 UTC157 viewsread 7 September 2026 ( ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)
ወስብሐት ለእግዚ…
Signed Ermias Adane
30 Aug 2026, 08:53 UTC163 viewsread 7 September 2026 ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ የሚያምር ጐልማሳ አምሳል በቅዱስ ሚካኤል ክነፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ወዳዴ አትፍራ እንግዲህ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን እነደ ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኀፀን መርጬ አከብራሃለሁና እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኩሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ።
ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘብን ሁሉ ለድኖችና ለምስኪኖች በተነ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደ ተከፈተ ትቶ ምርጒዙን ይዞ…
Signed Ermias Adane
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Ariosfagos1271. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.