6 Aug 2026, 19:37 UTC446 views6 reactionsread 12 August 2026 ስላመንኩት፥ ለሰጠኝ ፍቅር ዋጋ ስለሰጠሁ፥ እየተመቸኝ አልችልም ስለማልል፥ ስለሚወዱኝና ደጅ ስለሚጠኑ ወንዶች አያወራሁ ስለማልመጻደቅበት ...
እኔን የማግኘት መጓጓቱ ቀነሰ
ጥፋቱ ላይ ስለማላተኩር፥ ቅሬታዬን ስለማላሳየው፥ በልቤ ከሌሎች ጋ ስለማላወዳድረው...የማይገባኝ መሰለው!
ቅር ይለዋል ብዬ የማስበውን ስለማላደርግ፥ ቅድሚያ ስለምሰጠው፥ ስለምወደው ዋጋዬ አልገባውም።
እየተወኝ ሁኔታው ሁሉ ውለታ እንደዋለ ነው። እየበደለ ውለታ ዋልኩ እንደሚል ሰው ክፉ የለም!
ክፉ አለመሆኔን እንዴት እንዳለማወቅ መቁጠር ተቻለው?!
ረስቶት ነው..!? እንዴት አድርጎ ቀልቤን ለመግዛት እንደደከመ። ረስቶት ነው እንዴት አድርጎ ደጅ ጠንቶ እንደቀረበኝ። ረስቶት ነው እን…
❤6
24 Jul 2026, 06:41 UTC≈1,120 views21 reactionsread 12 August 2026 “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ!?”
ዝምታ ይረብሸኛል።
ለዚያም ነው፥ መንገድ ስሔድ መጽሐፍ ይዤ የምዞረው፣ ሁሌም ጆሮዬ ውስጥ ‘ኤርፎን’ የምወትፈው፣ ልተኛ ስል፥ ያለችውን ፀጥታ እንኳን ላለማስተናገድ፥ የኾነ ነገር ከፍቼ ነው የምተኛው ...
በዝምታ ውስጥ ከመኾን፥ ዝም ብሎ ከሚቀደደው ቱሪናፋው ከቤ ጋር ብውል እመርጣለሁ። ዝምታ ሽሽት የማልደውልበት፣ የማላነበው፣ የማልሰማው ዜና የለም።
ዝምታ እፈራለሁ!
መንገድ ስሔድ… ስቀመጥ!
የማነበው መጽሐፍ ካልያዝኩ፣ ስራመድ የምሰማበት ኤርፎን ካልወተፍኩ…. ፖሊሶች አቻኩለው ከቤት አስወጥተውኝ ነው የሚሆነው!
ዝምታ እፈራለሁ!
አስታውሳለሁ፤ 12ኛ ክፍል ነበርኩ። ሙዚቃ ከፍቼ እያጠናሁ፥ የአጎ…
❤14🔥7
23 Jul 2026, 18:19 UTC922 views6 reactionsread 12 August 2026 ወጣቶች ነበርን
በእውቀቱ ስዩም
ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ
ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ
ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ
ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤
ወጣቶች ነበርን
ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን
ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን
ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤
በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን
ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤
ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ
ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ
ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን
የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን
ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ
ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ
የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ
ምትቀበለን ፣ እየመሰለን
ከቁመታችን በላይ፣ የዘለልን፤
ወጣቶች ነበርን
ዛሬ እንደዋዛ
ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን፤
❤6
18 Jul 2026, 06:57 UTC≈1,310 views8 reactionsread 12 August 2026 "ለምንድነው ድንገት የተውከኝ አለቺኝ ?"
"እኔ'ንጃ ምን አልባት ፈርቼሽ ይሆናል"።
በአይኗ እየተቅለሰለሰች "ምኔ አስፈራህ ትባ'ላለች አሉህ ወይ "
ጥቁረቷ የዐይኗን ውበት ጨምሮታል ጥቁረቷ ጥርሷን ጥርሰ በረዶ ናት እንድትባል ያደረጋት ይመስለኛል።
ስታምር !
ትክ ብዬ እያየኋት
"የመወደድ ርኃብ ያለብሽ ይመስላል "አልኳት
ምን ማለት ነው ??
"የሚወደኝ አጥቼ ማለት ነው? " ሳቀች አሳሳቋ ፌዝ አዝሏል
አይምሰልሽ
የአንዳንድ ርሃብ ምንጭ እኮ የአቅርቦት እጥረት አይደለም የአስተዳደግ ጠባሳም ሊሆን ይችላል።
ቀጠሮ ኖርበት የክት ልብሱን አጥቦ ፀሃይን እንደሚጠብቅ ሰው ነው ቀልብሽ ቆሌሽ ሁሉ ነገርሽ መወደድሽን የሚጠብቀው ....
እመኚ…
❤6👍2
12 Jul 2026, 06:43 UTC≈1,440 views8 reactionsread 12 August 2026 "እናቴ ሦስቴ አግብታ ሦስቴ ፈታለች። ከእህቴ እና ከወንድሜ ጋር አባት እንደማንጋራ ታውቂያለሽ። እናቴ አዲስ ሕይወት በጀመረች ቁጥር በትዳሯ እንደምትፀና የምትወራረድ ቢሆንም፣ አዲሱ ሕይወት ብዙም ሳይቆይ መዝመም ይጀምርና የመጠገን እድልን ሳያገኝ ይፈርሳል።ይህ እንዴት ሆነ?››
‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››
‹‹ወንድሜ ለትዳር ምንም አይነት መጓጓት እንዳልነበረው ታውቂያለሽ... እማማና ዘመዶቿ ወትውተውት ካገባ በኋላ በሦስት ዓመቱ ተፋታ። ከትዳሩ መፍረስ በኋላ ለገዛ ልጁ እንኳን ግድ የለሽ ሆኖ የተገለለ ኑሮ እየገፋ እንደሆነ ታውቂያለሽ።... ይህ እርግማን አይደለም?››
‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››
‹‹እህቴ ቁጥብ እና በራስ መተማመን ያላት ሴት …
❤7👍1
11 Jul 2026, 12:55 UTC≈1,270 views23 reactionsread 12 August 2026 ኦሮማን
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠና…
😁15❤4🫡3🔥1
18 Jun 2026, 06:36 UTC≈1,950 views25 reactionsread 12 August 2026 አንድ ልጅ አጣብሰኝ እስቲ አለችኝ ። ያን ወቅት አንድ ልጅ አጣብሰኝ ሲለኝ ስለነበር እና ማች ያደርጋሉ ስላልኩ ።
አገናኘዋቸው ።
ከመሃል ወጣው ።
እሱ እንድወጣ አልፈለገም መሰለኝ
ያሰበውን ሁሉ ይነግረኛል በተለይ ያደረጉትን ሲነግረኝ ልጎመጅ ይዳዳኛል ....
"ምን አይነት አበባ ....ምን አይነት ቀሽት ልጅ ነው ያጣበስከኝ እንዴት እንደ ምትጣፍጥ .....ደሞ ሰውነቷ ደሞ ፍቅር ላይ አኳኃኗ "
በሌላ ቀን ...
"I think አስተዳደጓ ነው መሰለኝ ነፃ ነች ክላስ ይዛ ተሽሞንሙና ትጠብቀኛለች ...ደሞ ዋዛ እንዳመስልህ...ትሽከረከረዋለች ....OMG"
በሌላ ቀን
"አንተ እቺን መረቅ ልጅ አገናኝተኸኝ እኮ በቃ ኑሮዬ ሰመረ ....እንማጠ…
😁16👏5❤4
12 Jun 2026, 17:09 UTC≈2,120 views17 reactionsread 12 August 2026 በአፍላነቴ በተፈጥሮ አስገዳጅነት ጭምር ብርቱ የሆነ የተቃራኒ ጾታ ፍላጎት የተፈጠረብኝ ቢሆንም 'ሰይጣን አለባት' በሚል ተልካሻ ምክንያት የሚንቁኝና የሚያገሉኝ በዙ፡፡
በተገፋሁ ቁጥር ፍላጎቴ በእጥፍ አደገ፡፡ 'አንድ ወንድ አፈቅርሻለሁ ካለኝ ሳላቅማማ እኔም አፈቅርሃለሁ እለዋለሁ' ብዬ የነበረ ቢሆንም የፍቅር ጥያቄ የሚያቀርብልኝ ጠፋ፡፡ያኔ ለራሴ የፍቅር ደብዳቤ ፃፍኩ፡፡
‹‹ጫሊ ጉድ ሰማሽ?›› አልኳት የክፍላችንን ፍልቅልቅ ተማሪ
‹‹የምን ጉድ?››
‹‹ደብዳቤ ተፃፈልኝ››
‹‹ከማን?››
‹‹አላውቅም››
‹‹እንዴት አታውቂም?››
‹‹ስም የለውም፡፡ ግን ከዚህ በፊትም ጽፎልኝ ያውቃል›› ደብዳቤውን ከደብተሬ ውስጥ አውጥቼ ሰጠኋት፡፡
ወሬው ተናፈሰ፡፡ የሆነ…
👍8❤3💔3🤣3
11 Jun 2026, 17:10 UTC≈1,800 views9 reactionsread 12 August 2026 ምንገድ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)
በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ ኡራኤል ፊትለፊት ካለው አስፋልት ላይ ስደርስ የሚገርም ነገር ተከሰተ፤ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ቡሌ በፌስታል, ሸክፎ አስፋልት እያቁዋረጠ ሳለ አንድ ሞተረኛ ከላይ ሲንደርደር መጥቶ ደንብቆ ጣለው ፤ የሸገር ሞተረኞች ለምን እንደሚካልቡ አይገባኝም፤ አለምን ከጥፋት የሚታደግ መልክት ለማድረስ የሚነዱ እንጂ የጠወለገ በለጨ የጫኑ አይመስሉም፤
ሞተረኛው ከሞተሩ ተስፈንጥሮ አስፋልቱ ዳር ተዘረረ ፤ ሞተሩ ግን በራሱ ፈቃድ እየበረረ ሂዶ ባቅራቢያው ከሚገኝ ጋራጅ ውስጥ ገብቶ ተሰወረ፤ የጎዳናው ሰውየ ተሽቀንጥሮ መንገዱ ጠርዝ ላይ ተገኘ፤ ወድያው…
👍6😁3
9 Jun 2026, 06:51 UTC≈1,710 views16 reactionsread 12 August 2026 ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካልደረሰ መውጣቷ አይቀርም" ብሎ ችላ ይላታል።
ወዲያው ግን አንድ በጣም አስደንጋጭ ነገር ትዝ ይለውና፣ በአስደናቂ ጀግንነት ድጋሚ ዘሎ ወደሚቃጠለው ቤት ይገባል። ሚስቱንም አንከብክቦ ይዟት ይወጣል።
በኋላ ላይ ጋዜጠኞች ተሰብስበው፦ "እንዴት በዚህ ድፍረት ወደሚቃጠለው ቤት ገብተህ ሚስትህን ልታተርፋት ቻልክ? ስታገኛትስ በምን ሁኔታ ላይ ነበረች?" ብለው ጠየቁት።
ስሜቱን በራሱ ቋንቋ እንስማው...
我不能把手机和妻子单独留在家里。我一直担心她会拿起我的手机偷看信息。当我急…
🤣14❤1🗿1
6 Jun 2026, 06:17 UTC≈1,740 views11 reactionsread 12 August 2026 "የአስራ ሰባት አመት ወንድም እንዳለኝ ነግሬሽ አውቃለሁ?"
"አላስታውስም"
"የአስራ ሰባት አመት ወንድም አለኝ"
"ምን ሆነ?"
"ዘመቷል"
"መዝመት ማለት?.... ወደ ጦርነቱ?"
ጮኸች። በቡናቤቱ የነበሩ ሌሎች ሰዎች በሙዚቃውና በግል ወሬያቸው ተይዘው ባይሆን ድንጋጤ ያዘለ ድምጿ ያስደነግጣቸው ነበር። ወንድሜ እንደዘመተ የሰማኹ ቀን 'ወደ ጦርነቱ ነው የዘመተው?' ብዬ እንደተደናበርኩ እሷም ተደናበረች
"አዎ። ወደ ጦርነቱ ነው የዘመተው"
"ቤተሰብ እንዴት ፈቀደ?"
"በቤተሰብ ፈቃድ አይደለም"
"ታፍሶ ነው?"
"አልታፈሰም። ስለ ጦርነቱ እንደ አቅሙ መረጃ ይሰበስብ ነበር። ነሸጠውና ተመዘገበ። ነገር ግን ወደ ስልጠና ከገባ በኋላ ስልክ አግኝቶ ደውሎልኝ እን…
❤11
5 Jun 2026, 05:12 UTC≈1,530 views16 reactionsread 12 August 2026 ‹‹እማዬ ስራ ስይዝ ሀበሻ ቀሚስ እገዛልሻለሁ››
‹‹ለማን?››
‹‹ላንቺ ነዋ››
‹‹ምን ላደርገው?››
‹‹እንድትለብሺው››
‹‹እኔው?›› ከንፈሯን እንደ አሽሙረኛ ሴት ታጣምመዋለች
‹‹አትፈልጊም?››
‹‹ጽድቁ ቀርቶብኝ በወጉ በተኮነንኩ››
‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹ይልቅ ለራስሽ አስቢ። እኔ ረፍዶብኛል። ከዚህ በኃላ ማጌጥ አልፈልግም። አንቺ ሰው ከሆንሽ ለእኔ ከበቂ በላይ ነው››
‹‹ሰው ከሆንኩ በኃላስ?››
‹‹ከዛማ ምን እፈልጋለሁ?››
‹‹እንደ ሌሎች እናቶች መሆን አትፈልጊም?››
‹‹እኔ አሁን ከስሜያለሁ። ለማጌጥ ረፍዶብኛል፣ ለመዋብ ብሞክር አያምርብኝም››
ሁሉም ነገር ከእጇ ያመለጠ ይመስላታል፡፡ መጎሳቆልን እጣፋንታዋ አድርጋ ስለተቀበለች የተሻለ ነገር…
💔14❤2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @BookstoresAZ. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.