28 Aug 2026, 21:12 UTC19 viewsread 29 August 2026 Photo
90ኛው ደቂቃ ድረስ 2ለ0 እየተመራ የቆየው ፒኤስጂ ነጥብ ተጋርቶ ወቷል::
በፈረንሳይ ሊግ አ ከሜዳው ውጪ ሊልን የገጠመው ፓሪስ ሴንት ዤርመን 90ኛው ደቂቃ ድረስ 2ለ0 እየተመራ የቆየ ቢሆንም ቪቲንሃ እና ማርኪንሆስ ባስቆጠሯቸው ግቦች ነጥብ መጋራት ችሏል::
በጨዋታው ሀራልድሰን እና ባካዋ ለሊል ግብ ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ሲሆኑ ኦልቪየር ዢሩ ሁለት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል::
Signed Tamirat Kebede
28 Aug 2026, 21:04 UTC22 viewsread 29 August 2026 Photo
ማንቼስተር ሲቲ ድል ቀንቶታል::
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሃግብር ወደ ሴል ሃረስት ፓርክ ተጉዞ ክሪስታል ፓላስን የገጠመው ማንቼስተር ሲቲ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል:: በጨዋታው ሀላንድ እና ቼርኪ ሁለት ሁለት ግቦችን ማስቆጠር የቻሉ ሲሆን የፓላስን ብቸኛ ግብ ዶናሩማ በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል::
Signed Tamirat Kebede
28 Aug 2026, 20:58 UTC22 viewsread 29 August 2026 Photo
የሩበን አሞሪም ኤሲ ሚላን ተከታትይ ድሉን አሳክቷል::
በጣሊያን ሴሪ ኤ ሁለተኛ ሳምንት በሳን ሲሮ ቬኔዚያን የገጠመው ኤሲ ሚላን 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል:: በጨዋታው ጎንካሎ ራሞስ ግብ ሲያስቆጥር ቀሪዋን ግብ ቬኔዚያዎች በራሳቸው መረብ ላይ አሳርፈዋል::
Signed Tamirat Kebede
28 Aug 2026, 20:33 UTC23 viewsread 29 August 2026 Photo
ባየርን ሙኒክ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል::
በጀርመን ቡንደስ ሊጋ በሜዳው አሊያንዝ አሬና ስቱትጋርትን የገጠመው የቪንሴንት ኮምፓኒው ባየርን ሙኒክ 5ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል::
በጨዋታው ኡፔሜካኖ, ኦሊሴ, ፓቭሎቪች, እና ዲያዝ አንድ አንድ ግብ ሲያስቆጥሩ ቀሪዋን አንድ ግብ ስቱትጋርቶች በራሳቸው ግብ ላይ አሳርፈዋል::
በጨዋታው አዲሱ ፈራሚ እስማኤል ሳይባሪ እና ጆሾዋ ኪሚች ሁለት ሁለት ኳሶችን ለግብ አመቻችተው ማቀበል ችለዋል::
Signed Tamirat Kebede
28 Aug 2026, 20:17 UTC22 viewsread 29 August 2026 Photo
አል ነስር በሮናልዶ ግብ አሸንፏል::
በሳውዲ ፕሮ ሊግ አል ነስር ከአል ታዎን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ሳሙ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነስርን አሸናፊ ያደረጉ ግቦችን አስቆጥረዋል::
የማሸነፊያዋን ግብ ያስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ህይወቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች 978 ማድረስ ችሏል::
ውጤቱን ተከትሎ አል ነስር ከ4 ጨዋታዎች 12 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሊጉን እየመራ ይገኛል::
Signed Tamirat Kebede
27 Aug 2026, 21:16 UTC50 viewsread 29 August 2026 Photo
ባርሴሎና ላ ሊጋውን ዳግም መምራት ጀምሯል::
በስፔን ላሊጋ ተስተካካይ መርሐ ግብር በካምፕ ኑ አትሌቲኮ ቢልባኦን የገጠመው ባርሴሎና በራፊና እና ፌርሚን ሎፔዝ ግቦች 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል:: ውጤቱን ተከትሎ ብሉ ግራናዳዎቹ ነጥባቸውን 6 በማድረስ ላሊጋውን ዳግም መምራት የጀመሩ ሲሆን በሁለት ጨዋታዎች 7ግቦችን አስቆጥረው ምንም ግብ ሳይቆጠርባቸው መዝለቅ ችለዋል:: በጨዋታው አዲሱ የባርሴሎና ፈራሚ ሮድሪ የክለቡ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል::
Signed Tamirat Kebede
27 Aug 2026, 21:01 UTC55 views1 reactionsread 29 August 2026 Photo
ቼልሲ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል::
በካራባኦ ካፕ ሁለተኛ ዙር መርሃግብር ቼልሲ በሜዳው ስታንፎርድ ብሪጅ ሉተን ታውንን ገጥሞ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደቀጣዩ ዙር ያለፈ ሲሆን በጨዋታው አዲሱ ፈራሚ ዳኒ ዌልቤክ አንድ ግብ ሲያስቆጥር ሌላኛዋን ግብ ኦዶፊን በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል:: ውጤቱን ተከትሎ ሰማያዊዎቹ በሶስተኛው ዙር ከሊድስ ዩናይትድ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
👍1
Signed Tamirat Kebede
27 Aug 2026, 19:08 UTC68 views2 reactionsread 29 August 2026 Photo
ቼልሲ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል::
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አርጀንቲናዊውን የ33 ዓመት ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን በ7.5 ሚሊዮን ፓውንድ ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን ግብ ጠባቂው አንድ ተጨማሪ ዓመት ሊራዘም በሚችል የሁለት አመታት ውል ሰማያዊዎቹን የሚቀላቀል ይሆናል::
👍2
Signed Tamirat Kebede
27 Aug 2026, 08:34 UTC86 viewsread 29 August 2026 Photo
ሊቨርፑል ባርኮላን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል::
Signed Tamirat Kebede
26 Aug 2026, 22:03 UTC95 viewsread 29 August 2026 Photo
የ2026/27 ቻምፒዮንስ ሊግ 36 ተሳታፊ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል::
በአዲሱ የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የተደረጉ የማጣሪያ ጨዋታዎች ምሽት ከተጠናቀቁ በኃላ ሁሉም የመድረኩ ተሳታፊዎች የተለዩ ሲሆን ሐሙስ ከሰዓት የመርሃ ግብር ድልድል እጣ የማውጣት ስነስርዓት የሚደረግ ይሆናል::
Signed Tamirat Kebede
26 Aug 2026, 21:38 UTC85 viewsread 29 August 2026 Photo
የካራባኦ ካፕ 3ኛ ዙር ድልድል እጣ ወቷል::
በዚህም መሰረት :-
ሊቨርፑል ከ ቶተንሃም
ኢፕስዊች ከ አርሴናል
ማንቼስተር ሲቲ ከ ኖርዊች
ማንቼስተር ዩናይትድ ከ ብራይተን
የቼልሲ እና ሉተን አሸናፊ ከ ሊስድ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል::
Signed Tamirat Kebede
26 Aug 2026, 21:11 UTC63 viewsread 29 August 2026 Photo
ሪያል ማድሪድ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል::
በስፔን ላሊጋ ተስተካካይ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ሳንቲያጎ ቤርናባኦ ላይ ሪያል ሶሴዳድን ገጥሞ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በጨዋታው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ሀትሪክ መስራት ችሏል። የሎስ ብላንኮስን ቀሪ ጎል ቪንሰስ ጁኒየር ከመረብ ሲያሳርፍ ለሪያል ሶሴዳድ ሱቺች ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
በጨዋታው ጁድ ቤሊንግሀም በጨዋታው ሁለት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ሲችል ውጤቱን ተከትሎ የሆዜ ሞሪንሆ ቡድን 6 ነጥቦችን ሰብስቦ ሊጉን መምራት ጀምሯል::
Signed Tamirat Kebede
Showing the 12 most recent of 56 posts we hold for @Crayfista. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.