6 Aug 2026, 04:27 UTC301 views21 reactionsread 7 August 2026 ቀን 200
ያልታረሰውን መሬት ማረስና የእግዚአብሔር ጽድቅ ዝናብ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ሆሴዕ 8-14
ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ ዕዳሪውንም መሬት ዕረሱ፤ እርሱም መጥቶ፣ ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።" (ትንቢተ ሆሴዕ 10፥12)
በነቢዩ ሆሴዕ ዘመን የእስራኤል ሕዝብ ልብ በዓለማዊነት፣ በጥፋትና በባዕድ አምልኮ ምክንያት ደንድኖ፣ ልክ እንደ አልታረሰ ድንጋያማ መሬት ሆኖ ነበር። ዘር በደረቀና ባልታረሰ መሬት ላይ ቢዘራ ፍሬ እንደማያፈራ ሁሉ፣ የደነደነ ልብም የእግዚአብሔርን ቃልና መለኮታዊ በረከት ሊቀበል አይችልም። ሆሴዕ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው የልባቸውን …
🙏14❤7
6 Aug 2026, 04:27 UTC282 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤3
4 Aug 2026, 20:53 UTC349 views25 reactionsread 7 August 2026 ቀን 199
እግዚአብሔርን ማወቅና እንደ ንጋት የሚያበራው መታደስ
የዕለቱ የመጽሃፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ሆሴዕ 1-7
"እግዚአብሔርን እንወቀው፤ የበለጠ እናውቀውም ዘንድ አጥብቀን እንከተለው፤ እንደ ንጋት ብርሃን፣ በርግጥ ይገለጣል፤ ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣ እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።" (ትንቢተ ሆሴዕ 6፥3)
በነቢዩ ሆሴዕ ዘመን የነበሩት የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔርን ትተው ወደ ጣዖታት በመሄዳቸውና ከሕጉ በመራቃቸው ምክንያት መንፈሳዊና ምድራዊ ውድቀት ገጥሟቸው ነበር። ሆኖም እግዚአብሔር በታላቅ ፍቅሩና ምሕረቱ ወደ እርሱ እንዲመለሱ ጥሪ ያቀርብላቸዋል። እውነተኛ መታደስ የሚጀምረው እግዚአብሔርን ለማወቅና እርሱን ለመከተል …
🙏15❤10
4 Aug 2026, 20:53 UTC308 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤5
3 Aug 2026, 19:53 UTC376 views18 reactionsread 7 August 2026 ቀን 198
በሙሉ ልቡ አደረገ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - 2 ነገስት 18:1-18፥ 2 ዜና 29-31፥ መዝሙር 48
"በእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት በሕጉና በትእዛዙ አምላኩን ይፈልግ ዘንድ የጀመረውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ልቡ አደረገ፥ ተከናወነለትም።" (2 ዜና መዋዕል 31፥21)
ንጉሥ ሕዝቅያስ በይሁዳ ሲነግሥ አገሪቱ በመንፈሳዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ ነበረች። አባቱ አካዝ የቤተ መቅደሱን ደጆች ዘግቶ፣ ጣዖታትን አቁሞና አገሪቱን ለጠላት አሳልፎ ሰጥቶ ነበር። ሕዝቅያስ ግን ገና በነገሠ በጀመሪያው ወር የቤተ መቅደሱን ደጆች ከፈተ፣ አጸዳ፣ አምልኮን መለሰ፣ እንዲሁም ሕዝቡን ወደ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ የሕዝ…
🙏14❤4
3 Aug 2026, 19:53 UTC353 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
🙏5
2 Aug 2026, 19:29 UTC425 views17 reactionsread 7 August 2026 ቀን 197
የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራና ዘላለማዊ ታማኝነት
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ኢሳይያስ 23-27
"አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አከብርሃለሁ፥ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ ድንቅ ነገርን፥ ከጥንት የነበረውን እውነተኛና ታማኝ አሳብ አድርገሃልና።" (ትንቢተ ኢሳይያስ 25፥1)
በኢሳይያስ ምዕራፍ 23 እስከ 27 ባሉት ክፍሎች ውስጥ በንግድና በሃብቷ ትመካ በነበረችው በጢሮስ ላይ የተነገረው ፍርድና በዓለም ሁሉ ላይ የሚመጣው ታላቅ የእግዚአብሔር ፍርድ ይታያል። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ትርምስና ውድቀት መካከል እግዚአብሔርን የሚያውቁትና የሚተመኑበት ሕዝቦች አምላካቸውን ያመሰግናሉ። ከዚህ ጥቅስ የምንማራቸውን ሦስት ቁልፍ እውነቶች እንመልከት፦
1. …
❤9🙏8
2 Aug 2026, 19:29 UTC417 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤4
1 Aug 2026, 20:11 UTC526 views26 reactionsread 7 August 2026 ቀን 196
አምላክን ማወቅና በጽኑ እምነት መቆም
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ኢሳይያስ 18-22
"እግዚአብሔርም በግብፅ ዘንድ የታወቀ ይሆናል፥ ግብፃውያንም በዚያ ቀን እግዚአብሔርን ያውቃሉ፤ በመሥዋዕትና በቁርባን ያመልካሉ፥ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ ይፈጽሙትማል።" (ትነቢተ ኢሳይያስ 19፥21)
በኢሳይያስ ምዕራፍ 18 እስከ 22 ባሉት ክፍሎች ውስጥ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ (ኩሽ)፣ በግብፅ፣ በባቢሎን፣ በኤዶምና በኢየሩሳሌም ላይ ስላለው ፍርድና ውድቀት ይናገራል። ግብፅ በዚያ ዘመን በምድራዊ ጥበቧ፣ በጠንቋዮቿና በወታደራዊ ኃይሏ የምትመካ ትልቅ አገር ነበረች። ነገር ግን እግዚአብሔር ምድራዊ አቅሟን ሁሉ ሲመታው፣ የቆመችበት መሠረት እን…
🙏18❤8
1 Aug 2026, 20:11 UTC418 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
🙏4❤1
31 Jul 2026, 20:14 UTC555 views24 reactionsread 7 August 2026 ቀን 195
የእግዚአብሔር ሉዓላዊ አሳብና የማይወድቅ ዓላማ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ኢሳይያስ 13-17
"የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሏል፦ በእውነት እኔ እንዳሰብሁት ይሆናል፥ እንደ መከርሁትም ይቆማል።" (ትነቢተ ኢሳይያስ 14፥24)
በኢሳይያስ ምዕራፍ 13 እስከ 17 ባሉት ክፍሎች ውስጥ እግዚአብሔር በዘመኑ በነበሩት እንደ ባቢሎን፣ አሦር፣ ሞዓብና ደማስቆ ባሉ ታላላቅና አስፈሪ የዓለም መንግሥታት ላይ ፍርዱን ሲናገር እንመለከታለን። ሰዎች በምድራዊ ኃይላቸው፣ በጦር አቅማቸው ወይም በግንቦቻቸው ቢመኩም፣ በእግዚአብሔር ፊት ግን እንደ ገለባ ናቸው። ይህ ጥቅስ በዓለም ክስተቶችና በገዛ ሕይወታችን ላይ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር …
🙏20❤4
31 Jul 2026, 20:14 UTC432 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤5
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @DailyWordOfLife. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.