25 Jul 2026, 21:28 UTC77 views2 reactionsread 8 August 2026 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል!
ሐምሌ ፲፱ ቀን፣ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣንና ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስን ከፈላ ውኃ ያዳነበትን በዓል እናከብራለን።
▪︎.ዲዮቅልጥያኖስ፡ በዚያን ዘመን የነበረ ክርስቲያኖችን የሚጠላ ጨካኝ ንጉሥ ነበር። ክርስቲያኖች እምነታቸውን እንዲክዱና ለጣዖታት እንዲሰግዱ ያስገድድ ነበር። አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉና ክርስቲያኖች እንዲሰደዱ አዋጅ ያወጣው እርሱ ነው።
▪︎.ቅዱስ ቂርቆስ፡ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ። ገና የሦስት ዓመት ሕፃን ቢሆንም ስለ ክርስቶስ በመመስከርና ለእምነቱ ጸንቶ በመቆም አርዓያ ሆኖናል።…
❤2
11 Jul 2026, 12:02 UTC131 views1 reactionsread 8 August 2026 #ሐምሌ_5
#ቅዱስ_ጳውሎስና_ቅዱስ_ጴጥሮስ
ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።
በዚህች ዕለት ስለክርስቶስ የተገፋ፣ ስለክርስቶስ የተወገረ፣ ስለክርስቶስ የተሰደደ፣ ስለክርስቶስ የታሰረ፣ ስለክርስቶስ ከአለም ሃሳብና መሻቷ የተለየ፣ ስለክርስቶስ ራሱን የለየ፣ ስለክርስቶስ ምእመናን ያነጸ፣ ስለክርስቶስ መልካምን መልእክት የፃፈ #ቅዱስ_ጳውሎስ ሰማዕት ሆነ። ነገር ግን በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ህያው ነው፤ የጽድቅን አክሊል ተቀበለ ከክርስቶስ ጋር መኖርን እንደናፈቀ አገኛት፤ ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን ማኅበር ተቀላቀለ ከመላእክት ምስጋና ተጋራ በሥጋ ሕይወቱ ከእው…
👍1
18 Jun 2026, 18:04 UTC422 views4 reactionsread 8 August 2026 🕊 † ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት † 🕊 ሰኔ ፲፪
መላእክት የሚለው ቃል መልእክተኞች ‘ተላላኪዎች’የእግዚአብሔር ይቅርታ ወደ ሰው የሰውን ልመና ወደእግዚአብሔር የሚያደርሱ’ የእግዚአብሔር ልዩ ወዳጆች ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ አለቆች ገዥዎች ወይም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ማለት ይሆናል፡፡ ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ እግዚአብሔር ‘እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?›› ማለት ነው፡፡ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል /ዳን.10፥13’ 2፥1/ ውስጥ ነው፡፡በመጽሐፈ ሄኖክም ለበርካታ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ከዚህ ሌላ በብሉይ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍት በኪዳነ አብርሃም ውስጥ ተጠቅሶም ይገኛል፡፡
ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይ…
❤4
31 May 2026, 19:04 UTC565 views3 reactionsread 8 August 2026 ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) መቼ ይገባል ?
ለምንስ ይጾማል ?
❖ ጾመ ሐዋርያት ወይም ሰኔ ጾም ግንቦት 24 # ይገባል (ይጀምራል) ሐምሌ 5 ቀን ይፈታል።
❖ ይህ ጾም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ጾም ነው።
❖ የሰኔ ጾም ይህ ጾም የሐዋርያት ጾም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ጾም ተባለ ቢሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት ጾም ስለሆነ ነው።
የሰኔ ጾም የሚጾምበት ጊዜያት
❖ የሰኔ ጾም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይጾማል
❖ የሰኔ ጾምን እስከ 9 ሰአት እንድንጾም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።
❖ ጾሙ የሚገባበት ቀን በየ…
👏3
30 May 2026, 20:29 UTC133 views1 reactionsread 8 August 2026 ርዕስ፦ በዓለ ጰራቅሊጦስ - የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን! 💡⛪
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ (በዓለ ኃምሳ) በዓል አደረሳችሁ!
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ፣ በኢየሩሳሌም ከተማ በዚያች ጠባብ ሰገነት ላይ ታላቅ የዝምታና የፍርሃት ጊዜ ነበር። ሐዋርያት አይሁድን በመፍራት ደጆቹን ዘግተው፣ ልባቸው በሐዘን ተሰብሮ፣ ጌታ የሰጣቸውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ በትዕግሥትና በአንድ ልብ ሆነው ያችን 10 ቀን አሳለፉ።
ይህች ታሪካዊት ቤት የወንጌላዊው የቅዱስ ማርቆስ እናት የማርያም ቤት ስትሆን፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ «ጽርሐ ጽዮን» ተብላ ትጠራለች። ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተወለደችባት በመሆኑም «ማኅጸነ ጽዮን» (የቤ…
👍1
20 May 2026, 20:00 UTC316 viewsread 8 August 2026 የጌታችን ዕርገት! 🕊️
“ዕርገት” የሚለው ቃል “ዐርገ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከታች ወደ ላይ መውጣት፣ ከፍ ከፍ ማለት፣ ማረግ ማለት ነው፡። ዕርገት ከጌታችን ከ9ኙ ዓበይት በዓላት ውስጥ አንዱ ነወ። ጌታችን መድኃኒታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ፣ ለተከታታይ 40 ቀናት ለደቀ መዛሙርቱ እየታያቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ምስጢራትን አስተማራቸው። በአርባኛው ቀን ግን፣ ታሪኩ አዲስ ምዕራፍ ሊይዝ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተሰበሰቡ።
ሐዋርያቱ ጌታ ሊለያቸው እንደሆነ ሲረዱ ልባቸው በሐዘን ተነካ። "ያለ አንተ እንዴት እንኖራለን?" የሚል ስጋት ቢያድርባቸውም፣ ጌታችን ግን የኃይልን ተስፋ ሰጣቸው፦ "መንፈስ ቅዱስ …
18 May 2026, 18:20 UTC471 views1 reactionsread 8 August 2026 🌿 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ
💦 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን በ505 ዓ/ም በአክሱም ከተማ ተወለደ። እናቱ ክርስቲና አባቱ ይስሀቅ ይባላሉ።
🫧 ቅዱስ ያሬድ በሰባት ዓመቱ አባቱ ስለሞቱ እናቱ ክርስቲና የአክሱም ገበዝ ለነበረዉ ለአጎቱ ለጌዲዮን እንዲያስተምረዉ ሰጠችዉ። ቅዱስ ያሬድ ከአጎቱ ዘንድ ገብቶ በሚማርበት ጊዜ ትምህርት አይገባዉም ነበር በዚህ ምክንያት አጎቱ ስለሚገርፈዉ ያሬድ መታገስ ተስኖት ከአጎቱ ተለይቶ ጠፋ። በዚያም በአንድ ዛፍ ስር ተጠግቶ ሳለ አንድ ትል ከቅጠሉ ለመዉጣት እየሞከረ ሲወድቅ እንደገና ከቅጠሉ ለመዉጣት ሲወጣ እየወደቀ ለስድስት ጊዜ ሲሞክር ተመለከተ። እንዲህ ሲሆን በ7ተኛዉ ቅጠሉ( ዛፍ) ላይ እንደወጣ ሲያይ እኔማ ተስፋ መቁረጥ የለ…
👍1
8 May 2026, 18:39 UTC787 viewsread 8 August 2026 ግንቦት ፩ ልደታ ለማርያም
🌿 የሰዉ ልጅ በኃጢአት ተይዞ ከእግዚአብሔርም ተጣልቶ 5500 ዘመን ሊደፍን ጥቂት ዓመታት ሲቀረዉ ጴጥርቃና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተዉ ይኖሩ ነበር ይህ ቀረሽ የማይባሉ ሀብታሞችም ጻድቅም ነበሩ፤ ነገር ግን የሚወርሳቸዉ ልጅ አልነበራቸዉምና መካን ነበሩ በዚህም ፍጹም ያዝናሉ ወደ እግዚአብሔርም ይጸልያሉ።
🌞 ቴክታም በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ ፯ት ትዉልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችዉ። ህልም ፈቺ ዘንድም ሄደዉ ህልሙን አስፈቱ ደጋግ ሴት ልጆች እንደሚወልዱ ፯ተኛዋ ጨረቃን መዉለዷ ከሰዉና ከመላእክት…
12 Apr 2026, 00:30 UTC≈1,110 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
✝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም
"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ
ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ
ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና"
፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን።
✝ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ✝
ዲ/ን የአብስራ
https://t.me/God2929
https://t.me/God2929
https://t.me/God2929
👍1
11 Apr 2026, 06:37 UTC767 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
👉 ቅዳሜ
ቀዳም ስዑር ትባላለች
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለምለም ቅዳሜ ይባላል
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቄጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ…
❤3
10 Apr 2026, 05:43 UTC831 views3 reactionsread 8 August 2026 ሰሙነ ሕማማት እለተ አርብ ✝
✝️ የስቅለት አርብ ፦ አምላካችን በጥንተ ተፈጥሮ አዳምን በዕለተ አርብ ፈጥሮታል። ዳግመኛም በዚያዉ ዕለት አዳምን ለማዳን ራሱ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል። መሥዋዕት የሆነዉ ደግሞ በመስቀል ተሰቅሎ ነዉና ዕለቱ ስቅለተ አርብ ተብሎ ይጠራል።
🪄 ማኅበረ አይሁድ ከኀሙስ ምሽት ሥስት ሰዓት ጀምረዉ እስከ አርብ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ለ18 ሰዓታት በጌታችን ላይ ብዙ መከራ አድርሰዉበታል። ክርስቶስም " ሥጋዬን በበላችሁ ጊዜ ደሜንም በጠጣችሁ ሰዓት " መከራዬን ሞቴን ትናገራላችሁ ባለዉ መሠረት ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ዕለት ሁሌም ታስበዋለች። በተለይም የክርስቶስ ሥጋና ደም በሚፈተትበት ጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ የጌታን መከራ ታስበዋለች። ሥጋዉና ደ…
❤3
8 Apr 2026, 18:17 UTC696 views2 reactionsread 8 August 2026 ሰሙነ ሕማማት ሐሙስ
💧ይህ ዕለት ቅድመ ዓለም ለፍጥረታት ሁሉ ምግበ ሥጋን የፈጠረ ጌታ ለሰዉ ልጆች ምግበ ነፍስን የሠራበት፣ ራሱን ማዕድ አድርጎ ብሉኝ ትድናላችሁ ያለበት እና ይህንን ምግብ ለመቀበል ቅድሚያ መደረግ ያለበት ሥርዓተ ጸሎትን ያስተማረበት ዕለት ነዉ። ማቴ 26፥36
በዚህ ዕለት ጌታችን ካደረጋቸዉ ሥራዎች አንጻር ለቀኑ የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥቷል፦
፩. ጸሎተ ሐሙስ
📘 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ መከራና ፈተና በገጠመን ጊዜ ተግተን እንድንጸልይ ለማስተማር፣ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተዉ እስኪይዙት ድረስ በመጸለዩ፣ እንዲሁም ኅብስቱን ለመባረክ ስለጸለየ ለሐዋርያትም ሥርዓተ ጸሎትን ስላስተማራቸዉ ዕለቱ ጸሎተ ሐሙስ ተብሎ ይጠራል። ( ማቴ ፳፮፥፴…
👍2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @God2929. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.