10 Aug 2026, 16:34 UTC33 views4 reactionsread 12 August 2026 #ለድህነት_አፍቃሪዎች_በሙሉ
ገንዘብ ደስታን እገዛም ብላችሁ አትሸወዱ
ገንዘብ 5ቱን ይገዛል
1. እንደፈለጉ የመኖር ነጻነትን
ጠዋት በዝናብ፣ ከሰአት በጸሐይ
መደብደብ የሚቀርልህን ገንዘብ ካለህ ነው።
2. ከፈጣሪ በታች ዋስህ ነው
ብትታሰር ያስፈታሃል፣ ብትታመም ያሳክምሃል።
3. የእድል በርህን ይከፍትልሃል
አመድ ለአመድ አትንከራተትም። ቀጥ ብለህ
ሸራተንና ሂልተን ትገባለህ።
4. የአእምሮ ሰላም ይሰጥሃል
ኪራይ ደረሰ ብለህ እንቅልፍ አታጣም።
ታክሲ ተወደደ ብለህ አታለቃቅስም።
5. ለወገንህ ደራሽ ያደርግሃል
ማገዝ ያለብህን ታግዛለህ እንጂ ከንፈርህን መጥጠህ
ብቻ አታልፈውም።
👍3👏1
7 Aug 2026, 06:34 UTC38 views1 reactionsread 12 August 2026 ደፋርና የተግባር ሰው መሆን!
በጣም የሚያስፈሩህ ነገሮች ከብዙ ነገር ያስቀሩሀል፤ እንደ ንፋስ ሽው ብሎ ለሚያልፈው ዘመንህ እስከመቼ በፍርሀት ትኖራለህ? ምንም ነገር እስክትጀምረው ድረስ ነው ልብህ የሚያመነታው።
መሳሳት የማይፈልግ ሰው ጥጉን ይዞ ይቀመጥ፤ ስኬትና ደስታ ያለው ግን ከፍርሀትህ ጀርባ ነው። ቆራጥ መሆን ምርጫ ነው እንጂ ዕድል አይደለም! ያመንክበትን ለማድረግ፣ የምትፈልገውን ሰው ለመሆን ደፋርና የተግባር ሰው መሆን አለብህ!
👍1
4 Aug 2026, 16:09 UTC45 views1 reactionsread 12 August 2026 "ማህበረሰቡ የተወለድክበትን የመጀመሪያውንና እውነተኛውን ማንነትህን ይወስድብሃል፤ በእሱ ምትክ ደግሞ ሌላ ሰው ሠራሽ ማንነት ይሰጥሃል።
ስም ይሰጥሃል፣ ሃይማኖት ይሰጥሃል፣ የማህበራዊ ደረጃ ይሰጥሃል... ከዚያም ያንተ እውነተኛ ማንነት በነዚህ ተደብቆ ይረሳል። አንተም በሰዎች ፊት የምትለብሰውን ጭንብል እውነተኛው ማንነቴ ነው ብለህ ማመን ትጀምራለህ።
በእውነተኛው ማንነትህና በለበስከው ጭንብል መካከል ትልቅ ክፍተት ይፈጠራል። የጭንቀትህ፣ የብቸኝነትህና የውስጥ መታወክህ ምስጢር ይሄው ነው!
የለበስከውን ጭንብል አውልቀህ ስትጥልና ወደ ገዛ እውነተኛ ተፈጥሮህ ስትመለስ ብቻ ነው ፍጹም ሰላምና ደስታ የሚሰማህ።"
👍1
3 Aug 2026, 03:51 UTC64 views2 reactionsread 12 August 2026 ሁሉም ነገር አያልፍም
👍2
1 Aug 2026, 05:56 UTC74 views3 reactionsread 12 August 2026 የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት
በህይወት መኖር በራሱ ትልቅ ፍርሃት ነው። ትልቁ ፍርሃት ሞት አይደለም፤ በሕይወት የመኖርን አደጋ (risk) መጋፈጥ እንጂ፡፡ የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት እራሱን የመሆን ፍርሃት ነው።
ከልጅነታችን ጀምረን የተማርነው የሌሎች ሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት መኖርን ነው። ተቀባይነት ማጣትን እና በሌሎች አይን በቂ ሆኖ አለመታየትን አምርረን ስለምንጠላ፣ በሌሎች ሰዎች አመለካከት ታስረን መኖር እጣ ፈንታችን ሆኗል፡፡
👍2❤1
30 Jul 2026, 04:23 UTC82 views3 reactionsread 12 August 2026 የሰው ልጅ በህይወት ለመኖር የሚያስፈልገው ምግብ፣ ውሃና መጠለያ ናቸው። ስንፈጠር የነበረው እውነታ ይህ ነው፤ እነዚህን መሰረታዊ ነገሮችም በነፃ ያገኝ ነበር። በዃላ ሰለጠንኩ ዘመንኩ ብሎ በቡድን በመንጋ ማሰብ ሲጀምር በንጉስና ፖለቲከኞች መተዳደር ጀመረ ..... ከዛ ምግብ፣ ውሃና መጠለያ ከፖለቲከኞቹ እየለመነ መኖር ቀጠለ።
❤1👍1🔥1
28 Jun 2026, 17:36 UTC137 views3 reactionsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍3
8 Mar 2026, 13:35 UTC314 views2 reactionsread 12 August 2026 ሀብታም ነኝ ብለህ የምታስበው በባንክ ሂሳብህ ባለው የገንዘብ መጠን ከሆነ ተሳስተሀል። ትክክለኛው ጥያቄ፡- "ዛሬ ስራ መስራት ብታቆም፣ ያጠራቀምከው ገንዘብ ወይም ንብረት ለስንት ጊዜ በህይወት ያቆይሀል?" የሚለው ነው።
"ሀብታም ሰው ማለት ስራ ባይሰራም እንኳ ንብረቱ የኑሮ ወጪውን የሚሸፍንለት ሰው ነው። ድሃ ማለት ግን ስራው ሲቆም ህይወቱ የሚቆምበት ሰው ነው።
📕ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ
📚 @Goldanmind
👍2
4 Mar 2026, 18:07 UTC278 viewsread 12 August 2026 Video
Video, posted without a caption
25 Feb 2026, 10:12 UTC193 views1 reactionsread 12 August 2026 #ተገትረህ_አትቅር
ትናንት፦
ከገንዘብ ፍቅር ይበልጣል ያሉህ
ዛሬ፦
ገንዘብ ስሌለህ ይንቁሃል!
ትናንት፦
ጠንክረህ ተማር ያሉህ
ዛሬ፦
መማርህ የት አደረሰህ ይሉሃል!
ትናንት፦
በጉብዝናህ ያደነቁህ!
ዛሬ፦
ጎበዝ ሰርቶ የሚለወጥ ነው ይሉሃል!
ዛሬህን ምሰል! ባለፈ ሀሳብ ተገትረህ አትቅር!
@Goldanmind
👍1
18 Feb 2026, 10:11 UTC163 views2 reactionsread 12 August 2026 የለውጥህ ቁልፍ በእጅህ ነው!
"አንዳንድ ጊዜ እንድትጠነክር እንድትጀምር ወይም እንድትለወጥ የምትጠብቀው ሰው... ያው ራስህ ነህ!"
ብዙዎቻችን ሕይወታችን እንዲቀየር ሌላ ሰው ወይም ምቹ ሁኔታ እስኪመጣ እንጠብቃለን።
ነገር ግን እውነታው ማንም መጥቶ ህልምህን አያሳካልህም። ወደፊት ለመንሸራተት ራስህን ከጀርባ መግፋት ያለብህ አንተ ራስህ ነህ።
ልብ በል
አመለካከት፦ ለገጠመህ ፈተና የምትሰጠው ትርጉም ማንነትህን ይወስነዋል።
ራስን መግፋት፦ 'ተአምር' አትጠብቅ፤ ተአምሩ አንተ ራስህ ነህ።
እርምጃ፦ ስለተፈጠረው ነገር ከማውራት ይልቅ ምን ማድረግ እንዳለብህ አስብና ተንቀሳቀስ።
ያስታውሱ፡ ማዕበሉን ማስቆም ባትችልም ጀልባህን መንዳት ግን ትችላለህ። ⛵️
ለመሆ…
❤2
5 Feb 2026, 09:18 UTC152 views3 reactionsread 12 August 2026 "መኖር የሚጀመረው አለመኖርን ከመፍራት ነው!"
በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው! ረሀብ የለም። በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው ብርድ የለም። ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም ምቾት፣ መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሀ ውስጥ መንሳፈፍ ነው። ግን ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድክበት ቅፅበት ይለወጣል።
መተንፈስ ግድ ይላል! ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን ለመኖር፤ አለበለዚያ መኖር የለም! መታፈን፣ በረሀብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሀታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ። በእናታችን ማህፀን ውስጥ የምናውቀው መኖርን ብቻ ነው። መወለድን ግን አለመኖርን አመላካች ነው!
.......
አለመኖር
በዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ
❤3
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Goldanmind. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.