10 Jul 2026, 21:03 UTC451 views5 reactionsread 7 August 2026 ለፈተና ትቀመጣላችሁ ተብሏል!
በቀድሞው ዲፕሎማ ወይም ከ12+2 ወይም ከ10+3 የተመረቁና ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ ኖሯቸው ነገር ግን የደረጃ ስድስት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ ተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የሚያስችል መመሪያ ሊዘጋጅ ነው፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫና የአቻ ግመታ መመሪያ ማሻሻያ ላይ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
እንዲሁም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሁለተኛ…
❤3👏2
8 Jul 2026, 08:04 UTC500 viewsread 7 August 2026 በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% መደረጉ ተገለጠ
ከ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤት ኪራይ ገበያ ላይ የሚታየውን ያልተገባ አሰራር በዘላቂነት ለመግታትና የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል ያለመ አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ዓመታዊ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ብቻ ሆኖ እንዲገደብ መወሰኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
* ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ የአከራይና ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የቤቶች አስተዳደር ፅሕፈት ቤቶች በይፋ መተ…
1 Jul 2026, 20:27 UTC592 viewsread 7 August 2026 Photo
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሊዮን በረራ ጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንይ ሊዮን ከተማ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት ማስጀመሩን ይፋ አድርጓል።
ይህም ለአየር መንገዱ በፈረንሳይ 3ኛ፣ በአውሮፓ 23ኛ እንዲሁም የዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ቁጥር 146 የሚያደርሰው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በወቅቱ እንዳሉት፤ የበረራ አገልግሎቱ መጀመር አየር መንገዱ አፍሪካን ከዓለም ጋር የማገናኘት ጉዞው ተጨማሪ ስኬት ነው።
ወደ ሊዮን የጀመረው በረራ ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ተጨማሪ ዕድል የሚፈጥር ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡
መንገደኞችን ከማመላለስ ባሻገር የሀገራት ሁለንተናዊ ትስስሮች እንዲጠናከሩ አቅም መፍ…
1 Jul 2026, 20:25 UTC499 views1 reactionsread 7 August 2026 ዜና፦ ቮዳኮም በሳፋሪኮም ውስጥ ያለውን የአብላጫ ድርሻ ግዥ ማጠናቀቁን ገለጸ፤ በኢትዮጵያ ያለውን የማደግ ፍላጎትም ጠቅሷል
በደቡብ አፍሪካ መሥሪያ ቤቱን ያደረገው ቮዳኮም ግሩፕ በሳፋሪኮም ኃ/የተ/የግል ማኅበር ውስጥ የነበረውን ድርሻ በ20% በማሳደግ፣ ጠቅላላ የባለቤትነት ድርሻውን ወደ 55% አካባቢ ማድረሱንና በኬንያ እና በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሰውን የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ የአብላጫ ባለቤትነት መብት መረከቡን አስታውቋል።
ኩባንያው ሰኔ 23 ቀን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰኔ 19 ቀን የኬንያ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረውን ዕገዳ ማንሳቱንና የቀሩት ቅድመ ሁኔታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ተከትሎ ግብይቱ በይፋ መጠናቀቁን ገልጿል።
እ…
❤1
1 Jul 2026, 20:24 UTC352 viewsread 7 August 2026 የዱባይ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመግባት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገለጠ
በአቡ ዳቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደገለጸው፣ የዱባይ ንግድ ምክር ቤት አባል የሆኑ ኩባንያዎች፣ ሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ የወሰነችውን ውሳኔ ተከትሎ “ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ እና የባንክ ዘርፍ ለመግባት ዝግጅት” ጀምረዋል።
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር፣ ከዱባይ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሐመድ አሊ ራሺድ ሉታህ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። ኤምባሲው እንደገለጸው፣ ውይይቱ ከዱባይ የሚመጣውን ኢንቨስትመንት ለማመቻቸት ቀደም ሲል ከተደረጉ ስብሰባዎች ቀጣይነት ያለው ሲ…
1 Jul 2026, 11:19 UTC323 viewsread 7 August 2026 Photo
ስደተኞችን የተቃወመው የደቡብ አፍሪካውያን ሠላማዊ የተባለሠልፍ በተለያዩ አካባቢዎች እየተጀመረ ነው።
የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ከማለዳው ጀምሮ ስደተኞችን በተቃወመው የደቡብ አፍሪካውያን አስፈሪ የተቃውሞ ሠልፍ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሽፋኖችን በመስጠት ተጠምደዋል።
በተለይም በጠዋቱ የዘገባ ሠዓታቸውየደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅቶ የተቃውሞ ሠልፉ ወደመጥፎ ክስተት እንዳይቀየር እየሰራ ስለመሆኑ በተለያዩ ከተማዎች ያሉ ሁኔታዎችን በማሳየት በስፋት ሲዘግቡተስተውለዋል።
ከደቂቃዎች በፊት እየተሰሙ ያሉ መረጃዎች የማርች ኤንድ ማርች ንቅናቄ የሚመራው የተቃውሞ ሠልፍ በደርባን ኢተክዊኒ እና ምስራቅ ኬፕታውን አካባቢ ተጀምሯል።
አፍሪካን ሬኔሳንስ ቴሌቪ…
1 Jul 2026, 07:09 UTC371 views2 reactionsread 7 August 2026 ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የ‘ጄሲአይ’ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱ ተነገረ
ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ከጆይንት ኮሚሽን ኢንተርናሽናል (ጄሲአይ) የላቀ የሕክምና አገልግሎት ጥራትና የሕሙማን ደህንነት ማረጋገጫ ዕውቅና በማግኘት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሆስፒታል ሆኗል። ይህ በሀገሪቱ የጤናው ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ ተብሎ የተጠቀሰው ስኬት የተሰማው ሆስፒታሉ የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት ነው።
የጄሲአይ ዕውቅና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና ተቋማት የጥራት ቁጥጥርና የሕሙማን ደህንነት ጥበቃ ረገድ እጅግ ከፍተኛውና ተደራሽ ለመሆን አስቸጋሪው መመዘኛ እንደሆነ ይታወቃል።
አንድ የሕክምና ተቋም ይህንን ዕውቅና ለማ…
❤1👏1
1 Jul 2026, 07:09 UTC500 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
29 May 2026, 07:04 UTC694 views2 reactionsread 7 August 2026 Photo
ማዕከላዊ ባንኩ ለአራተኛው ሩብ ዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ሊያቀርብ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ2018 በጀት ዓመት የመጨረሻ ሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጨረታ መርሃ-ግብርን ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ለዚሁ ተግባር 200 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መመደቡን አስታውቋል። ይህ የተመደበው በጀት በሙሉ በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን ባንኩ ገልጿል።
የማዕከላዊ ባንኩ መግለጫ እንዳመለከተው፣ ይህ አዲስ የአቅርቦት ስትራቴጂ በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለማረጋጋት ታሳቢ ያደረገ ነው።
ባንኩ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ይፋ ካደረገው 520 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦት አንጻር፣ በሦስተኛው ሩብ ዓመት የነበረው አሰራር በእያን…
😁2
11 May 2026, 09:30 UTC885 views1 reactionsread 7 August 2026 በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በ500,000 እና 400,000 ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ።
መንሱር ጀማል የተባለው ተከሳሽ ግን አቃቢ ህግ መቃወሚያ ስላቀረበበት ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ በ1.9 ቢሊዮን ብር የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ታዋቂ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች፣ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ፈቅዷል።
ባለፈው ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከ5 ተከሳሽ መንሱር ጀማል ውጭ ባሉ ተጠርጣሪዎች ከሀገር እንዳይወጡ እና ከፍ ያለ ዋስትና…
❤1
9 May 2026, 19:07 UTC784 viewsread 7 August 2026 መቐለ : ዛሬ ጠዋት ምን ተፈጠረ?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ ጧት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መቐለ ከበረረ በኋላ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሳያርፍ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ።
አውሮፕላኑ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ማረፍ ያልቻለው፣ ከአውሮፕላን ማረፊያው የኮሚንኬሽን መሳሪያ ብልሽት ጋር በተያያዘ መኾኑን የአየር መንገዱ ሃላፊዎች እንደነገሩት ጠቅሶ የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።
ኾኖም ከሰዓታት በኋላ የኮምንኬሽን መሳሪያው ብልሽት በመስተካከሉ አውሮፕላኑ ወደ መቐለ መጓዙን እንደተረዳ ምንጩ ጠቅሷል።
9 May 2026, 14:33 UTC754 viewsread 7 August 2026 Photo
በታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሣ እና በሻኩራ ፕሮዳክሽን ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የንብረት እና የባንክ ሂሳብ እገዳ መጣሉ ተሰማ።
ይህ እርምጃ የተወሰደው "ኢትዮጵያ" በተሰኘው የባህል ማስተዋወቅ ፕሮጀክት ላይ በተሳተፉ 37 አርቲስቶች የቀረበባቸውን የ30.8 ሚሊዮን ብር ክስ ተከትሎ ሲሆን፣ አርቲስቶቹ በቻይና እና በሩሲያ ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት 11 የባህል ትርኢቶችን ቢያቀርቡም የተስማሙበት ክፍያ እና የልምምድ አበል እንዳልተከፈላቸው ገልጸዋል።
አቀናባሪ ካሙዙ ካሣ በበኩላቸው ክፍያዎችን በስምምነቱ መሠረት እየፈጸሙ መሆናቸውን በመጥቀስ ክሱን ቢያስተባብሉም፣ ፍርድ ቤቱ ግን ጉዳዩ በህግ ታይቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በአቀናባሪው ስም ያሉ ማ…
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @Hulaadiss. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.