21 Aug 2026, 05:23 UTC48 viewsread 22 August 2026 Forwarded from @EOTCmahlet
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አመ ፲፮ ለነሐሴ በዓለ ኪዳነምህረት ስርዓተ ዋዜማ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ዋዜማ በ፩
ሃሌ ሉያ
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ወተወልደ እምኔኪ ቃለ ጽድቁ ለአብ፤ማርያምሰ ተሐቱ ዉስተ ከርሡ ለአዳም፤ከመ ባሕርይ ፀዓዳ፤ ፆረቶ እግዝእቱ ለአዳም፤
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ምልጣን፦
ማርያምሰ ተሐቱ፤ ዉስተ ከርሡ ለአዳም፤ከመ ባሕርይ ፀዓዳ፤ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም፤ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም።
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም/፪/
ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ለእግዚአብሔር በምላዕ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኀርያ ሰአሊ ለነ ማርያም
…
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
21 Aug 2026, 05:23 UTC49 views0 reactionsread 22 August 2026 Forwarded from @EOTCmahlet
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ሥርዓተ ማኅሌት ዘነሐሴ ፲፮ በዓለ ኪዳነምህረት
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ …
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
21 Aug 2026, 04:44 UTC59 viewsread 22 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
21 Aug 2026, 04:44 UTC59 viewsread 22 August 2026 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፲፭
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የመኰንን ርባኖስ ልጅ ቅድስት ክርስጢና በሰማዕትነት ሞተች ።
አባቷ ጣዖታትን የሚያመልክ ነው ። እርሷም አባቷ እንደ አስተማራት ታጥናቸው ነበር ። በአንዲት ዕለትም አስባ ተመራመረች በልቧም እግዚአብሔርን መፍራት አደረ ተነሥታም ፊቷን ወደ ምሥራቅ መልሳ ቆመች የምትጓዝበትንም የሕይወት መንገድ ይመራት ዘንድ ጸለየች መንፈስ ቅዱስም አንድነቱንና ሦስትነቱን ገለጠላት ።
አባቷም በመጣ ጊዜ ልጄ እንዴት አለሽ አላት በክብር ባለቤት በክርስቶስ ሕይወት አለሁ አለችው ። አባቷም ሰምቶ ደነገጠ ልብሽን ምን ለወጠው አላት እርሷም ከሰማይ አምላክ ተማረኩ …
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
21 Aug 2026, 04:44 UTC58 viewsread 22 August 2026 ያም ሕፃን አደገ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ
መነኰሰ ። አርባ ዓመትም ሲፈጸም ሦስት ቀኖች ያህል ታማ በሰላም አረፈች ደወልንም ደውለው መነኰሳቱ ሁሉ ተሰበሰቡ ሊገንዙም ገብተው ልብሶቿን በገለጡ ጊዜ እርሷ ሴት እንደ ሆነች አግኝተዋት ደነገጡ መሪር እንባንም አለቀሱ አበ ምኔቱም በጣም ጊዜ ያለ በደሏ ከባድ ንስሐ ቀኖና ስለሰጣትና በእርሷ ላይ ስለ አደረገው ተግሣጽ መሪር ዕንባን አለቀሰ ።
ከዚህም በኋላ መልእክተኞችን ልኮ የዚያችን የሐሰተኛ ልጅ
አባቷን አስመጥቶ እንባመሪና ሴት እንደሆነች ነገረው ። ከዚህም በኋላ በድኗን ተሸክመው ይቅር ይበለን የሚል ቃል ከበድኗ እስከ ሰሙ ድረስ አቤቱ ክርስቶስ ማረን እያሉ ጸለዩ ከዚያም በኋላ በዝማሬና በማኅሌት ከ…
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
20 Aug 2026, 04:27 UTC99 viewsread 22 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
20 Aug 2026, 04:27 UTC97 viewsread 22 August 2026 ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት
ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል ።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን ።
✝ http:/…
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
20 Aug 2026, 04:27 UTC75 viewsread 22 August 2026 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፲፬
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ አራት በዚች ቀን የአባ ስምዖንና የወዳጁ የዮሐንስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ ።
እሊህ ቅዱሳንም በአማኒው ዮስጦንስ ዘመን መንግሥት የነበሩ ናቸው እሊህም ወንድሞች የከበሩ ክርስቲያን ናቸው።
ከዚህ በኋላ ለከበረ መስቀል በዓል ቅዱሳት መካናትን ሊሳለሙ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ ሥራቸውንም አከናውነው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ ኢያሪኮ ቀረቡ ።
ዮሐንስም በዮርዳኖስ በረሀ ያለውን የመነኰሳቱን ገዳም አይቶ ወንድሙ ስምፆንን ወንድሜ ሆይ ለእሊህ ገዳማት እኮ የእግዚአብሔር መላእክት ይኖራሉ አለው ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋራ ከሆን አወን ልናያቸው እንችላ…
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
20 Aug 2026, 04:27 UTC66 viewsread 22 August 2026 አስተውል የከበሩ ነቢያት ድኆች ችግረኞችም እንደነበሩ ሐዋርያትም እንደርሳቸው ችግረኞች እንደነበሩ ። ጌታችንም ድኆችን ወንድሞቼ ይላቸው እንደነበረ ። ሰይጣን ግን የጓደኛውን ምክር እንዲቀበል ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ለውጦ ነፍሱን እስከማጥፋት ድረስ አነሣሣው ቀሰቀሰው እንጂ ።
ከዚህም በኋላ ወደ ፈለስኪኖስ ሒዶ በአንተ ዘንድ እንዳገለግል ተቀበለኝ አለው ። ፈለስኪኖስም እንዲህ ብሎ መለሰለት በሃይማኖቴ የማታምን አንተ ልታገለግለኝ አይገባም ከቤተ ሰቦቼም ጋራ የማትተባበር ልቀበልህ አይገባኝም ። ሁለተኛም ይህ ጐስቋላ ወዳንተ ተቀበለኝ እኔም ወደ ሃይማኖትህ እገባለሁ ያዘዝከኝንም ሁሉ አደርጋለሁ አለው ።
አይሁዳዊው ባ…
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
19 Aug 2026, 11:15 UTC59 views2 reactionsread 22 August 2026 Forwarded from @Fikureegzi4
በዓለ ደብረ ታቦር
" ነቢዩ ዳዊት ከተራሮች ከፍ ከፍ ባደረጋት
በኪሩቤል አምሳል በመሰላት
በሩቅ ሰማይ ጥግ በደብረ ታቦር
የቃል ኪዳን ራስ ክርስቶስ በተገለጠባት ጊዜ
እነሆ ጴጥሮስ በመካከሏ
ማደሪያ ይሠራ ዘንድ ተመኘ "
ነግሥ ዘደብረ ታቦር
በዓለ ደብረ ታቦር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት የጌታ በዓላት መካከል አንዱ ነው ምን አድርጎበታል ቢሉ ብርሃነ መለኮቱን ለሐዋርያት ገልጾበታል ታቦር የተራራ ስም ነው ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ ብዙውን ጊዜ የሚያስተምረው ተአምራት የሚያደርገው በተራራ ላይ ነበር በዚህም ዕለት ዘጠኙን ከእግሩ ደብር ትቶ ሶስቱ ጴጥሮስን ዮሐንሰንና ያዕቆብን አስከትሎ ከርእሰ ደብር ወ…
❤2
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
19 Aug 2026, 11:13 UTC50 viewsread 22 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
19 Aug 2026, 11:13 UTC55 viewsread 22 August 2026 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፲፫
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው ።
በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው ። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ ።
ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገ…
Signed የጅ/ር/አ/ወ/ደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ ዓምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @JMAHSTB. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.