8 Aug 2026, 03:47 UTC7 views1 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @poem_Hiwe
ክፍል ሰላሳ አንድ
ፍቅር ወይንስ እምነት
#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
“እኔ…እ”
አለችኝ አብሱ።
ድምጿ እየተንቀጠቀጠ...
እኔ ግን ምንም አልተናገርኩም... ልቤ ሌላ ነገር አላሰበም ከአፏ ጥሩ ቃል እየጠበቅሁ በዝምታ ተመለከትኳት።
“እኔ… አንተን ማጣት አልፈልግም…”
በቀስታ አለችኝ
“የቱ ጓደኛ አለኝ? ወንድምስ አለኝ? ማን አለኝ ከአንተ በቀር?”
(ዓይኖቿ እንባ ሞልተው ወደ እኔ ተመለከቱ)
“ብቸኛ ነኝ አቤኒ… አንተ ግን… እኔ ሳላውቅ እንኳን ከጎኔ ነበርክ።”
እኔ ለጥቂት ሰከንዶች ተመልክቻት...ከዛን
“ምን እያልሽኝ ነው?”
አልኳት በተሰበረ ድምፅ።
እሷ ግን በእንባ እያየችኝ—
“ታስፈልገኛለህ… እባክህ አትጥላኝ። ተረዳኝ…”
አለችኝ።
ረጋ…
❤1
Signed 🙏፩፫❣ 😂Mÿ Ĺĩ£ę😭
8 Aug 2026, 03:05 UTC13 views1 reactionsread 8 August 2026 እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።
— ወደ ዕብራውያን 11:1
Amharic Bible Bot
🥰1
Signed Amharic Bible Bot
7 Aug 2026, 17:09 UTC29 viewsread 8 August 2026 ብዙ ያስታመመ ብዙ አያለቅስም🙌
ምንማለት ነው fam😊
7 Aug 2026, 03:05 UTC44 viewsread 8 August 2026 እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው።
— መዝሙረ ዳዊት 9:9-10
Amharic Bible Bot
Signed Amharic Bible Bot
6 Aug 2026, 03:04 UTC58 views1 reactionsread 8 August 2026 ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
— ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13
Amharic Bible Bot
🔥1
Signed Amharic Bible Bot
5 Aug 2026, 10:38 UTC45 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @poem_HiwePhoto
ምረጪ🥰☹️
🔥2
Signed 🙏፩፫❣ 😂Mÿ Ĺĩ£ę😭
5 Aug 2026, 03:05 UTC75 viewsread 8 August 2026 አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።
— መዝሙረ ዳዊት 25:3
Amharic Bible Bot
Signed Amharic Bible Bot
4 Aug 2026, 03:05 UTC86 viewsread 8 August 2026 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል።
— 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:15-16
Amharic Bible Bot
Signed Amharic Bible Bot
3 Aug 2026, 19:21 UTC98 views0 reactionsread 8 August 2026 ንገሪኝ
አሁን እንደኔ ያለ
አለ!?
ክንፍ ሳይኖረው ለሰማይ
ስንጥብ ሳይኖረው ለባህር
ልብ ሳይኖረው ለምድር
እንዲሁ የተፈጠረ !?
በጨካኝ ዓለም ውስጥ
ጥርሱ ሳይሾልለት
ጥፍሩ ሳይረዝምለት
ቀንድ ሳይቆምለት፤
እንዲሁ
እያለቀስክ
ተንፍስ የተባለ!?
አለ !?
ንገሪኝ
ሰምተሻል!?
ሰው
ጭንብሉን ጥሎ
ሰው
ሲኾን አይተሻል!?
ሰው
ልቡን ቢያራራ
ሰው
ትጥቁን ቢፈታ
ሰው
ፍፁም ይቅር ቢል ይኖር ይመስልሻል!?
ይቻላል !?
መርዝ የሌለው ዕባብ
ጥርስ የሌለው አዞ
እሾህ የሌለው ጃርት በደስታ ይኖራል!?
እሾህ
ቀንድና
መርዝ
የፈጠረ ጌታ ጦርነት ይጠላል!?
ይቻላል!?
ሰው
ላይሞት ይኖራል !?
ቻው ...
ባይኖረው ፍቅር
ሰው ችሎ ያፈቅራል!?
እንጃ ፤
እኔ ..…
3 Aug 2026, 03:06 UTC87 viewsread 8 August 2026 እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
— 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:7
Amharic Bible Bot
Signed Amharic Bible Bot
2 Aug 2026, 06:20 UTC86 views3 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @poem_Hiwe
#ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ እውነተኛ ታሪክ ነው...ለግለሰቧ ደህንነት ስል ስሞችን ለውጬዋለሁ።
-ከገጠመኝ ውስጥ ....
*ትሁትና ፍቅረኞችዋ💔
ነገሩ የሚጀምረው የዛሬ 5 አመት ይሆነዋል በክረምቱ ሰበብ እረፍት ስለሆነ የሆነ ገዳም ለሱባኤ በሄድኩበት ጊዜ አንዲት መልከ መልካም አይኖችዋ የሚያማምሩ ስትታይ ውብ የሆነች ነገርግን አለባበሷ ጉስቅል ያለ ፊቷ የገረጣ ሰውነቷ ክስት ብሎ ያለእድሜዋ ስትታይ ትልቅ ትመስላለች ግን አተኩሮ ላያት ስትታይ አፍላ ወጣት ናት...23 አመቷ ነው
በሁለት ሳምንት ተግባባን እና በወሬ ወሬ ስለ ፍቅር ታሪኳ ጠየቅኳት ውስጧ ባይደሰትም ቀስ በቀስ.... ነገረችኝ
ትህትና እውነትም እንደ ስሟ እሷም ትሁት ናት። …
🥰2🔥1
Signed 🙏፩፫❣ 😂Mÿ Ĺĩ£ę😭
2 Aug 2026, 04:32 UTC255 views1 reactionsread 8 August 2026 እመክርሻለው ውዷ እህቴ
የፍቅር ጥያቄ ሲቀርብልሽ "ቆይ ላስብበት" የምትይበትን ሳይሆን "ቆይ ልፀልይበት" የማለትን ልብ ይስጥሽ..... ለምን መሰለሽ እንደዝ ያልኩት 👉አስበሽ ከመለስሽለት መልስሽ በአንች ልክ ነው የሚሆነው 👉ፀልየሽ ከመለስሽለት ከፈጣርሽ ጋር ተመካክረሽ ነው የምትመልሽው ያን ጊዜ ከሕይወት ባለቤት ጋር ስለተመካከርሽ የነገ ሕይወትሽ የተስተካከለ ነው የሚሆነው......
ምን ታስቢያለሽ የምትፈልጊውን ወይስ የሚያስፈልግሽን????
መልካም ዕለተ ሰንበት🥰
https://t.me/Kenako_12
❤1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Kenako_12. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.