18 Sept 2026, 10:59 UTC82 views0 reactionsread 3 October 2026 ሙ…ሐ…መ…ድ
ባፍላነት ወራቶች
አንደሰሩት ገድል ዝናን የሚዘራ፣
ጧት እንደሚበሰር
እንደ ማለዳ እድል ህላዌን ሚያበራ።
ለነግ ተነግ በስቲ እንዳይላላ ትልቁ፣
ልብን እያደሰ የሚያኖር ስንቁ፣
ሲያነቡ ሚያብስ ሚደግፍ ሲወድቁ።
ሲሰበሩ ጠጋኝ ሲከፉ የሚያስደሳ፣
ሲያዝኑም የሚያባብል
ሲጣ፝ሉ ሚያነሳ፣
ሲረሱ ሚያወሳ።
ሲራቡ ’ሚቀልብ እንደ’ናት እንጎቻ፣
ካ’ፋፉ ሚታደግ ከክስመት ዳርቻ።
ሲያነቡ የሚያስቅ ሚያድን ሲታመሙ፣
በማዓዛው ሚያጌጥ ፅጌረዳ ስሙ።
ሙ…ሐ…መ…ድ
በተጠራ ቁጥር በቀልብ ላይ ሰርጎ፣
ሩሕ የተጠማ’ለት የሚጠ፝ጣ እንደርጎ።
ሙ …ሐ… መ… ድ
ሙሐመድ የኔታ ፍቅር ኹሉ ድካም
ፍቅር ኹሉ ቁስል፣
ኣንድም አልተገኘም አልታየም አይታይ
ፍቅርሁን ሚመስል።
…
Signed Reyan Abudi
13 Sept 2026, 10:41 UTC103 viewsread 3 October 2026 Video
ስለ ዘይዲያ መዝሀብ የነገርኳችሁ የተጋነነ ወይንም ውሸት የመሰላችሁ ይሄንን የሸይኻችንን ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን ንግግር አዳምጡልኝ።
እንደውም እኔ ከገለፅኩትም በበለጠ የምንጠቀመው መሷድር ሁሉ አንድ ነው ብለው አስቀምጠውታል።
በውሸት የሆነን ነገር እንዲትረዱት አልፈልግም።
የምፈልገው ያለ አግባብ በውሸት ተመስርታችሁ ሙስሊሞ ወገኖችን ከማክፈርና የኡማው ፊትና ከመሆን እንዲትጠበቁ ብቻ ነው!
ይህን ያክል በመስደርና በመዝሀብ ደረጃ እንኳ አንድ የሆንን ህዝቦች መጁሳ ናቸው የሚል ቅጥፈት አላህም ዘንድ የሚያስጠይቅ ትልቅ ወንጀል ነው።
@Reyan_islamic_post
Signed Reyan Abudi
11 Sept 2026, 20:55 UTC99 views2 reactionsread 3 October 2026 አሁን ስለ ሁቲዎች አቂዳ እና ስለሚታሙባቸው ነገሮች እናወራለን🇾🇪
1ኛ የሁቲዎች ሀይማኖት ኢስላም ነው። አይደሉም የሚሉ አሳላፊዎች እንዳሉ ቢታወቅም በሁሉም የኢስላምና የኢማን መሰረቶች የሚያምኑ የማያወላውሉ ሙስሊሞች ናቸው።
2ኛ መዝሀባቸው የዘይዲያ መዝሀብ ነው። የዘይዲያ መዝሀብ በሱኒ እና በሺአ መካከል ያለ መዝሀብ ነው ይሉታል። ብዙዎችም የሱኒ አምስተኛው መዝሀብ ነው ይሉታል። ያ ማለት ሀነፊያ ፤ ማሊኪያ ፤ ሻፊኢያና ሀንበሊያ መዝሀብ ጋር አንዱ የሱኒ መዝሀብ እንደማለት ነው።
የመዝሀባቸው መስራች የነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የልጅ ልጅ ልጅ ፤ የአሊ እና የፋጢመቱ የልጅ ልጅ ፤ የኢማም ሁሰይን ልጅ የሆኑት ዘይኑል አቢዲን ልጅ የሆኑት ዘይድ ቢን …
❤1🤣1
Signed Reyan Abudi
11 Sept 2026, 20:54 UTC67 viewsread 3 October 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Reyan Abudi
8 Sept 2026, 20:31 UTC144 viewsread 3 October 2026 Photo
የደህንነት ካሜራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውሾችን ከአንድ ቤት ውጭ ተሰብስበው ቀረጸ። ልክ እኩለ ሌሊት ካለፈ በኋላ፣ የሰፈር የደህንነት ካሜራ ማንም ሊያብራራው የማይችለውን ነገር ቀረጸ። አንድ የጎዳና ውሻ ከመንገዱ መጨረሻ ላይ ካለ አሮጌ ቤት ውጭ ቆመ። ከዚያም ሌላ መጣ ። ከዚያም ሌላ በአንድ ሰዓት ውስጥ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ውሾች በቤቱ ፊት በጸጥታ ተቀምጠው ነበር። ፀሐይ ስትወጣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውሾች ነበሩ። ጎረቤቶች አንድ ሰው እየመገባቸው ለምግብ እንደሆነ ያስቡ ነበር፣ ነገር ግን ማንም ሰው ለቀናት ወደ ቤቱ አልገባም ወይም አልወጣም። የእንስሳት ቁጥጥር ወደ ቦታው ደረሰ፣ ትርምስ እየጠበቀ። በምትኩ፣ እያንዳንዱ ውሻ ተረጋግቶ የፊት በሩን እያየ ነበር።
…
Signed Reyan Abudi
6 Sept 2026, 05:07 UTC114 viewsread 3 October 2026 ለሙስሊሞች ትልቁ ጠላት የውጭ ወራሪዎች ወይንም ጥቃት አይደለም። የኢስላም ትልቁ ጠላት ፅንፈኝነት ነው። አክፋሪነት ! ከኔ ውጭ ትክክለኛ ሙስሊም የለም ማለት!
ፅንፈኝነት ወይንም ተክፊርነት በሙስሊሞች ያመጣውን ውድመት ማንም አላመጣውም!
የመጀመሪያውን ትልቁን የሙስሊሞች ፊትና የፈጠረው ተክፊርነት ነው።
ታላቁን ሶሀባና ኸሊፋ ኡስማንን ትክክለኛ ሙስሊም አይደለህም ሙብተዲእ ነህ ብለው ገደሏቸው። ሹፉ ከኡስማን በላይ እነርሱ ትክክለኛ ሙስሊም ሆነው አመፁባቸው። እና ያ ፈተና በኢስላም ታሪክ እስካሁንም ጠባሳውን ያላነሳውን የመከራ የመፈራረቅ ጥንስስ ጠንስሶ አለፈ።
ከዚያ በሗላ ወልዩሏህ አሊ ላይ ትክክለኛ ሙስሊም አይደለህም ብለው አመፁባቸው። አላህ ያሳያችሁ ከአ…
Signed Reyan Abudi
1 Sept 2026, 18:07 UTC128 viewsread 3 October 2026 ከመጅሙዕ ረሳዒል አሽሂድ ኢማም ሐሰን አልበና የተወሰደ
🔻 ሁለንተናዊው እስልምና
📍 ወንድሞች ሆይ! እኔ ከዚህ ሚንበር ላይ ሆኜ በሙሉ ግልጽነት፣ በጥራትና በጽናት እማውጀው፤ እስልምና ተቃዋሚዎቹና ከገዛ ልጆቹ መካከል ያሉ ጠላቶቹ ሊገድቡትና ሊያጥሩት ከሚፈልጉት ትርጉም ውጭ የሆነ ሰፊ መለኮታዊ መንገድ መሆኑን ነው። እስልምና እምነትና አምልኮ፣ ሀገርና ዜግነት፣ ይቅርባይነትና ጥንካሬ፣ ሥነ-ምግባርና ቁሳዊ ሕይወት፣ ባህልና ሕግ ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው በእስልምናው እምነት ምክንያት የሕዝቡን (የኡማውን) ጉዳይ ሁሉ ሊከታተልና ሊያስበው ይገባል፤ «የሙስሊሞችን ጉዳይ ያላሳሰበው ከእነሱ አይደለም» እንደተባለው።
📍 የቀደሙት ሰለፎቻችንም — የአላህ መልካም …
Signed Reyan Abudi
1 Sept 2026, 18:07 UTC89 viewsread 3 October 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Reyan Abudi
28 Aug 2026, 20:30 UTC129 viewsread 3 October 2026 ከሙፍቲ ኅልፈት በኋላ የተጋጠምኩት ደግሞ ከሌላ ጣጣ ጋር ነው፡፡ ለዝግጅቱ በሰጠሁት ሙሉ ትኩረትና በምኖርበት አካባቢ የአየር መለዋወጥ ምክንያት፣ ረፍት የሚፈልገውንና ነጻነት የማይለግሠውን የሳምባ ምች ሕመም ሸምቼ ነበር። “ሳልጨርሰው አልሞትም” እያልኩ በዚሁ ሕመም ውስጥ ለመጽሐፉ ዳርቻ ግብግብ አካሄጃለሁ። አልሐምዱሊላህ! በሒደት ሕመሜ ፈውስ፣ መጽሐፉም ፍጻሜ አግኝቷል፡፡
ከእርሳቸው ጋር በነበረህ ቆይታ አይረሴ የምትለውንገጠመኝ ብትነግረኝ?
•ተቀዳሚ ሙፍቲ ለበርካታ ሚዲያዎች ግለ ታሪካቸውን ስለሰጡ፣ ብዙ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ዘጋቢ ፊልሞች ስለተሠራላቸው፣ የመጽሐፍ ዝግጅቱ ከዚያ የተለየ እንደማይኾን በመገመት እምብዛም ትኩረት አልሰጡትም ነበር። ለመጀመር…
Signed Reyan Abudi
28 Aug 2026, 20:30 UTC98 viewsread 3 October 2026 “የሀገር መልክ” መጽሐፍ ደራሲ ጋር የተደረገ ቆይታ
By Ahmed Abdurehman- ዓ 15 ربيع الأول 1448AH 28-8-2026AD
ኸድር ታጁ ባለፉት ዓመታት ለግሉ ብቻ የተሠጠው በሚመስል የአጻጻፍ ሥልት ያለማቋረጥ የታሪክ መጽሐፍትን በማቅረብ ላይ የሚገኝ ጸሐፊ ነው፡፡ “ዓምደ ሀገር – ሸይኽ ዓሊ ጎንደር”፣ “ዳናዎቹ ቅጽ 1”፣ “ዳናዎቹ ቅጽ 2”፣ “ሸይኽ ሰይድ ኢብራሂም – የሸይኽ ጫሌ አንጸባራቂ ታሪክ”፣ “የበጌ ምድር አራጣ ሊቃውንት (ዑለማዎች)” እና “አግራሞታዊ ጉዞ” ከሥራዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ በተያዘው ዓመት ጥቅምት 9/2018 ከምድር ሕይወት የተለዩትን የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ በማጠናቀ…
Signed Reyan Abudi
28 Aug 2026, 20:30 UTC76 viewsread 3 October 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Reyan Abudi
26 Aug 2026, 09:42 UTC118 viewsread 3 October 2026 Forwarded from @AlimrancmcPhoto
✨ የመውሊድ በዓል ድምቀቶች ✨
በዛሬው የመውሊድ ፕሮግራም ድምቀት ከነበሩት መርሀ ግብሮች መካከል፣ በአህባቡል ሐቢብ የመድህና ነሺዳ ጀመዓ የቀረበው በአይነቱ ልዩ የሆነ አዲስ ነሺዳ አንዱ ነበር። 🎙️✨
በተጨማሪም ከኢማም አል-ቡሰይሪ የቡርዳ ቀሲዳ የተመረጡ የነብያችን ﷺ ውዳሴዎችን በድምፁ በማቅረብ የታዳሚውን ልብ ያለሰለሰው ተማሪ አቀራረብም ከዕለቱ የማይረሱ ትዕይንቶች አንዱ ነበር። 🤍🌙
በመቀጠልም የዙሁር ሶላተል ጀመዓ ከተሰገደ በኋላ፣ የምሳ ግብዣና የመውሊድ ሰደቃ በመካሄድ የዕለቱ አንኳር መርሀ ግብር ሆኖ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። 🍽️🤲
🌹 በውልደቱ ተደስታችሁ ያገለገላችሁ፣ ፕሮግራሞችን ያሰናዳችሁ፣ ለመድረኩ ውበትና ስኬት የተጋችሁ ሁሉ፤ አላህ ሥራ…
Signed Reyan Abudi
Showing the 12 most recent of 12 posts we hold for @Reyan_islamic_post. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.