28 Aug 2026, 14:36 UTC154 views2 reactionsread 28 August 2026 Photo
የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን አስቀድሞ ከተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ማዛወር፣ ተቀብሎ ማስተማር በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን 06/11/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ሰርኩላር፤ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በሚኒስቴር መ/ቤቱ በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብ መሆኑን አስታውሷል፡፡
ይሁን እንጂ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተመደቡ ተማሪዎች በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እየተማሩ ያሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ ጥናት፣ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ዕውቅና ውጪ ዩኒቨርሲቲዎች ባልተሰጣቸው ስልጣንና አ…
❤2
27 Aug 2026, 20:15 UTC226 views4 reactionsread 28 August 2026 Photo
#ጥቆማ
እንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም ክፍያ በማንኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው ይማሩ!
ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን የመምህራን እና የተማሪዎችን እንግሊዘኛ ቋንቋ ለማሻሻል የሚያግዝ ፖርታል ይጠቀሙ፡፡
ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጀ ነው።
በቀላሉ ለመረዳት በሚቻሉ በድምፅ፣ በፅሁፍ እና በምስል በተቀናበሩ ማስተማሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያስችል ትምህርት ያገኛሉ።
ወደ ፖርታሉ ለመግባት👇
http://learn-english.moe.gov.et
ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት የሚያስፈልግ ቢሆንም ገንዘብ የማይቆርጥ ሲሆን፤ በስማርት ስልክ፣ ስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌት እና በኮምፒውተር በማንኛውም የዌ…
❤4
27 Aug 2026, 11:28 UTC294 views8 reactionsread 28 August 2026 Photo
በሀገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች ከፍተኛ የሆነውን የ12ኛ ክፍል ውጤት (583) ያስመዘገበችው ተማሪ ሕዳሴ ዘመኑ ሽልማት ተበረከተላት።
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ከእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የዕውቅና መርሐግብር፤ ተማሪ ሕዳሴ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልክ ተሸልማለች።
ተማሪ ሕዳሴ ዘመኑን ለላቀ ውጤት ያበቁ ወላጆቿ እና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርም ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የተማረችበት አገው ምድር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።
@tikvah_edu
❤4👏4
26 Aug 2026, 19:04 UTC363 views14 reactionsread 28 August 2026 Photo
የተማሪዋ አሳዛኝ መጨረሻ‼
12ተኛ ክፍል ፈተና የወደቀች ልጅ ራሷን ማጥፋቷ ተሰምቷል ❗
በምስራቅ ሲዳማ ዞን በንሳ ዳዬ አካባቢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ባለማለፏ ምክንያት የተሰማትን ከፍተኛ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ መቋቋም ያልቻለች የ18 ዓመት ወጣት ተማሪ፣ «ቦኖራ» በተባለ ወንዝ ውስጥ ራሷን አስገብታ ህይወቷን በማጥፋቷ የተሰማው ዜና የብዙሀኑን ልብ ሰብሯል ።
⚠️ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ህይወትን የሚወስን እንዳልሆነ እና የሰውን ዋጋ፣ ችሎታ ወይም የወደፊት ህይወት እንደማይገድብ በመገንዘብ ብሎም ሌላ ዕድል ፣ ሌላ መንገድ እና ሌላ ጅማሬ እንዳለ በማሰብ ወደተሻለ የህይወት መስመር መጓዝ ያስፈልጋል ።
ትምህርት እውቀት እንጂ ህይወት አይደለም‼
…
😭4😱4❤2😢2😨1🙊1
26 Aug 2026, 14:18 UTC369 views6 reactionsread 28 August 2026 Photo
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ተማሪዎች በሙሉ (100%) የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ተማሪ ሰምሃል መሃሪ የትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት 550.76 ማስመዝገቧ ተገልጿል፡፡
@tikvah_edu
❤6
26 Aug 2026, 09:44 UTC379 views4 reactionsread 28 August 2026 Photo
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል በ2018 ዓ.ም ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ (100%) ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ካሳለፉ 88 ትምህርት ቤቶች መካከል፣ አራት ትምህርት ቤቶች በትግራይ ክልል የሚገኙ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።
@tikvah_edu
❤4
26 Aug 2026, 09:44 UTC335 views3 reactionsread 28 August 2026 Photo
የጋሞ ባይራ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም ያስፈተናቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ (100%) አሳልፏል።
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተፈተኑ 172 ተማሪዎቹ በሙሉ (100%) ማለፋቸውን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር አሳውቋል።
@tikvah_edu
❤3
26 Aug 2026, 09:43 UTC340 views3 reactionsread 28 August 2026 Photo
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
566.92 በትምህርት ቤቱ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት ሲሆን ዝቅተጋው ውጤት ደግሞ 448 መሆኑ ተገልጿል፡፡ ትምህርት ቤቱ በተከታታይ ለሦስተኛ ዓመት ያስፈተናቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ (100%) ማሳለፍ ችሏል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሚደገፈው ነገሌ ቦረና ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተመሳሳይ በ2018 ዓ.ም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ (100%) አሳልፏል።
ሌላው በዩኒቨርሲቲው የሚደገፈው በቆጂ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተመሳሳይ በ2018 ዓ.ም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ (100%) አሳልፏል።
@t…
❤3
26 Aug 2026, 08:57 UTC312 views4 reactionsread 28 August 2026 Photo
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም ያስፈተናቸው 34 ተማሪዎች በሙሉ ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
18 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን፣ 568.3 በትምህርት ቤቱ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት ሆኗል።
@tikvah_edu
❤4
26 Aug 2026, 08:06 UTC311 views3 reactionsread 28 August 2026 Photo
በውጤትዎ ላይ ቅሬታ አለዎት?
የ 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ማጠናቀቂያ ፈተያ ውጤት ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በኦንላይን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
@tikvah_edu
❤3
26 Aug 2026, 08:00 UTC297 views3 reactionsread 28 August 2026 Photo
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎች በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።
566.5 በትምህርት ቤቱ ተማሪ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት ሲሆን፣ ዝቅተኛው ደግሞ 417 መሆኑ ተገልጿል።
ትምህርት ቤቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
@tikvah_edu
❤3
26 Aug 2026, 08:00 UTC278 views4 reactionsread 28 August 2026 Photo
የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎቹ በሙሉ ማለፋቸውን ገልጿል።
ትምህርት ቤቱ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተናቸው 69 ተማሪዎች በሙሉ ያለፉ ሲሆን፣ በሲዳማ ክልል ይህን ማሳካት ከቻሉ ሁለት ትምህርት ቤቶች አንዱ ሆኗል።
@tikvah_edu
❤4
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @Tikvah_edu. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.