11 Sept 2026, 08:25 UTC360 views16 reactionsread 14 September 2026 Photo
እንቁጣጣሽ❤ እንኳን❤ ከዘመነ 🌹ማርቆስ 🌹ወደ ዘመነ 🌹ሉቃስ❤ ለዘመን መለወጫ🌹 በዓል በሠላም አደረሰን🌹 አደረሳችሁ 🌹 በዓሉን
ያለ ፀብ ~በፍቅር🌹
ያለ ህመም ~በጤና❤
ያለ ቂም ~በይቅርታ🌹
ያለ ሀሜት ~ በፀሎት ❤
ያለ ስስት ~በምፅዋት🌹
ያለ ክፋት -በቅንነት ♥️
ያለ ሀጢአት~በቅድስና🌹
ለማክበር የእናቱና የልጇበረከት ከሁላች ጋር ይሁን። ወስብሐት ለእግዚአብሄር።❤
መልካም🌹🌹🌹አዲስ ዓመት🌹🌹🌹!!!
❤8🔥8
8 Sept 2026, 06:31 UTC606 views12 reactionsread 14 September 2026 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ መንፈስቅዱስ ስም ጳጉሜን 3 በዚህች ቀን የረድኤት የፈውስ መልአክ የተባለ፣ በመናብርት ላይ ለተሾመ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የሲመቱና የቅዳሴ ቤቱ በአል ሆነ። ይህቺ ቀን የፍጡር ሁሉ ጸሎት የሚሰማባት፣ መተትና ስራይ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት የሚደመሰስባት፣ የአጋንንት ስራ የሚፈርስባት፣ የረድኤት፣ የበረከት፣ የጸጋ ሁሉ ቀን ነችና፣ ሁላችንም በአቅማችን ጸሎት እናደርግ ዘንድ፣ አንዳችንም ሌላዎችን እናስብ ዘንድ ይገባናል።
ዳግመኛም በዚህች ቀን ለዘመኑ ጥንትና ፍጻሜ የለውም ተብሎ የተነገረለት በእግዚአብሔር እጅ ካህን እና ነቢይ ሆኖ ሊሾም፣ የክርስቶስም ምሳሌ ሊሆን የተገባው ታላቁ ቅዱስ መልኬጼዴቅ በሰላም አረፈ። እ…
❤12
2 Sept 2026, 15:32 UTC883 views6 reactionsread 14 September 2026 Photo
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ" ማቴ 26፥41
ወርኃዊ የመሐረነ አብ ጸሎት 🤲
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን
በግቢ ጉባኤያችን በወሩ የመጨረሻ አርብ የመሐረነ አብ ጸሎት እንደምናደርስ ይታወቃል። ስለሆነም የፊታችን አርብ ነሐሴ 29/11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 - 11፡00 የአመቱ የመጨረሻው የመሐረነ አብ ጸሎት ስላለ ሁላችሁም በመገኘት ስለ ሀገራችን ፣ ስለ ሃይማኖታችን ፣ ስለ ማኅበራችን በኅብረት እንጸልይ ስትል ግቢ ጉባዔያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
ለበለጠ መረጃ፦
0912947576
0970038830
ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
❤6
29 Aug 2026, 19:32 UTC≈1,060 views31 reactionsread 14 September 2026 ✨እንኳን ለአቡነ ተክለሃይማኖት አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✨
የአቡነ ተክለሃይማኖት ታሪክ
ከአባታቸው ከጸጋ ዘአብ (ዘርአ ዮሐንስ) እና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኅረያ (ሣራ) በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት በመጋቢት 24 1196 ዓ.ም ተጸንሰው በዕለተ ሰኞ ታህሳስ 24 1197 ዓ.ም በቡልጋ፣ ሸዋ በዘመነ ዛግዌ ሥርወ መንግሥት በቅዱስ አፄ ነአኩቶ ለአብ ዘመን ተወለዱ ።
እንደተወለዱም ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመሰገኑ። በ3ተኛውም ቀን ደግሞ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግናዋል።
ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍስሐ ጽዮን አሏቸው።ይህም የጽዮን ደስታ ማለት ነው በእመ…
❤31
27 Aug 2026, 18:40 UTC855 views4 reactionsread 14 September 2026 Photo
✨እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗
እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የዓመቱ የመጨረሻው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የጽዋ መርኃግብር ይኖረናል።
በዕለቱም ጸሎት፣ ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ፣ የኅብረት ዝማሬ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርኃግብራት ስለሚኖሩ ሁላችንም ተጠራርተን በመምጣት በዓሉን አብረን እንድናከብር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች!
📆 ቅዳሜ ነሐሴ 23 ፤ 2018 ዓ.ም
🕰 ከቀኑ 06:00 ጀምሮ
አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም
ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ ፦
0912947576
0970038830
ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
❤4
21 Aug 2026, 18:29 UTC≈1,180 views12 reactionsread 14 September 2026 እንኳን አደረሳቹሁ
በዓለ ፍልሰታ ወዕርገታ ለማርያም ወፍልሰተ አጽሙ ለሊቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት
ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን…
❤7🙏5
18 Aug 2026, 19:20 UTC≈1,110 views7 reactionsread 14 September 2026 ደብረ ታቦር
የታቦር ብርሃን ቀድሞ የሚያበራ የትንሣኤ ብርሃን ነው::
በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሶቹም እንደ ብርሃን ነጭ ሆኑ። ሙሴና ኤልያስም በግራና በቀኙ ቆመው ነበር። "ብሩህ ደመናም ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ እንዲህ የሚል ድምፅ መጣ፦ 'የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ በእርሱ ደስ ይለኛል'" (ማቴዎስ 17፥1 -8)።
ክርስቶስ ለሐዋርያው እንደተገለጠው "በእግዚአብሔር መልክ"
(ፊል 2፥6-7) ነበር—እርሱም ከሥላሴ አካላት አንዱ ሆኖ ነው። ይህ መገለጥ ስለዚህ የሥላሴ መገለጥ (theophany) ነበር፤ የአብ ድምፅና መንፈስ ቅዱስ በብርሃናዊው ደመና ውስጥ ተገኝተዋል።
"የታቦር ብርሃን የተፈጠረ ብርሃን አይደለም፤ እርሱ የመለኮት ያ…
❤7
18 Aug 2026, 08:43 UTC≈1,110 views3 reactionsread 14 September 2026 ✅ የስራ ማስታወቂያ
የስራ መደቡ መጠሪያ: Architect
የስራ ልምድ : 0 - 2 ዓመት
የስራ ሰዓት: ከ ጠዋቱ 2 :00 - 11:00
አድራሻ : Gerji Unity University ከፍ ብሎ
ደሞዝ: በስምምነት
Portfolio በ 0916832471 ይላኩ
❤3
14 Aug 2026, 18:57 UTC675 views3 reactionsread 14 September 2026 Photo
✨እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗
እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የበዓለ ደብረታቦር ልዩ መርኃግብር ይኖረናል።
በዕለቱም ጸሎት፣ ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ፣ የኅብረት ዝማሬ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርኃግብራት ስለሚኖሩ ሁላችንም ተጠራርተን በመምጣት በዓሉን አብረን በድምቀት እንድናከብር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች!
📆 ቅዳሜ ነሐሴ 9 ፤ 2018 ዓ.ም
🕰 ከቀኑ 06:00 ጀምሮ
አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም
ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ ፦
0912947576
0970038830
ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
❤3
14 Aug 2026, 05:02 UTC≈1,190 views7 reactionsread 14 September 2026 ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ ከቅዱስ ምሥጢር የሚቀበሉ ሁሉ እንዲህ ይበሉ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ርኵስት ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም።
እኔ አሳዝኜሃለሁና በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና ሥራም ምንም ምን የለኝምና።
ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፣ ስለ ክቡር መስቀልህም፣ ማሕየዊት ስለ ምትሆን ስለ ሞትህ፣ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ፣ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁም።
የቅድስናህንም ምሥጢር
በተቀበልኩ ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራ…
❤6👍1
13 Aug 2026, 18:34 UTC≈1,040 views8 reactionsread 14 September 2026 በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ቀን እነሆ ደረሰ 🤗
በነገው ዕለት በግቢ ጉባዔያችን የሕይወት ቀን (በሕብረት ቅዱስ ቁርባን የመቀበል ቀን) እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም ከቅዳሴ ሥርዓት ጀምሮ ሁላችንም በዕለቱ የሚቀበሉ ወንድም እና እህቶቻችንን በማጀብ አብረን በማስቀደስና ከቅዳሴ በኋላ ደግሞ አጋፔ (የጋራ ማዕድ) በመሳተፍ ይህንን ልዩ ቀን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን🤗
🕰 ከቀኑ 05:00 - 11:00
አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም
ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ ፦
0912947576
0970038830
ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
❤8
13 Aug 2026, 16:40 UTC935 views2 reactionsread 14 September 2026 Photo
✨ የሕይወት ቀን - '1 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨
📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም
ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
🙏2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @UnityGebiGubae. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.