4 Aug 2026, 06:10 UTC46 views2 reactionsread 9 August 2026 « የሆነ ልብህን ረጠብ፣ በአደብ ሞቅ፣ በፈገግታ ለስለስ፣ የሚያደርግ ነገር ካሻህ ስለ እናታችን ኸዲጃህ እና ስለ አሽረፈል ኸልቅ ፍቅር አንብብ!
አላህ… አላህ… እንዴት ያለ መተናነስ… እንዴት ያለ መፋቀር… ሰርክ ቢደጋግሙት የማይጠግቡት አይነት።
አጂብ የሆነ ፍቅር ነው መቼስ አንደበቱ በማይጥም ሰው እንኳ ሲነገር ቢደመጥ የማይሰለች።
«እኔ ፍቅሯን ተሰጠሁኝ! » ፍቅር በራሱ እንደዚህም አልተገለፀ።
የሁሉም የዱንያ የሕይወት ውጣ ወረዶች አሉት በፍቅራቸው ውስጥ። ስለ ሕይወት ምንም ባታውቅ የጧሒራን እና የነብያችንን የፍቅር ሕይወት ብቻ ጠልቀህ ብትመረምር የሚጎድልብህ የለም።
በሕይወታቸው ውስጥ በነበረው ያ ሁሉ ውጣ ወረድ ግን ፍቅራቸው የተባ፣ ንፅህናው እንደተ…
❤2
Signed Babi
4 Aug 2026, 05:55 UTC41 views6 reactionsread 9 August 2026 Photo
መገን አኽላቅ ውበት ኩሎ
መገን ልህቀት ዝንት ተተክሎ
መገን ክብር አስከብሮ
ናፍቆት ጠንቶ ፍቅር ታፍሮ
ሰው መሆን በፍጥረት ገንኖ
ሁሉን አየን ሙሀመድን ሆኖ።
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13M
@Venuee13M
❤6
Signed Babi
3 Aug 2026, 08:26 UTC45 views4 reactionsread 9 August 2026 Photo
አህመድ ጧሃ ዘይኑ የምግባሩ ዋርካ
ሙሀመድ አሚኑ ሳይመጣ የፈካ
ቢቀርቡት ጀነት ቢርቁት መባከን
ሙሉዕነት ካባው አንድ የሌለው እንከን።
በእዝነት ሲዳብሱ በኢሽቅ ሲያቀናጡ
ደንደን ያሉ ልቦች ገር መሆን መረጡ
ያጣ ሲያባሽሩ አይቶ የተደነቀ
የቲም በሆንኩ ብሎ አለ የናፈቀ።
ዱንያ ያስበረደው ሰላሙ የራቀው
አንቱን ሲያወሳ ልቦናውን ሞቀው
ስምዎ የሪዝቅ መንገድ የሀሴት መድረሻ
አንቱ የትፍስህት የኑር ለምለም እርሻ።
እንኮይ ሙዳይ የውበት ገፅ
በልብ አፀድ የሚታነፅ
በነፍስ ዜማ የሚቀለፅ
በፍጥረት አፍ ማይገለፅ
ሀለትዎ ድንቅ
ለዛዎ ስንቅ
አንቱ ውዱ፣ ሙሀመዱ
ብራ ጠሀይ የመንገዱ
ሸፈዓዬ አህመዴዋ
የናፈቁኝ ነብዬዋ።
ሙሉዕ ሆኖ መኖር፣ ተሟልቶ መፈጠር፣
በከውናቱ ዘል…
❤4
Signed Babi
3 Aug 2026, 08:15 UTC47 views3 reactionsread 9 August 2026 Photo
« ብዙዎች ፍቅርን ተጠቅመው አፈቀሩ። እንያ ፍቅር ግን ፍቅርን ሆኑ። በእርግጥም ፍጥረታት ፍቅር መሆንን ከእሳቸው ሊማሩ ተጉ። አንዳቸውም ግን ፍቅርን ማፍቀር እንጂ ፍቅርን መሆን አልተቻላቸውም። ከፍጥረታት ውስጥ የፍቅር የረቂቅነት ጥልቀት ሚዛን ልኬታውን ያሟሉት ፍቅርን የሆኑት ፍቅር የሚናፍቃቸው ንፁሁ ፍቅር ብቻም ሆኑ። በእርግጥም ፍቅር የልቅና ስሙ ሙሀመድ አለይሂ ሰላም እንጂ ሌላ አይደለም።
አል ወዱድም እንደሳቸው ያላቀው፣ ፍቅር ሲነሳ እንደ ንፁሁ ፍቅር መወሳቱን ከፍ ያደረገው አንድም ፍጥረት የለም። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13M
@Venuee13M
🥰3
Signed Babi
2 Aug 2026, 18:56 UTC56 views4 reactionsread 9 August 2026 « አርቆ አሳቢው፣ እዝነትም ጀግንነትም በአንድ የተላበሱት፣ ሲቆጡ ከእዝነት የተጣሉ፣ ሲያዝኑ ፈፅሞ ቁጣ የማይቀርባቸው የሚመስሉት፣ ግርማ ሞገሳሙ ፍትህ የሚናፍቃቸው ኡመር ኢብኑል ኸጧብ አርቆ አሳቢነታቸው፣ ሰዎች ከአላህ ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዳይበላሽ የሚያደርጉት ጥንቃቄ፣ ጥልቁ አስተውሎታቸው አጀብ ነው።
የምዕመናን መሪ አሚረል ሙዕሚኒን እንደሆኑ አንድ በጣም ረቂቅ አስተውሎትን የሚጠይቅ እና እጅግ ከባድ የሆነን ውሳኔ ወሰኑ። ሮማውያን፣ ፋርሶች፣ የአረብ ዘላን ጎሳዎች፣ ጊዜ ጠብቀው ሙስሊሞችን ማጥፋት ግባቸው የሆኑት ሙናፊቆች ሁሉ አሰፍስፈው በቆሙበት ጊዜ ያልተጠበቀ፣ ለብዙዎች ስህተት የመሰለ ትክክለኛ ውሳኔን አስተላለፉ። ይህም ለየርሙክ ዘመቻ በተሰናዱበ…
❤🔥4
Signed Babi
2 Aug 2026, 18:46 UTC483 views6 reactionsread 9 August 2026 « ሰው በሁሉም ሲዋብ፣ በሁሉም የተዋጣለት እንደሚሆን አወቅን። በእርሷ በሴቶች አውራ፣ የኸልቁን ፍቅር በፍቅር በጠቀለሉት፣ በልባቸው በክብር በተቀመጡት፣ ከሰው ልጆች አይነታ ልብ ውስጥ ክብራቸው ማንም ሊነቀንቀው ባልቻለው የተከበሩት የአሽረፈል ኸልቅ ውድ ሪዝቅ በሆኑት በምዕመናን እናት በኸዲጀቱል ኩብራ።
ስለ ፍቅር ምን ታውቃለህ ብባል እሳቸውን እላለሁ። በየትኛው ፍቅር ትብቃቃለህ ብባል በእሳቸው ፍቅር እላለሁ። የሰማየ ሰማያት፣ የእልፍ አዕላፍ ዓለማት፣ የሁሉም ነገሮች አድራጊ ፈጣሪው፣ ልዕለ ኃያሉ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የመላዕክቶች ሁሉ አለቃ የሆነውን ጅብሪልን ልኮ ሰላምታን ላከላቸው። መገን ውዴታ! መገን መመረጥ።
እናታችን ኸድጃ እንዴት አይነት የታፈ…
❤5❤🔥1
Signed Babi
2 Aug 2026, 18:44 UTC60 views4 reactionsread 9 August 2026 « ሁቡ ረሱሉላህ ዘይድ አብኑ ሀሪሳ የዚህን ያህል ረሱል ዘንድ ለምን ተወደደ? ስል እጠይቃለሁ ለራሴ። ዘይድ በስነምግባሩ የተዋጣለት፣ ትሁት እና ምግባረ ሰናይ ሰው ነው። ሁሉም የረሱሉላህ ባልደረባዎች ምግባራቸው እጅጉን የተዋበ ነው። ግን ከሁሉም ባልደረባዎቻቸው በተለየ ዘይድ ሁቡ ረሱሉላህ ለምን ተሰኘ ስል አሰብኩ።
ጥያቄዬ ወዴት ወሰደኝ። እዚያ ምንም አይነት ምትክ የማይገኝለት፣ አንደበቱ በማይጥም ሰው ቢነገር እንኳ ስለማይሰለቸው፣ ልብን በፍቅር ሞቅ ወደሚያደርገው ፍቅር ወሰደኝ። የጧሒራ እና የአሚኑ ፍቅር ዘንድ።
አሽረፈል ኸልቅ ውዴታቸው፣ አክብሮታቸው ሁለመናቸውም ንፁህ ነው። ለንፁኋ ያላቸው ፍቅር ደግሞ ለየት ይላል። ዘይድ ሁቡ ረሱሉላህ ለመባሉ አንደኛ…
❤🔥3❤1
Signed Babi
1 Aug 2026, 16:31 UTC419 views3 reactionsread 9 August 2026 File
ንፁህ ፍቅሬን አልሰጠኾትም!
:
@Venuee13M
@Venuee13M
😢3
Signed Babi
1 Aug 2026, 15:48 UTC82 views3 reactionsread 9 August 2026 " ይድረስ ብዬ የምለው… "
ክርታሴን ከፍቼ፣ ብዕሬን አንስቼ
የውስጤን የአንጀቴን ብሶቴን ቋጥሬ
" ይድረስ ለታላቁ… " አልኩና ደፍሬ
መልሼ ሰረዝኩት በስራዬ አፍሬ።
አሰላሙ ዓለይኩም ያልቀረብኮት ደጉ
ከመንገዶ ስርቅ የቀረሁ ከጥጉ
እኔ ያንቱ ወንድም ናፍቆቶን የምሻ
በአፍ ብቻ እያመንኩ የጠፋኝ መድረሻ።
በምን ቃል ነጥዬ በምናቤ ሄጄ
ባገኞት ማወጋ ንፍቅናዬን ጥጄ?
ባልዋሉበት ግድም ስሞ እየጎደፈ
ለክብሮ ሊሰዋ ልቤ እየሰነፈ
ወዳጆን ያላቀ ጠኔ ሲያነደው መቆጨትን ጥዬ
ምንም ማድረግ ያልቻልኩ በእንጃ ጉያ ውዬ
እንደምን አስቤ በምናቤ ስዬ
በምን አቅም ልግለፅ ይድረስ ላንቱ ብዬ?
አሰላሙ ዓለይኩም አንቱ ታላቅ መሪ
ላለፈው ላሁኑ ለመጪው ሁሉ አብሪ።
እኔ ውልግ…
❤3
Signed Babi
31 Jul 2026, 07:29 UTC101 views4 reactionsread 9 August 2026 Video
« ፍቅር ጥልቅ ነው። ለአላህ የሆነ ፍቅር፣ ለንፁሁ መልዕክተኛ የሆነ ፍቅር ረቂቅ ነው።
የንፁሁ ፍቅር ልብ ንፁህ አድርጋ ስትይዝ ፍቅሯ ይጋባል።
ያንን ልዕለ ምግባር የተራቡት አሉ፣ በስራቸው ሳይሆን በአላህ እዝነት ላይ ብቻ ተማምነው በጀነት ሊያገኟቸው፣ አሰላሙ ዓለይኩ ያ ሀቢበሏህ ብለዋቸው የሰላምታቸውን ምላሽ በጀነት መስማትን የናፈቁ አሉ።
ፍቅር ንፁህ ሲሆን የሌሎችንም ቀልብ ያናግራል፣ አይኖችን በሀያዕ እንባ ያጥባል፣ ፈገግታን ይሞሽራል፣ ንፁህ ተስፋን ያሰንቃል።
ከፍጥረታት ውስጥ ንፁህ የሆነን የተከበረ ፍቅርን የሚደርሳቸው፣ በወቅት በዘመን፣ በእድሜ በእውቀት ሳይገደብ ጥልቅ የሆነ ረቂቅ ፍቅር ልቦች ሸሽገው የሚያስቀምጡት ለባለ ታላቅ ጠባዩ ለአሚናይቱ ል…
❤4
Signed Babi
31 Jul 2026, 07:11 UTC101 views1 reactionsread 9 August 2026 « የቁረይሽ ንግስት፣ የመጀመርያዋ የምዕመናን እናት፣ ጧሒራ፣ ባለ ሙሉ ስብዕና ባለቤቷ ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ። ሰዎች ውብ የሆነውን መልካቸውን የሚያስረሳ እጅጉን ያማረ ምግባር የተላበሱ ንፁህ ሰው። አንዲትንም ነገር ከልብ ወለድ የማይናገሩት፣ ንግግራቸው ፍፁም እውነት የሆነው ንፁሁ ነብይ አብዝተው የሚናፍቋቸው፣ ምትካቸው ያልተገኘው፣ ሁሌም ረሱል ዘንድ በክብር የሚወሱት ጧሒረቱ።
የፍጥረታት እንቁ፣ የባለ ታላቅ ጠባዩ፣ የልዕለ ምግባር የልቅና መቋጫ የሆኑት፣ የታማኙ ፊተ በሻሻው ነብይ ዘር በብቸኝነት በእሳቸው በኩል ብቻ እንዲቀጥል አላህ የመረጣቸው ኸዲጀቱ።
መገን ምግባር ከውበት ይበልጣል። እንዴት ያሉ ሴት ቢሆኑ ከሴቶች ሁሉ የተላቁ ሆኑ። አዕምሮ አሰላስሎ፣ …
❤1
31 Jul 2026, 07:05 UTC460 views1 reactionsread 9 August 2026 ልክ እንደ ሲዲቁ ንፁህ ፍቅር ባኖር
እንደ ወንዱ ፋሩቅ ፍትህ ሆኜ ብዞር
ከኡስማኑ ሀያዕ ስንቅ ብይዝ ለአደቤ
እንደ ዓሊ ሂማ ማፍቀር ቢያውቅ ልቤ
ንፁህ የምሰጠው፣ ንፁህ የማደርሰው
ምናል ንፁህ ብሆን የሻው ንፁሁ ሰው
ወንጀሌ አራግፌ ንፁሁን ባነግሰው?
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13M
@Venuee13M
👍1
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @Venuee13M. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.