5 Aug 2026, 06:53 UTC57 views8 reactionsread 8 August 2026 Photo
አንዳንዴ መኖር መሞትህ ግድ ማይሰጣቸው
ሰሆች እንዳሉ ማወቅ አለብህ ምትኖረው ለራስነው ሲኖርህ የከበበህ በሙሉ ስታጣ ከጎንህ አይሆኑም ማንም መኖርህን አያስተውልም ማንም መሞትህን አያስተውልም ሞተሀል ቢሏቸው እንኳን ሁሉም ተሰብስቦ ካርታነው ሚጫወተው በሳምንቱ ትረሳለህ እና ወዳጄ ለዚች አለም ለምን ትጨነቃለህ ስትኖር ሰው ለማስደሰት ሳይሆን ፈጣሪህን ለማስደሰት ኑር ህይወት ቢመርህም እስኪጠራህ ድረስ በጸሎትህ ተግተህ እራስህን ለውጥ ማንም ስላንተ ግድ የሚሰጠው የለምና ሁሉም በራሱ አለም ነው አንተም አርፈህ መኖርህን ቀጥል ወዳጄ
✍abilo
❤8
2 Aug 2026, 18:48 UTC95 views14 reactionsread 8 August 2026 ይድረስ ለበቆሎ
ሽፋኗ ተገልጦ በእጅ ታሽታ ወይም ተፈልፍላ የተበላች በቆሎ ለገበያ አትቀርብም ፣ አትተመንም ፣ መውደቂያም የላትም ።
ድንገት ተአምራዊ ነገር ከተጎናጻፋት መልሳ በቆሎ የመሆን እድል አላት ።
ተአምሮች ደግሞ ሰዋዊ ሳይሆኑ መለኮታዊ ናቻው ።
ይድረስ ለበቆሎ
ምሳሌ ሆነሽ ነው ፤ እኔን አትቆጪ
አፈጣጠርሽ ነው ፤ አንቺስ ተገለጪ
ይድረስ ለበቆሎ
በጣሙን በጣሙን ፤,ምስጋና ይድረስሽ
እንዴት እጽፍ ነበር ፤ ገልጬ ባልግጥሽ
✍ menduban
🔥10👏4
31 Jul 2026, 17:17 UTC92 views7 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @love_words_qutes
አንድ ገጠር ቀበሌ ውስጥ አንዲት እህል ስትፈጭ የምትኖር ሴት ነበረች። ከጎዶሎ ቀኖች ባሏ ታሞ ይተኛል። ጎረቤቷ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም አጥሯን ገፋ አድርጎ ቤት ይሠራል። ጎረቤትየው ያዲሱን ቤት ግድግዳ ያቆመበት (የገደገደው) ቦታ ሴትዮዋ ሽንቷን የምትሸናበት እንዲሁም ግብር ውሃ የምትወጣበትን ስፍራዋ ነበር። ታመመና ባሏ ሲሞት ቀብር ላይ እንዲህ አለቀሰች
''እንኳንስ አንተ ሞተህ እያለህልኝ
በሽንት መሽኛዬ ላይ ገደገዱብኝ''
ይህንን ሲሰማ ለቀስተኛ ሁሉ ሳቀ‼ ጥርሱ ይርገፍእና
(በእውቀቱ ስዩም ከማለዳ ድባብ✍️ከሚለው መፅሃፉ ገፅ 94)
@love_words_qutes
@love_words_qutes
@love_words_qutes
😁6❤1
29 Jul 2026, 19:12 UTC86 views7 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @love_words_qutesPhoto
ሰላም ሰላም🙌🙌
የበቀል ስብራት የተሰኘውን የፀሀፊ ቪክቶሪ ድርሰት የሆነውን ምርጥ ትረካን በተከታታይ ክፍሎች እናቀርብላችኋለን
በቅርብ ቀን ጠብቁን🙌
@love_words_qutes
@love_words_qutes
@love_words_qutes
❤7
28 Jul 2026, 12:56 UTC83 views9 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @love_words_qutes
ፍቅር የሞተበት ልብ ፍቅርን የሚሸሽ አእምሮን ይወልዳል አንዳንድ ሰዎች ፍቅርን አይጠሉም። የሚሸሹት ግን በፍቅር ስም ያገኙትን ህመም ነው፡፡ አንድ ሰው ከልቡ ሲወድ ፍቅር ብቻ አይሰጥም። እምነቱን ይሰጣል። ህልሙን ይሰጣል። ነገውን ይሰጣል። ራሱን ሙሉ ለአንድ ሰው አደራ ያስረክባል። ከዚያ በኋላ ያ አደራ ሲከዳ፣ የሚሰበረው ልብ ብቻ አይደለም። የሰዎችን ልብ የማመን አቅሙም አብሮ ይፈርሳል። ስለዚህ አንዳንዶች ግድየለሽ የሚመስሉት ቀዝቃዛ ሰዎች ስለሆኑ አይደለም። ብዙ ጊዜ በጣም ሞቅ ያለ ልብ ኖሯቸው ስለነበር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ይጠይቃሉ። "ለምን እንደገና አትወድም?" "ለምን ልብህን አትከፍትም?" መልሱ ግን ቀላል አይደለም፡፡ አንድ ጊዜ በእሳት የተ…
❤8🔥1
27 Jul 2026, 10:14 UTC76 views6 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @love_words_qutesPhoto
መልስልኝ እስቲ🥺
አልከለክልህም
መገድን አሊዝም
አትሂድ እያልኩኝ አልልብህም አወይ😞
እስቲ መልስልኝ?🤔🥺
ከራስ በላይ መውደድ መገድ ይጠርጋል ወይ?
የናተው አክታቢት✍
@love_words_qutes
@love_words_qutes
@love_words_qutes
🥰6
26 Jul 2026, 15:22 UTC124 views11 reactionsread 8 August 2026 ሞት
ሞት ያልተጠበቀ ክስተት ነው። አስቀድሞ የጥሪ ካርድ አይሰጥም። በፀጥታ ይመጣና በአንድ ተራ ቅፅበት መጨረሻችንን እንካቹ ይላል። የምንወዳቸውን ሰዎችም ለመሰናበት ዝግጁ ሳንሆን ትዝታ ይሆናሉ።
በሞት ህግ ነገ ማለት ተስፋ እንጂ የተረጋገጠ ቃልኪዳን አይደለም።
የሞት አሳዛኝ ክፍሉ አንድ ሰው መተንፈስ ማቆሙ አይደለም።.......ያ ሰው በሌለበት አለም መቀጠሉ ነው። ፀሀይ መውጣቷን ትቀጥላለች፣ ዝናብም ይዘንባል፣ ሰዎችም ይስቃሉ፣ ሰዓታትም ይሄዳሉ። ነገር ግን ለቀሪው ሰው "ለሟች ወዳጅ" ያ ሰው በጠፋበት ቅፅበት ቅዝቃዜ ይሰማዋል። ልክ መድረሻ እንዳጣ ፍቅር። ለመጨረሻ ጊዜ ያሳለፉት ጊዜያት። እንዲሁም ስንብት የማይመስሉ ንግግሮች..... ለጥቂት ሰከንዶች ያ…
🔥4✍3👏3🤯1
24 Jul 2026, 08:24 UTC183 views13 reactionsread 8 August 2026 Video
ልጅ :- ማማዬ
እናት :- ወደይ
ልጅ :- ፍቅር ሒዙኒ
እናት :- ምስ መን ምስ መን እዪ ?
ልጅ :- ማልያም 🥰🥰 ማርያም 😍
😍5🤩4🥰4
21 Jul 2026, 17:34 UTC133 views8 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @love_words_qutes
እናተ ብቶኑ ምን ታደርጋላቹ?💔🥺
በእግሩ የወጣ በሳጥን ቢመለስ
ሰለነገ አውርቶ ምሽትን ባይደርስ
የኔ ያላቹት ሰው
ሞቶል ብትባሉስ!!!
ደም እንባ ቢለቀስ
አይን ቢጎረብጥ
ጥርስ ደስታ ቢአጣ
ገላ ጥቁር ቢለብስ
እግዝሄር ቢከሰስ
ያ ሰው አይመለስ
እያሉ ቢአወሩስ?
ነገለይ ደርሳቹ ትላት ለይ ቢቀር
እስቲ እናተ አውሩ ምን ታደርጉ ነበር?🥺
የናተው አክታቢት✍
@love_words_qutes
@love_words_qutes
@love_words_qutes
💔6😢2
19 Jul 2026, 16:40 UTC267 views14 reactionsread 8 August 2026 "ሕይወት ተረት ተረት አይደለችም"
አንዳንድ ሰዎች ሕይወት እንደ ተረት እንደሆነች እያመኑ ያድጋሉ።
ሰዎች ለዘላለም አብረውን እንደሚቆዩ፣ ፍቅር ፈጽሞ እንደማይጎዳ፣እናም የተሰበረ ማንኛውም ነገር በሆነ መንገድ እንደሚጠገን። እኔም ይህንኑ አምን ነበር።
ነገር ግን ሕይወት እንደዛ አይደለችም። እኔ ልዑሉን አይደለውም፣ አንቺም ሲንደሬላን አይደለሽም። ሕይወታችንን በአስማት የምትቀይርልን መልካም ጠንቋይ የለችም። ለማንም ሰው "ለዘላለም በደስታ መኖር ቀጠሉ" የሚል መጨረሻ አልተሰጠም።
ሕይወት የምታስተምረን በህመም ነው። ልናጣቸው የማንፈልጋቸውን ሰዎች እንድናጣ ታደርገናለች። ልባችንን ትሰብራለች፣ ህልሞቻችንን ታፈርሳለች፣ እንዲሁም ነገሮች ለምን እንደዚ እን…
❤🔥6🔥4🥰3👏1
19 Jul 2026, 09:04 UTC178 views17 reactionsread 8 August 2026 አንበሳዬ(1)
እድለኛ ሆኜ አገኘው ጓደኛ
በመልክም በፀባይ ከሁሉም አንደኛ
እኔም ተማርኬ አልኩት አንበሳዬ
ከድብርት አውጥቶ ሚሆነኝ ደስታዬ
ደስታዬ ስለው ግን ቀላል ደስታ አደለም
ደስታን አስተካክሎ የሚገልፀው ቃል የለም
ለዚህም ነው ያልኩት ደስታዬ ነው እሱ
ሌላ ቃል ባላገኝ ሚመጥነው ለሱ
ከደስታዬም በላይ ሆነ እንደ ወንድሜ
ምንም ሳልደብቀው ምነግረው ህመሜ
ብዙ ያዩን ሰዎች አሉኝ ፍቅረኛሽ ነው?
ከፍቅረኛም በላይ እሱ ደስታዬ ነው
✍️ወፏ🦜
🤗5✍4💘4❤2🔥2
19 Jul 2026, 03:48 UTC170 views10 reactionsread 8 August 2026 እቱ ኮከቢቱ!
በፀዳል ውበትሽ - ደመቀ ሌሊቱ
በሞገስሽ ጮራ - ሰከረ ፍጥረቱ
የሰማይ ፈርጥ ነሽ ኮከብ ነሽ በውነቱ።
መቼም ኮከብ ሆነሽ - ከጠፈር ባትሸሺም፣
ያዳም ዘር በምሽት - ከ'ቦ ቢያደንቅሽም፣
ማንም በሌት እንጂ - በቀን አያይሽም፣
አይገርምሽም!? ።
✍️በለው ገበየሁ
🔥9👏1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Wisdom1888. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.