10 Aug 2026, 06:16 UTC356 views10 reactionsread 12 August 2026 እግዚአብሔርን እየመረጥን ነው የምንሰማው?
2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡— እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ።
3 አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።
.
.
.
.
7 ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብፅ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው።
8 የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።
9 ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና በሬዎች ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያ…
❤10
Signed @doni
5 Aug 2026, 18:34 UTC713 views33 reactionsread 12 August 2026 ይህንን ሳታደርጉ ወደ መኝታችሁ እንዳትሄዱ
" በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና።" መዝ 4:8
✨ወዳጆቼ እንዴት አመሻችሁ? ዛሬ ቀኑን ከነበጀቱ ሰጥቶን ውለንበት አልፏል። ለአንዳንዶቻችን የደስታ ቀን፣ ለአንዳንዶችም የሀዘን፣ ለአንዳንዱ የውድቀት፣ ለአንዳንዱም የስኬት ቀን ሆኖ አልፎ ይሆናል ነገር ግን የሁላችንንም የቀን ውሎ እግዚአብሔር አይቷል። አሁን ውድቀታችን ከጠለቀችው ፀሐይ ጋር አብሮ አልፏል አሁን ለሊቱ ሊመጣ ነው። ስለዚህ ሁሉን ለእግዚአብሔር አስረክባችሁታል?
✨ አንዳንዶቻችን አልጋ ላይ ሰውነታችን ያርፋል እንጂ አዕምሯችን ግን ቢዚ ይሆናል የሃሳብ ትርምስ ውስ…
❤22🥰5🙏5🔥1
Signed @doni
3 Aug 2026, 07:53 UTC774 views23 reactionsread 12 August 2026 ሲመሽ ይመጣል ሲመሽ
ወዳጄ ያልከው ሲሸሽ" ዘ.ትዝታው
ቀን ሳለ የጨለመባቸው፣ በቀትር የመሸባቸው፣ የሚወዱትን ከዓይናቸውም ከልባቸውም የሸኙ፣ ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ሆኖ የራቃቸው፣ በዝግ ቤትና በዝግ ልብ መኖር የከበዳቸው፣ በአዕምሯቸው አደባባይ የወጡ፣ በብቸኝነት ብርድ የሚገረፉ ብዙ ናቸው።
🙏አቤቱ ኢየሱስ ሆይ በዝግ ቤት ሁሉን አልፈህ ገብተሃል። ይሄን ሁሉ ችግራችንን ጥሰህ ናልን። የመሸበትን ወዳጅ ነህና ዛሬ ናልን፤ ከፍቶናል የተከፉትን የምትፈልግ አንተ ነህና ዛሬ ናልን! በሀዘን ያዘቀዘቁ ብዙ አንገቶች አሉ ኢየሱስ ና ቀና አድርገን። የዓይናችንን ሳይሆን የልባችንን እንባ ጥረግልን። እንደ ራሔል የእንባን ጎርፍ ወዳንተ እናፈሳለን…
❤17🙏3👏2😢1
Signed @doni
2 Aug 2026, 17:59 UTC803 views21 reactionsread 12 August 2026 ኢየሱስን ለምንድነው የምትወዱት?
✨አንተ ያለ ምክንያት ወደድከኝ እኔ ግን በብዙ ምክንያት እወድኃለው።
✨ሳልወድህ ስለወደድከኝ፣ ሙት ሳለሁ ስላልረሳኸኝ፣ ፅድቄ እንኳን የመርገም ጨርቅ ሳለ ከእኔ ስላልራቅ፣ ፍቅርህ በሁኔታዬ ስለማይለወጥ፣ በድክመቴም ስለማይቀንስ፣ በስኬቴም ስለማይጨምር እወድሃለው።
✨ማንም ያላንከባለለው ሸክሜን ስለወሰድክልኝ፣ ኃጢአቴን ይቅር ስላልከኝ፣ ተስፋ በሌለኝ ጊዜ እንኳን ተስፋ ስለሆንከኝ፣ በጨለማው መንገዴ ብርሃን ስለሆንከኝ እወድሃለው።
✨ማቄን ቀደድ ደስታን ስላስታጠከኝ፣ ፈጥረህ ስላልተውከኝ፣ ሰልችቼህ ጀርባ ስላልሰጠኸኝ፣ በደስታዬ ብቻ ሳይሆን በሀዘኔም ከእኔ ጋር ስለምትሆን፣ በመ…
❤18🙏3
Signed @doni
31 Jul 2026, 05:24 UTC905 views16 reactionsread 12 August 2026 ኢየሱስ ክርስቶስ
✨በቃላት ብቻ የማይገለጽ የክብር ጌታ ነው።
✨ እርሱ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ ሰውን በማዳን ፍቅሩን የገለጠ፣ የትሕትና አርአያ፣ የሰላም አለቃ እና የዘላለም ሕይወት ምንጭ ነው።
✨እርሱ የሚጮኸውን ይሰማል፣
✨ የሚያለቅሰውን ያጽናናል፣
✨የወደቀውን ያነሣል፣
✨የተጎዳውን ይፈውሳል፣
✨የጠፋውን ይፈልጋል።
✨ፍቅሩ ወሰን የለውም፣ ምሕረቱ መጨረሻ የለውም፣ ታማኝነቱም ለዘላለም ይኖራል። አሜን
✍በአዶኒ
Telegram👉 t.me/adonigospel
Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ
❤11🙏5
Signed @doni
30 Jul 2026, 15:25 UTC924 views9 reactionsread 12 August 2026 Photo
❌ማስጠንቀቂያ
ይህ ከላይ የምታዩት ስክሪን ሹት ቻናሉ ላይ ያሉ ወዳጆች የላኩልኝ ሲሆን ለእኔ ምንም አይነት ማስታወቂያ መለቀቁን አያሳየኝም። ይህ ሊንክ ከኔ ፍቃድና ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ የተለጠፈ ነውና በማን? እንዴት? እንደተለቀቀም የማላውቅ መሆኑን እንድትገነዘቡና ሊንኩን ባለመክፈት ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስል የጥንቃቄ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
መልዕክቱ ከእኔ መስሏቸው ሰዎች እንዳይታለሉ በዚህ ዙሪያ ላይ መፍትሄውን ልትሰጡኝ የምትችሉ ባለሙያዎች ካላችሁ ትብብራችሁን የምሻ መሆኑን በፍቅር እጠይቃለሁ።
ከታላቅ ፍቅር ጋር
አዶኒ
👍6🙏3
Signed @doni
30 Jul 2026, 13:59 UTC714 views16 reactionsread 12 August 2026 በሕይወታችሁ ማንንም አታቃሉ
ዘፍ 16:4
✨ የሰው ልጅ በየጊዜው የተለያዩ ጠባዮችን ያበቅላል። አወቅነው ስትሉ ጭራሽ አለማወቃችሁ ይገባችኋል። ወደ ልቡ የአመታት ጉዞ ብታደርጉ ጫፉን የማትደርሱበት ስምጥ ሸለቆ ማለት የሰው ልጅ ነው። አውቃችሁ አትጨርሱትም። ሰው ለሰው ብቻ ሳይሆን ለአምላኩም አስቸጋሪ የማይያዝ የማይጨበጥ ፍጡር ነው።
✨አጋር የሳራ ባርያ ናት። የአጋር ሀላፊነት ቤት ውስጥ የሚያስፈልገውን የጉልበት ስራ መስራት እንጂ የመውለድ የማግባት ሀላፊነት የለባትም። ድንገት ግን ከሀላፊነቷ ውጪ ሌላ ነገር ገጠማት ጌታዋ አብርሃም ወደ እርሷ ገብቶ ልጅ ፀነሰች። ይህ ለአጋር ድንገተኛ ነገር ነው። ይህች አጋ…
❤11🙏5
Signed @doni
27 Jul 2026, 17:31 UTC836 views30 reactionsread 12 August 2026 🙏
ባለፉት አምስትና ስድስት ወራቶች ውስጥ እንደተለመደው በተለያየ ችግር ውስጥ ሆናችሁ በጸሎትም፣ በሃሳብም እንድረዳችሁ በውስጥ መስመር የተለያዩ መልዕክቶችን ልካችሁልኝ ምላሽ ያልሰጠኋችሁ ሁላችሁም ከልብ የሆነ ይቅርታን እጠይቃችኋለሁ። ከነበርኩበት ጥልቅ ኃዘን የተነሳ ዝም ማለትን ስለመረጥኩ እኔም ከነበርኩበት ስሜት እስከወጣ ነውና በዚህ መሃል ተቀይማችሁ ብሎክም ያደረጋችሁኝ ሁላችሁን ከልብ ይቅርታ እላችኋለሁ። እግዚአብሔር ባስለመደን ጸጋ እድሜ ጨምሮ ብዙ ለመማማር ያብቃን። በጸሎታችሁ አስቡኝ እወዳችኋለሁ። የክርስቶስ ፍቅር ይብዛላችሁ።❤️
አዶኒ
❤26🔥4
Signed @doni
27 Jul 2026, 15:21 UTC≈1,100 views13 reactionsread 12 August 2026 ክርስቶስን የመምሰል ህይወት
✨ክርስትና እድገት ያለው ሕይወት ነው። ክርስቲያን የሚያድገው ወደጎን አይደለም፣ በቁመትም አይደለም! እድገቱ ክርስቶስን ወደ መምሰል ነው። የተጠራነው እገሌንና እገሊትን መስለን እንድንኖር ሳይሆን ክርስቶስን መስለን እንድንኖር ነው። የክርስቲያን የሕይወት ግብ ሰማይ መድረስ ብቻ ሳይሆን በምድርም ሳለን የክርስቶስን መልክ ተላብሰን መኖር ነው። ብዙዎች ክርስትናን በስም፣ በስርዓት ወይም በውጫዊ ምልክት ለመለካት ይፈልጋሉ። ይህ የፈሪሳውያን ጠባይ እንጂ የክርስትና ሕይወት ገጽታ አይደለም። ጌታ ኢየሱስ የሚፈልገው የተለወጠ ልብን እንጂ አስመሳይን አይደለም።
"ክርስቶስን መከተል በቃል ብቻ አይደለም። ሕይወታችንም የእርሱን …
❤13
Signed @doni
25 Jul 2026, 07:45 UTC955 views16 reactionsread 12 August 2026 ኢየሱስ ለእኔ ያላረክልኝ ምን አለ
ከማህፀን ያየኸኝ፤ በዓላማህ ያኖርከኝ፤ እንደ ዳዊት ከተረሳሁበት ያነሳኸኝ፤ ጸጋህን እንደ ልብስ አለበስኽኝ ጌታ ኢየሱስ ተመስገንልኝ።
እጆቼን ባዶ አልተውከኝም፣ ልቤን ተስፋ አልነሳኸውም፣ ከቀን ወደ ቀን ታማኝነትህን አሳየኸኝ፣ አዕምሮዬን ጠበከው፣ ከብዙ ጉድ አወጣኸኝ ጌታ ኢየሱስ ተመስገንልኝ።
ያልታየኝን አንተ አየኸው፣ ያልቻልኩትን አንተ ሰራኸው፣ የተሰበረውን ልቤን አከምከው፣ የተዘጉ ደጆችን ከፈትክልኝ፣ ያልጠየኩትን ሰጠኸኝ፣ ያላሰብኩትን ጨመርክልኝ፣ በረከትህ ቀድሞ ደረሰልኝ፣ ምህረትህም በፊቴ ሄደ ጌታ ኢየሱስ ተመስገንልኝ።
የሰጠኸኝን ስቆጥር መጨረሻው አይታወቅ…
❤16
Signed @doni
24 Jul 2026, 17:24 UTC928 views12 reactionsread 12 August 2026 ኢየሱስ
✨የታረድከው ጌታ፤ በክብር በምስጋና፣ በይባቤ ያረከው ጌታ ታማኝነትህ ያልጎደለብን፣ ሁኔታዎች ሲገለባበጡ ፀንተህ የቆምክልን፣ ድል መንሻችን ኢየሱስ ሆይ ተመስገን።
✨ኢየሱስ ሆይ እንወድሃለን፤ ኢየሱስ ሆይ እናከብርሃለን፤
ኢየሱስ ሆይ እንሰግድልሃለን፤ ኢየሱስ ሆይ ከፍ ከፍ እናደርግሃለን። ለማንነትህ እንጂ ለስጦታህ አንዘምርም፤ ለፍቅርህ እንጂ ለበረከትህ ብቻ አንሰግድም። አንተ ወድቀህ ያነሳኸን ጀግና፤ ሞተህ ያኖርከን ወዳጅ፤ ከናንተ በፊት እኔን ያስቀድመኝ ብለህ የሞት ፅዋ የጠጣህልን ኢየሱስ ሆይ እንወድሃለን።
✨አንተ በረሃችንን የምታረካ፤ ጥማችን የምትቆርጥ ውሃችን፤ ለሊቱን ስንጓዝ የእሳት አምድ …
❤11🔥1
Signed @doni
22 Jul 2026, 05:43 UTC≈1,100 views29 reactionsread 12 August 2026 እግዚአብሔር ሁን ያለውን ጉም አይጋርደውም፤ ድምጽን በድምጽ የሚሽር የበላይ ዳኛ ነው። እርሱ ያለው ከአድማስ እስከ አድማስ ያለከልካይ ይሆናል። ተመስገን
Telegram👉 t.me/adonigospel
Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
❤25🙏4
Signed @doni
Showing the 12 most recent of 21 posts we hold for @adonigospel. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.