6 Aug 2026, 19:26 UTC25 viewsread 6 August 2026 “እናት ልጇን ዳዴ ስታስለምደው አስቀድማ እጁን ትይዘዋለች፡፡ እንዲሄድም ታደፋፍረዋለች፡፡ ትንሽ መሄድ ሲጀምር ትለቀዋለች፡፡ ትልቀቀው እንጂ ልቧ ሐሳቧ ሁሉ ግን ከልጇ ጋር ነው፡፡ ሊወድቅ ሲል ፈጠን ብላ ትደግፈዋለች፡፡
እግዚአብሔርም ለእኛ ለልጆቹ እንደዚህ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእኛ እይታ ክፉ በሚመስሉ ሁኔታዎች እንድናልፍ ይፈቅዳል፤ ወርቅ ወርቅነቱ ይታወቅ ዘንድ በእሳት እንዲያልፍ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደዚያች እናት በቅርብ ርቀት ሆኖ ይከታተለናል፡፡ ሐሳቡ ልቡ ሁሉ ከእኛ አይለይም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ነገር ግን መልሶ ያነሣናል፡፡ እዚህ ጋር መጠንቀቅ ያለብን ቢኖር በዚሁ የልምምድ ጊዜ ሰይጣን ያንን ሁናቴ ተጠቅሞ በክፉ ዐይን እን…
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
4 Aug 2026, 07:23 UTC75 views4 reactionsread 6 August 2026 ወዳጆችዬ ዛሬ በዚህ ማለዳ፡ ሳስበው በጣም የገረመኝንና፡ እምነትን የጨመረልኝ ነገር ጀባ ልበላችሁማ ፡ አይገርማችሁም እግዚአብሔር አባታችን ነው፡ በጣም ብዙ ጊዜ ፡ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፡ እሱን/ሷን፡ እንደ ልጄ ነው ማየው/ያት ሲባል ሰምቻለው፡ ምን መስማት ብቻ፡ ተብያለው አሁንም ጭምር እባላለሁኝ፡ እሱን እኮ ከልጆቼ አልለየውም ፡ እሷን እኮም ይባላል። እውነት ለመናገር እንደዚህ በሚሉኝ ሰዎች በጣም ነው ደስ የሚለኝ፡ ደስታ ብቻ ሳይሆን እኔ እራሴ ፡ እገሌ/ሊት እንደ እናቴ ነው የማያት፡ እንደ አባቴ ነው። ስለ አስታውሳለው። አይገርማችሁም እግዚአብሔር ግን እንደ አባት አይደለም ለእኛ አባት ነው እንጂ እኛም ለሱ እንደ ልጅ አይደለንም፡ ልጆች እንጂ ።…
🥰3❤1
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
10 Jul 2026, 19:30 UTC206 views2 reactionsread 6 August 2026 ፨ የበረሀው ጉዞ ፨
ለሀገሩ ባዳ ነኝ ፤ የምሄድበትንም የምደርስበትንም አላውቅም ግን በአሰሩኝ ሰዎች ምሪት እንደ ጥላ እከተላቸዋለሁ። በውስጤ ብዙ ሀሳብ ይተራመሳል፤ አንዱን ጀምሬ ሳልጨርስ በሌላ ሀሳብ ይደፈርሳል። ውስጤ አልቅስ አልቅስ ይለዋል እንባ ግን ከየት ይምጣ እንዲሁ በበረሃው ቃጠሎ እየነደድኩኝ ውስጤን ለምን በሚል ምሬት እየናጥኩኝ፤ በረሃውን አስቀናሁት በእሳቱ ወላፈን ሊገርፈኝ ሲነሳ እሳተ ገሞራ ሆኜ አገኘኝ።
``እርሱም በመገረም ምን ሆነህ ነው? ከእኔ የባስከው? ምን ቢገጥምህ ነው? በአፍላነትህ እንዲህ የነደድከው?``
ብሎ ሊያጫውተኝ የውስጤን እሳት አጥፍቶ በእርሱ ጭው ባለው በረኻ እንዳውተነትን ፈለገ። እኔ ግን ዝም አልኩት…
🔥2
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
29 Jun 2026, 16:35 UTC263 views5 reactionsread 6 August 2026 "እግዚአብሔር ቤት ምን አመጣቹ?። ማጣታቹ ወይስ መዳናቹ?።ማለዳ ተነስታቹ የእግዚአብሔርን ቤት ስትረግጡ (ሞቲቫቹ)ምንድን ነዉ?። የምታቁትን ኑሮአቹ በአገልጋይ እከሌ እንዲነገራቹ ነዉ?። ንገሩኝ እስቲ ከዘላለም የሞት መርገም የድህነት መርገም ይበልጣል እንዴ?።ታዉቃላቹ እግዚአብሔርን ለምነነዉ አደለም የዘላለም ህይወት የሰጠን እንዲሁ በነፃ ነዉ። ዛሬ ልላቹ የመጣሁት አንድ ነገር ነዉ።እግዚአብሔር ሙላታቹንም ጉድለታቹንም ያቀዋል። እራሱ እግዚአብሔርን ስትፈልጉት ጉድለታቹን ይሞላል።ነገር ግን የሌላቹን እና የምትፈልጉትን እያሰባቹ የምትመጡ ከሆነ የምትፈልጉት ነገር እናንተን እንዳይወስድበት ሲል አይሰጣቹም።እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ያዉቃል። እኔ እንደ ጎረቤቴ ል…
❤5
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
22 Jun 2026, 03:04 UTC456 views4 reactionsread 6 August 2026 ✍✍✍ የአብ ፍቃድ
““በሰማይ ያለውን ያባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም።”
— ማቴዎስ 7፥21 (አዲሱ መ.ት)
👉 አብ አባት ሆይ በሰማይ ያለውን ፍቃድህን እንድፈፅም ማስተዋልን ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁኝ።
👉 ይህ ፍቃድህም በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኜ የዘለዓለም ህይወት እንዳገኝ ነው።
“የአባቴ ፈቃድ ወልድን አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።””
— ዮሐንስ 6፥40 (አዲሱ መ.ት)
👉 አባቴ ሆይ ፍቃድህን ሳልፈፅም በከንቱ ስምህን ከመጥራት አድነኸኛል።
👉 ነገር ግን አባቴ ሆይ ዛሬም በዚህ ዘመን ፍቃድህን ሳይፈፅሙ ስምህን የሚጠሩ …
🔥3❤1
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
19 Jun 2026, 04:04 UTC409 views5 reactionsread 6 August 2026 👉👉ቀዳሚ መሆን👈👈
👉 ማግኔት ብረትን እንደሚስብ እንዲሁም በህይወታችን የእግዚአብሔር መልካምነት እንዲበዛ አስቀድመን የተካፈልነውን መልካምነት ለሌሎች ልናካፍል ግድ ይለናል።
👉 የብዙዎቻችን ክርስትና ህይወት ተከታይ በመሆን እንጂ ቀዳሚ በመሆን አይደለም።
👉 ከሌሎች ተቀብሎ መስጠትን እንጂ አስቀድሞ መስጠት እንደ ሽንፈት ቆጥረነዋል።
👉 ለይቅርታ የዘገየ ልብ ነው ያለን፤ ከሌላው ወገን ካልመጣ ከእኛ እንዲወጣ አንፈልግም።
👉 አግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ቀዳሚ ሆኖ ወደ እኛ እንደመጣ፤ እኛም ወደ ሌሎች ህይወት ቀዳሚ ሆነን የተካፈልነውን ህይወት ልናንፀባርቅ ግድ ይለናል።
“ሌሎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያት…
❤5
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
16 Jun 2026, 03:32 UTC450 views5 reactionsread 6 August 2026 ሁለቱ ሸክሞች
የመጀመሪያው ጠንክሮ በራስህ ላይ የተሻለ ሰው ለመሆን የመስራት ሸክም ነው፤ ሁለተኛው የፀፀት ሸክም ነው። ጠንክሮ መስራት ምናልባት 1 ኪሎ ግራም ቢመዝን ነው፤ ፀፀት ግን 100 ኪሎ ግራም ተሸክሞ እንደመዞር ነው። የቱ እንደሚሻልህ አንተው ምረጥ!
ሁላችንም አሁን ካለንበት የተሻለ ህይወት እንፈልጋለን፤ በከንቱ ቀንህ ያለፈ ጊዜ "በቃ አይኔ እያየ ምንም ሳልሰራበት ቀኑ አለፈ ,ሳልፀልይ አለፈ?" ቃሉን ሳላነብ አለፈ?,ሳልቀየር ቀናቶች አለፉ? ..እያልክ ራስህን የወቀስክበትን ጊዜ አስብ፤
አየህ ወዳጄ ጠንክረህ እራስህ ላይ የምትሰራው ና የምትለወጠው ከፍ እንድትል ብቻ አይደለም ሁሌም ከራስህ ጋር እንድትስማማ ነው በኋላ ፀፀቱን አትችለውም።
⁹…
❤2💯2🙏1
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
12 Jun 2026, 03:27 UTC342 views5 reactionsread 6 August 2026 2ነገ 8:7-15
“አዛሄልም፣ “ለመሆኑ እንደ ውሻ የሚቈጠር አገልጋይህ ይህን ጀብዱ መፈጸም እንዴት ይችላል?” አለ። ኤልሳዕም መልሶ፣ “መቼም አንተ በሶርያ ላይ እንደምትነግሥ እግዚአብሔር አሳይቶኛል” አለው።”
— 2ኛ ነገሥት 8፥13 (አዲሱ መ.ት)
✍ የብዙ ሰዎች ቅንነት ዘመን እስኪመጣ ነው።
✍ በቁሳዊ ወይም በዚህ ዓለም ንዋይ የተያዘ ሰው ማግኘት የሚፈልገውን እስኪያገኝ ድረስ ትሁት መምሰል ይችልበታል።
✍ ብዙ ሰው ባጎረስኩ ተነከስኩ ይላሉ። ነገር ግን እንዲነከሱ ያደረጋቸው ነገር ያጎረሱት ነገር መሆኑን ይዘነጋሉ።
✍ በጥቅም የተያዘ ነገር ሁሉ የተሻለ ጥቅም ሲገኝ የቀደመውን ጥቅም ለመርገጥ አይከብደውም፤ ለምን ጠቃሚ ሳይሆን ተጠቃሚ ተደርጎ ስለተ…
❤🔥5
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
7 Jun 2026, 05:43 UTC308 views6 reactionsread 6 August 2026 2 ነገስት 1:1-8
በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ እግዚአብሔር ትኩረታችንን እና ፍለጋችንን እርሱ ላይ ስናደርግ ደስ ይለዋል። ማንም ወላጅ ልጁ ሌላ ቤት ሲቀለዋጥ ደስ እንደማይለው ሁሉ እግዚአብሔር ደግሞ ልጆቹ ሌላ ቦታ ሲቀላውጡ ደስ አይለውም። ለምን? እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነው።
ስለዚህ ምንም ይሁን ምንም አይናችንን እርሱ ላይ እንድናደርግ በፀጋው ይደግፈን። ከእርሱ ላይ ትኩረታችንን የሳበ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከህይወት መንገዳችን ላይ ይነሳ።
https://t.me/akiyaneh
❤5🔥1
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
2 Jun 2026, 05:45 UTC492 views6 reactionsread 6 August 2026 ሰው ውሎውን ይመስላል፨
ዛሬን ከማን ጋር ለማሳለፍ እቅድ ይዘናል?
✍ በየትኛውም መውጣት መግባታችን ላይ ከኢየሱስ ጋር የምንቆይበትን እግዚአብሔር በመንፈሱ ሀይል በጥበቡ ይቃኘን።
✍ የንግግራችን ጅምር እና ድምድም
እግዚአብሔር አብ እኛን የወደደበት
እግዚአብሔር ወልድ ለእኛ ራሱን የሰጠበት
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይህን እውነት ለእኛ የገለጠበትን ምንጫወትበት ይሁንልን።
“ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤
ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ተገነዘቡ።”
— ሐዋርያት 4፥13 (አዲሱ መ.ት)
https://t.me/akiyaneh
👏5❤1
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
31 May 2026, 20:06 UTC418 views3 reactionsread 6 August 2026 🤌🤌ያልከኝ ሲመስለኝ✍✍
ልቤ ይጨነቃል ግራም ይጋባል
እርብሽብሽ ለማለትም ይቃጠዋል
እኔን ዝም ያልከኝ ሲመስለኝ
ለማስረዳት አቅም ሲያጥረኝ
አንደበቴ መናገር እየፈለገ ሲዘጋ
ሰውን እየናፈቀ ብቸኝነትን ሲያወጋ
በምን አቅም ነው በምን ችሎታ
ካንተ በቀር ይሄን ችግር የሚፈታ
ከራሴ በላይ እኔን የምትረዳኝ
ምላሴን አልፈህ ልቤን ምታደምጠኝ
እኮ አንተን ልጠይቅህ ስለኔ ጉዳይ
እኔን ገልጠህ ስታውቀኝ ከራሴ በላይ
እኮ ንገረኝ አባ መፍትሄውን አስጨብጠኝ
በዝምታ መራመድ ዙሪያዬን አስፈራኝ
ይሁና አንተ ካልክ
ዝምታን ከመረጥክ
ነገሩ ባይገባኝም ሳይ የአንተን ዝምታ
ማየት ልጀምር ሆኜ ባንተ ቦታ
ለምን አንተ መልካምና በጎ ነህ
ጨለምተኝነት አንተ ዘንድ የሌለህ
ይሁን አንተ…
🔥2❤1
Signed አኪያ ይናገር@akiyaneh
አኪያ ይናገር ✍✍✍ pinned «🤝🤝ይቅርታ🤝🤝 ✍ ይቅርታ ነገን ብሩህ ያደርጋል እንጂ ያለፈ ትላንትን አይቀይርም። ✍ ደስተኛነት ምርጫ ነው፤ ይህም የሚገኘው በይቅርታ ህይወት ነወ። ✍ የእውነት ማፍቀርን ከፈለግን፤ ይቅር ማለትን የግድ መልመድ አለብን። አለበለዚያ ፍቅራችን የግብዝነት ነው። ✍ ይቅርታ የጤንነት መለኪያ ነው። ከይቅርታ የራቀ ሰው በቀላሉ ለተለያዩ በሽታዎች ተጠቂ ይሆናል። ✍ ይቅር አለማለት እኔ መርዙን ልጠጣ እርሱ ይሙት…»
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @akiyaneh. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.