6 Aug 2026, 10:00 UTC121 views3 reactionsread 7 August 2026 “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !
በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!
የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤
ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረ…
❤3
31 Jul 2026, 08:50 UTC356 views4 reactionsread 7 August 2026 "የሰውን ጉድና ድክመት ይዞ መሮጥ የባሪያ ነፍስ ምልክት ነው። ሐሜተኛ ሰው የራሱን ቆሻሻ ቤት ረስተው የሌሎችን መስኮት በመጥረግ ይጠመዳል። የሌሎችን ስም የሚያጠፋ ሰው፣ የራሱን ክብር ከሰማይ ወደ ታች እየወረወረ መሆኑን ልቡ አያውቅም። ንጹሕ ሕሊና ያለው ሰው የሰውን ድክመት በዝምታ ይሸፍናል እንጂ በገበያ ውሎ አያወራም።"
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ፣
የተቀደሰ መልካም ቀን ይሁንልን 🙏🥰
https://t.me/ardssu
❤4
29 Jul 2026, 07:50 UTC254 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @eotcgssu21Photo
Photo, posted without a caption
29 Jul 2026, 07:50 UTC219 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @eotcgssu21
4ኛው የአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር ተከናወነ።
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት (ሐምሌ 22 / 11 / 2018 ዓ.ም)
4ኛው የአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና የምርቃት መርሐ ግብር በትላንትናው ዕለት በቅድስ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ተከናወናውኗል። በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዌሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰሜን ሸዋ እና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳ…
29 Jul 2026, 04:38 UTC298 viewsread 7 August 2026 Photo
እንኳን ለገናናው መልአክ ቅዱስ ኡራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
https://t.me/ardssu
29 Jul 2026, 03:54 UTC298 viewsread 7 August 2026 Photo
ምክረ አበው
ከወድሞች አንዱ ወደ አረጋዊ መጣና " አባ ፣ ደካማ ነኝና ጸልዩልኝ " አለው፡፡ አረጋዊም እንዲህ አለው " በሸተኛን ይቀባ ዘንድ በእጁ ቅባት የሚይዝና ሌላውን የሚቀባ ሰው እርሱም ደኀና ሆኖ ይቀባል፡፡
እንዲሁም እኛም ለሌላው ስንጸልይ ለራሳችን መድኃኒትና ፍስሐ ይሆነናል፡፡
ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይና እርስ በርሳችን በጸሎት ልንተሳሰብ ይገባናል፤ ሐዋርያው " ትድኑ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ ጸልዩ " ብሎ እንዳዘዘን፡፡
#ከበረሐውያን_ሕይወትና_አንደበት
https://t.me/ardssu
27 Jul 2026, 04:39 UTC751 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
አስቸኳይ የእርዳታ ተማፅዕኖ😭😭
"እነሆ አገልጋይን ማዳን አገልግሎትን ማዳን ነው"
🙏🙏🙏አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ🙏🙏🙏
በመላው ዓለም የምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ከታች በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን ዘማሪት ሰርክ አዲስ ኃ/መስቀል (ዘማሪት ሐና) ትባላለች። በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴደራል ፍኖተ ወንጌል ስንበት ት/ቤት አገልጋይ ስትሆን ባጋጠማት ከፍተኛ የልብ ሕመም ምክንያት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል ስታደርግ የቆየች ቢሆንም አሁን ላይ ህክምናው ከአቅም በላይ በመሆኑ ምክንያት ለቀዶ ጥገና ከ 1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ስለተጠየቅን ይህችን ዘማሪት እህታችንን በማሳከም ወደ አገልግሎት እንመልሳት ስንል …
🙏3
26 Jul 2026, 04:24 UTC341 viewsread 7 August 2026 [ሐምሌ 19 የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ በዓል]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ዶሮዳስ ታደሰ
❖ሐምሌ 19 ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።
❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃ…
26 Jul 2026, 04:22 UTC278 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
26 Jul 2026, 04:21 UTC314 viewsread 7 August 2026 "በመናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቅዱስነታቸው በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ አባታዊ መልእክት አስተላላፉ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ…
24 Jul 2026, 02:55 UTC974 views1 reactionsread 7 August 2026 *<<ወዳጄ ሆይ>>*
_«ስለ *ምሕረትና ፍቅር* »_
_«ልብህ ለፍጥረታት ሁሉ የሚራራ ይሁን፤ ልብህ ሰፊ ይሁን።_
ለአራዊት፣ ለአእዋፍ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ—እንዲያውም ለአሳዳጆችህና ጠላቶችህ እንኳ ሳይቀር በፍቅርና በዕንባ ጸልይ።
ቅዱስ ልብ ማለት ስለ ፍጥረት ሁሉ እያሰበ በፍቅር የሚቃጠል ልብ ነው።
ኃጢአተኛውን ስታይ አትናቀው፤ ይልቁንም 'እኔ ከእሱ የባስኩ ነኝ' ብለህ አስብ።
እግዚአብሔር ለዓለም ያለው ፍቅር ከባሕር አሸዋ ይበልጣል።
የሰው ልጅ ኃጢአት ወደ እግዚአብሔር ምሕረት ሲጣል፣ ወደ ባሕር እንደተወረወረ አንድ ጠብታ ውኃ ነው—ይጠፋል! ስለዚህ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ አትደቅ፤ ምሕረቱ ከኃጢአትህ በላይ ነውና።»
*ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ💙🦋…
👍1
23 Jul 2026, 03:06 UTC349 views3 reactionsread 7 August 2026 #ኦርቶዶክሳዊ_ሕይወትን_መኖር
#ለደከመች_ነፍስ_መመሪያ
#ለደከመች_ነፍስ_መመሪያ_4
ነፍስ ሆይ፣ በእምነት ኑሪ!
እምነት የማይታየውን የምታይበት አይንሽ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን የምትዳስሽበት እጅሽ ነው። እምነት ግን እንዲያው በደፈናው እግዚአብሔር አለ ማለት ሳይሆን አንቺን ራስሽን እንደሚወድሽ፣ እንደሚያድንሽ ማወቅ ነው። ስለዚህ ፈተና ሲገጥምሽ የፈተናውን ኃይልና መጠን አትመዝኚ፤ ይልቅስ ለዘመናት የታመነውን አምላክ አስበሽ ጽኑ ሁኚ። ጨቅላ በእናቱ እቅፍ እንደሚተማመን፣ በየቀኑ በፈጣሪሽ ተማመኚ።
#ለደከመች_ነፍስ_መመሪያ_5
ነፍስ ሆይ፣ በእግዚአብሔር ሰላም ተሞይ!
የዓለም ሰላም በምድራዊ ኃያላን ጉልበት ይደፈርሳል። እግዚአብሔር የሌለበት አእምሮ …
❤2👍1
Showing the 12 most recent of 12 posts we hold for @ardssu. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.