8 Sept 2026, 07:01 UTC29 views3 reactionsread 9 September 2026 تدبّرها…💭💭
﴿يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا﴾
<< በዚያ ቀን ምድር ዜናዋን ትናገራለች >>
አላህን ያመለክክበት የተገዛህበት እያንዳንዱ ቦታ ለአንተ ምስክር ይሆናል፤ አላህን ያልታዘዝክበትና ኃጢአት የሠራህበት እያንዳንዱ ቦታ ደግሞ በአንተ ላይ ምስክር ይሆንብሀል። ስለዚህ የሚመሰክሩልሆን አብዛ፤ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ አንድ ሱጁድ አድርግ፣ በምትጎበኘው ከተማ ሁሉ ሰደቃ ስጥ፣ በምትደርስበት መንደር ሁሉ ወደ መስጂድ ሄደህ በግልህ አላህን አምልክ።ይህች ምድር🌍 አፈርና ጠጠር ብቻ አይደለችም፤ በዚያ ቀን ከሚኖሩ ዋና ዋና ምስክሮች አንዷም ናት
@ayshamesjidlibrary
@ayshamesjidlibrary
❤3
7 Sept 2026, 05:59 UTC44 views5 reactionsread 9 September 2026 تدبّرها…💭💭
﴿قَالَ يَا بُنَيَّ لَا تَقْصُصْ رُؤْيَاكَ عَلَىٰ إِخْوَتِكَ فَيَكِيدُوا لَكَ كَيْدًا﴾
<< እርሱም(ያዕቁብ ዐ.ሰ) ‘ልጄ ሆይ! ሕልምህን ለወንድሞችህ አትንገራቸው በአንተ ላይ ሴራ እንዳያሴሩ እፈራለሁ’ አለ >>
ሁሉም ሰዎች ፊት አላህ የሰጠህን በረከት ሁሉ ማውራት አይጠበቅብህም።
አንዳንድ ልቦች በቅናት የተጠቁ ናቸው፤ አንዳንድ ዓይኖችም በምቀኝነት የተሞሉ ናቸው። ስለዚህ አላህ የሰጠህን በረከት በምስጋናና በጥበብ ጠብቅ፤ ካልሆነም ቢያንስ ለሁሉም አትንገረው።
🌿 ምቀኛ ሰው የሚያረካው የበረከቱ መወገድ ነው። በቀድሞውም ዘመን የዩሱፍ ወንድሞች እርሱ በሕልሙ ስላየው ነገር ቀኑበት።
እንግዲህ…
👍5
6 Sept 2026, 17:25 UTC51 views5 reactionsread 9 September 2026 ክፍል 19 – የምሽጉ መልስ
የኦቶማን ሠራዊት በምሽጉ ፊት ሰፈረ።
በማግስቱ ጠዋት ሱልጣን መሐመድ አል-ፋቲሕ አንድ መልእክተኛ ጠራ።
"ወደ ምሽጉ ሂድ።"
"ሰላምን አስቀድመን እንመርጣለን ብለህ ንገራቸው።"
መልእክተኛው ነጭ ባንዲራ ይዞ ወደ ምሽጉ ሄደ።
የምሽጉ ጠባቂዎች በሩን በጥንቃቄ ከፈቱ።
መልእክቱ ለአዛዡ ቀረበ።
አዛዡ በጥሞና አነበበው።
ከዚያም እንዲህ አለ፦
"እኛ ምሽጋችንን አሳልፈን አንሰጥም።"
"እንከላከላለን።"
መልእክተኛው ወደ ሱልጣኑ ተመለሰ።
መሐመድ አል-ፋቲሕ መልሱን ሰምቶ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ።
ከዚያም እንዲህ አለ፦
"እንግዲህ ከበባው ይጀምር።"
ነገር ግን አንድ ትእዛዝ ጨመረ።
"ማንም ሰው ያለ ትእዛዝ ጥቃት አይክፈት።"
"ሥርዓት ከድፍረት…
👍3❤1🔥1
6 Sept 2026, 11:18 UTC51 views3 reactionsread 9 September 2026 Forwarded from @SharpSwords1
ሱብሀነሏህ እንዴት የሚደንቅ የፅናት ታሪክ ነው
------
በ1977 በኢትዮጵያ በነበረው ድርቅ ምክኒያት የተፈጠረውን ርሃብ ተከትሎ የተከሰተውን ይህን አሳዛኝ ታሪክ ሌላ ሰው ቢያወራው ኖሮ ለማመን ይከብድ ነበር ነገር ግን ይህን ታሪክ የሚናገሩት ኩዌይታዊ ሼኸ ዶ/ር አብዱራህማን አስ-ሰሚጥ ናቸውና ለማመን እንገደዳለን አላህ ይማራቸውና በአፍሪካ አህጉር ከ11ሚሊዮን በላይ ሠዎችን ያሰለሙ ሸይኽ ናቸው
ታሪኩ እንዲህ ነው በ1977 አንድ የክርሰትያን በጎ አድራጊ ማህበር ከሰሜን አሜሪካ እርዳታ ለመሰጠት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣና በቀጥታ ድርቅና ርሃብ ወደ ተከሰተበት ገጠር ሂደው እርዳታ መሰጠት ይጀምራሉ ከዚያም የመስጂድ ኢማም የሆኑ አንድ ትልቅ ሠው እርዳታ ለመቀበ…
😢3
6 Sept 2026, 07:08 UTC47 views4 reactionsread 9 September 2026 تدبّرها…💭💭
﴿وَلُعِنُوا بِمَا قَالُوا ﴾
<< በተናገሩትም ምክንያት ተረገሙ >>
ቃላትን በጭራሽ አታቅልል አንዲት ቃል ወደ ጀነት ልትመራህ ትችላለች ሌላዋ ደግሞ ወደ እሳት ልትከትህ ትችላለች!
ነቢዩﷺ ምላሳቸውን እያመለከቱ ለሙዓዝ «ይህንን ተቆጣጠር!» አሉት። ሙዓዝም «የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በምናገረው ነገር ሁሉ እንጠየቃለንን?🗣️» ብሎ ጠየቃቸው።
እርሳቸውም «እናት ትጣህና ያ ሙዓዝ!(እንዴት ይህን አታውቅም ማለታቸው ነው) ሰዎችን በፊታቸው ደፍቶ ወደ እሳት የሚያስገባቸው ከአንደበታቸው የሚወጣው እንጂ ሌላ ምንድን ነው!» አሉት።
@ayshamesjidlibrary
@ayshamesjidlibrary
👍4
5 Sept 2026, 05:29 UTC60 views4 reactionsread 9 September 2026 تدبّرها…💭💭
﴿ إِن تَمْسَسْكُمْ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ وَإِن تُصِبْكُمْ سَيِّئَةٌ يَفْرَحُوا بِهَا﴾
<< መልካም ነገር ቢያጋጥማችሁ ያሳዝናቸዋል፤ ክፉ ነገርም ቢያጋጥማችሁ በእሱ ይደሰታሉ።>>
🌿 የሌሎችን መከራና ውድቀት አይቶ መደሰት የሙናፊቆች ባህሪ ነው።
ስለዚህ ለራሳችሁ መልካምን እንደምትወዱት ለሌሎችም ውደዱላቸው፤ ጉዳትም በራሳችሁ ቢደርስ እንደምትጠሉት በእነርሱ ላይ ሲደርስ ጥሉት
ሱሪ አስ-ሱቅጢ رحمه الله በዘመኑ ከታላላቅ ዓሊሞች አንዱ እንዲህ ይል ነበር፦
«ለሠላሳ ዓመታት ያህል ‘አልሐምዱሊላህ’ ብዬ በተናገርኩት ነገር ምሕረትን እየጠየቅሁ ነው።»
«እንዴት?» ተብለው ሲጠየቁም እንዲህ ሲሉ …
👍4
4 Sept 2026, 17:31 UTC64 viewsread 9 September 2026 File
File, posted without a caption
4 Sept 2026, 17:27 UTC70 views6 reactionsread 9 September 2026 የማጠልሸት ስልት (Demonization)
ከመረጣ እና መተው (ማስቀረት) በተጨማሪ ልሂቃኑ የኢትዮጵያን ታሪክ የቃኙበት ስልት ማጠልሸት (Demonization) ነው። ይኸውም አንድን የታሪክ ወቅት፣ ክስተት ወይም ታሪካዊ ስብዕና መጥፎ አድርጎ መሳል እንደማለት ነው። ለምሳሌ ጉልህ የሆነ የማጠልሸት (Demonization) ዒላማ ሰለባ የሆነው የኢትዮጵያ የታሪክ ወቅት ከ18ኛው እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ያለው ዘመን ነው። ይህን የታሪክ ወቅት ልሂቃኑ «ዘመነ መሳፍንት» የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። የዘመኑ ዓይነተኛ መገለጫ ተደርጎ በስፋት የሚተረከውም ኢትዮጵያ ከሌላው ዘመን በተለየ ሁኔታ በመሳፍንት አገዛዝ ተከፋፍላ በማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት…
❤6
4 Sept 2026, 04:54 UTC73 views4 reactionsread 9 September 2026 تدبّرها…💭💭
﴿ فَبِمَا رَحْمَةٍ مِّنَ اللَّهِ لِنتَ لَهُمْ ۖ وَلَوْ كُنتَ فَظًّا غَلِيظَ الْقَلْبِ لَانفَضُّوا مِنْ حَوْلِكَ ﴾
«ከአላህ በሆነው እዝነት ለነርሱ ለሰለስክላቸው (ለዘበክላቸው)። ደረቅ አነጋገር ያለው እና ልበ-ደንዳና በሆንክ ኖሮ ከዙርያህ በተበተኑ ነበር።»
ምንም እንኳን አንተ በእውነት ላይ ሌላው በስህተት ላይ ቢሆን፤ አንተ በቅን መንገድ ላይ ሌላው በጥመት ላይ ቢሆንም መልካም ሥነ-ምግባር ቅድሚያ ይሰጠዋል! 🤍
አንድ ሌባ የማሊክ ኢብን ዲናር رحمه اللهን ቤት ገባ ነገር ግን የሚወስደው ምንም ነገር አላገኘም።
ማሊክም ጠርተውት፦“ከዱንያ የሚወሰድ ምንም ነገር …
👍4
3 Sept 2026, 06:51 UTC83 views3 reactionsread 9 September 2026 تدبّرها…💭💭
﴿وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ ﴾
<< ከእርሱም(ከኑህ ዐ.ሰ ) ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም >>
እርሱ የመልእክተኞች ሁሉ አባት የሚባለው ነቢዩላህ ኑሕለይሂ ሰላም ነው።
ለሺህ ሃምሳ ዓመት ሲቀረው(950 ዓመት) ያህል ሕዝቦቹን ወደ እውነት ጠራ፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ጥቂት ሰዎች እንጂ አላመኑም።
🌿እኛ የምንጠየቀው ስለ ጥረታችን እንጂ ስለ ውጤቱ አይደለም፤ ስለተጓዝንበት መንገድ እንጂ ስለ መድረሳችን አይደለም።
በሐዲስም እንደተገለጸው:-በትንሣኤ ቀን ነቢያት ከሕዝቦቻቸው ጋር ይመጣሉ፤ነቢይ ይመጣል ከእርሱ ጋር ግን አንድም ተከታይ ያላመነለት! አው ከነቢያትም መካከል ማንም ያላመነበት ነቢይ ነበር።
ኢማሙ አው…
🔥3
2 Sept 2026, 20:24 UTC83 views7 reactionsread 9 September 2026 አሰላሙዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ
የአይሻ መስጂድ ቤተ-መፅሀፍት📚
የአይሻ መስጂድ ቤተ-መፅሀፍት ለሰዎች መጽሐፍ የማከራየት ሥራ ከጀመረ 3 ዓመታት አልፈዋል። አሁን ያለን መጽሐፍ ከአንባቢው አንፃር በቂ ባለመሆኑ፣ ከማህበረሰብ ዘንድ ያሉ ጠቃሚ መጽሐፍትን ለላይብረሪው እያሰባሰብን እንገኛለን::
እናንተጋ ያለ አንድ መጽሐፍ ለእናንተ በቤት የተቀመጠ ሊሆን ይችላል፤ ለሌላ ሰው ግን ለኸይር ስራ በር ሊከፍት ይችላል።
ያላችሁን መጽሐፍ አበርክቱ፤ እውቀትን አስፋፉ፤መልዕክቱንም ለሁሉም share በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።
قال رسول الله ﷺ:
«مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ»
“ወደ መ…
👍7
2 Sept 2026, 18:25 UTC85 views6 reactionsread 9 September 2026 ክፍል 17 – የሰርቢያ ዘመቻ
1454
የቁስጥንጥንያን ድል ካገኘ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ሱልጣን መሐመድ አል-ፋቲሕ ትኩረቱን ወደ ሰርቢያ አዞረ። በዚያን ጊዜ የሰርቢያ ገዥ የነበረው ደስፖት ጂዮርጂ ብራንኮቪች ከሃንጋሪ ጋር ግንኙነቱን እያጠናከረ ነበር። ይህም ለኦቶማን መንግሥት አሳሳቢ ሁኔታ ነበር።
በ1454 የጸደይ ወቅት ሱልጣን መሐመድ አል-ፋቲሕ ትልቅ ሠራዊት ይዞ ወደ ሰርቢያ ዘመተ።
የኦቶማን ሠራዊት ወደ ሰርቢያ እየገባ ሲሄድ በመጀመሪያ ሲቪሪቼሂሳር (ኦስትርቪትሳ) የተባለውን ምሽግ ያዘ። ከዚያም ኦሞልሂሳር የተባለውን ሌላ ምሽግ ተቆጣጠረ።
የሰርቢያ ገዥ ጂዮርጂ ብራንኮቪች ኦቶማኖችን ለመቋቋም ከስመደሬቮ የፈረሰኞች ጦር ላከ። ነገር ግን የሰርቢያ …
🔥6
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ayshamesjidlibrary. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.