29 Jul 2026, 21:22 UTC188 views9 reactionsread 6 August 2026 እስከ ምን ላስብ?
--🔘---
ከበርናባስ በቀለ
"ሰው የገዛ ሕይወቱ ሸማኔ ነው፣ መዘወሪያው ደግሞ ሃሳብ ነው።" ይላሉ የሃሳብ ኃይል አወዳሾቹ። እነዚሁ አስቦ አደሮች "ሃሳብህን ከተቆጣጠርህ የሕይወትህን ፍጻሜ ትቆጣጠራለህ" ብለውም ያምናሉ። አንዲት ጉዳይ ቢጤ እያሰብሁ ነውና እስከ ምን ድረስ ላስብ የሚለውን እያሰብኩኝ ነው።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
🥰5❤3👏1
27 Jul 2026, 09:37 UTC544 views14 reactionsread 6 August 2026 የ'ኔ ተራራ! ⛰️
--🔘--
ከበርናባስ በቀለ
አንደኛ ለመሆን አልሠራም። ጎበዝ ለመባል አልፈጋም። ተጽዕኖ ለመፍጠርም አልባትልም። ምድሩን ለማስደመም ድንጋይ አልፈነቅልም። ትላንት በሳቁብኝ በተራዬ ልስቅባቸው ጠብ እርግፍ አልልም። ታዋቂ መሆንም አልፈልግም። ዘመናዊ ለመሆን አላንቧችርም። ከማን አንሼ በሚል ተምች ቢሂል ናላዬ አይዞርም። እጄ ላይ ያለው ነገር ወደ ሰዎች እንዲደርስ ብዬ አልሠራም። እግዚአብሔርንም ላገለግለው ብዬም ያላቅሜ ከመለኮት እሰጥ እገባ ውስጥ አልገባም።
እኔ መሆን የምፈለገው "ራሴን"፤ ማሸነፍም የምሻው ራሴን። ለመግዛትም ጦሜ ምጸልየው ራሴን። ተጽዕኖ መፍጠሩንም የምፈልገው በራሴው። ይህ ራሴ አመጸኛ ዓለም ነውና ትግሌ ከርሱ …
❤5🔥5👏2👍1😢1
22 Jul 2026, 10:40 UTC409 views8 reactionsread 6 August 2026 ሕያዊቷ ማኅበር-- ሕያውነት ከራቃት ዓለሙማ ተስፋ የለውም። እርሷ ለዓለም እውነተኛ ህሊና ናት። የርሷ ህሊና ከጎደፈ ዓለሙማ በጨለማ ይዋጣል።
👍6❤2
22 Jul 2026, 10:38 UTC369 views7 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @metsihafuyinager
ክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እቅፍ ወጥቶ ለቤዝዖቱ ሥራ መጣ፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ማንነትና ሥራ የድነት ወንጌል ወጣ፣ ከወንጌሉ ውስጥ መሲሓዊቷ ማኅበር (ቤተ ክርስቲያን) ወጣች፣ ከቤተ ክርስቲያን (በኩል) ሕያውነት ወደ ዓለሙ ይወጣል።
------------
Join Us! & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess
❤5👍2
21 Jul 2026, 11:15 UTC461 views19 reactionsread 6 August 2026 በሥራዬ ጉዳይ ወጥቼ ቦሌ Morning Star አካባቢ ያለ ካፌ ውስጥ ነኝ። አጠገቤ አንድ ቆፍጠን ያለ ወጣት አለና ይደወልለታል። ስልኩን አንስቶ ወዳጁን "እ.. እየጠበኩህ ነው አትመጣም?" ይለዋል።
"እየመጣሁ ነው ግን አንተ መኪና ይዘሃል አይደል? የእኔን መኪና ትቼው ልምጣ?" ብሎ ይጠይቀዋል። አጠገቤ ያለው ጎረምሳ "የኔዋ መኪና ፓርኪንግ ውስጥ ናትና ያንተን ይዘህ ና እና ሮጥ ብለን እንመለሳለን" ይለዋል።
ከዚያም ያኛው ወዳጁ "የእኔ መኪና ላንተ አትሆንም፣ እባክህን ያንተን አውጣ ይለዋል" ኋላም ይኸኛው (አጠገቤ ያለው) ሰው "አንተ ምን ሆነህ ነው? እኔ በሳይክልም መኼድ እችላለሁ እኮ፣ ደግሞ vits እኮ ትልቅ መኪና ነው!" ይለዋል፣ ያኛው እንደተሳ…
😁12🤣5👍1💩1
20 Jul 2026, 07:28 UTC375 views12 reactionsread 6 August 2026 ካረጁ አይበጁ!
---🔘----
ከበርናባስ በቀለ
ዓለም ዋንጫዋን አስረክባለች። ሌጀንዶቹን እነ ክርስቲያኖንና ሊዮኔል ሜሲን ሸኝታ ላሚን Yamalንና መሰሎቹን (አዲሱን ትውልድ) ማንቆለጳጰሱን ይዛዋለች። "እኔ የሚያስፈልገኝ አዲስ ትውልድና አሠራር ነው!" (ካረጁ ለእኔም አይበጁ!) የምትል ይመስላል።
እርሷ እኮ ጎበዝ ናት ማንን መቼ መጠቀም እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች። "በእነ እንትና ዋጋ መክፈል የመጣ ለውጥ" እያለች ያለፈውን ዘመን legacy ስታሞካሽና ከበሮ ስትደልቅላቸው አዳዲሶቿን አትቀርብርም። "አዳዲሶች አሉኝ እኮ" እያለች ቡቃያዎቿን ወደ ምድሩ ፊት ገጽ ታወጣለች።
የቀዳሚዎቹን አሠራርና legacy ለማስቀጠል አዲሱን ትውልድ የሚሰዋ ማ…
❤12
19 Jul 2026, 03:30 UTC380 views23 reactionsread 6 August 2026 እግዚአብሔር ቸሩ!
---🔘----
ከበርናባስ በቀለ
አሁን በጨለማው ክምር ላይ ትንሽዬ የብርሃን ተስፋ እያቆጠቆጠች ነው። ቀጥሎ ያለውን ዐረፍተ ነገር ስጽፍ ደግሞ ጨለማው አድራሻውን ሊለቅ ይመስላል። ይኸው ብርሃን! ይኸው ወገግታ። ታዲያ ጎህ ሲቀድ ሊነጋ ሲያቅላላ የብርሃኑ ጮራ ሲፈነጥቅ ጨለማው ደግሞ ሲፈረጥጥ ያዩ ዓይኖቼ የእግዚአብሔርን በጎነት የሚተርክ ዘጋቢ ፊልም እያዩ ይመስል ትዕንግርት ውስጥ ናቸው። እግዚአብሔር ቸሩ! "ብርሃን ይሁን አለ፣ ብርሃንም ሆነ" የተባለለት እርሱ ዛሬም ለሊቶቼን የሚያነጋልኝ እውነተኛ ብርሃን ነው።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @bar…
❤14🙏5👍2🔥1🤗1
15 Jul 2026, 14:35 UTC524 views26 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @metsihafuyinager
ሰማዩ ዝም ያለ ሲመስለንና ነገረ ዓለሙ ግራ ገብቶን ስንዋትት እግዚአብሔር የነፍሳችን ማረፊያ ነው። እርሱ ልባችንን በሕያውነቱ የሚያሞቅ የደህንነታችን ምንጭ ነው። የሞት ሸለቆ በሚመስል ዝቅታ እያለፍን ያለን ሲመስለን እርሱ የዘላለሙ ከፍታችን ነው። ስለ ነገያችን አስበን እርግጠኝነት ሲጎድለን ዓለማትን በመግቦቱ የያዘው እርሱ መድን ዋስትናችን ነው።
-------
Join Us!
@metsihafuyinager
@metsihafuyinager
-------
በውስጥ፦ @adfontess
❤18🔥5🥰3
13 Jul 2026, 20:14 UTC580 views27 reactionsread 6 August 2026 የኢሉሚናቲ መንፈስ!
---🔘-----
ከበርናባስ በቀለ
ከሰሞኑ ሚስቴና ልጄ ለጋራ ተልዕኳችን ኼዴዋልና ሳምንቱን ላጤ ነኝ። ምግብ ሠርቼ መብላት እችላለሁ፣ ኧረ ማብላትም እችላለሁ። ግን እነርሱ ኼደው ብቻዬን ስበላ የከዳኋቸው ይመስለኝና አይዋጥልኝም። ላስበውም አልፈልግም። እናም ሚስቲቱ "ትክክል አይደለህም፣ እንደውም ስመለስ ሽምግልና መቀመጥ አለብን!" ብላኛለች። አንቺ ሰላም ተመለሺ እንጂ አያሳስብሽ ብዬአታለሁ። እሺ፣ እኔ ምን ላድርግ? እርሷ በሌለችበት ቤት ምግብ መብላት በታማኝነት ጉድለት የሚያስከስስ የሚመስለኝን ነገር ምን ላድርግ? ደግሞ እኮ ላለፉት 7 አመታት እንደ ትንሽ ልጅ እንዲሁ ነው ሳስቸግራት የኖርሁት (ለነገሩ ለእናቴ አሁንም ልጅ ነ…
😁21❤6
12 Jul 2026, 07:08 UTC685 views32 reactionsread 6 August 2026 ሞትም ሰልጥኗል!
---🔘----
ከበርናባስ በቀለ
የቅርብ ወዳጄ ናት። እጅግ ትጉህና የአቋም ሴት በመሆኗ በዙሪያዋ ባሉ ዘንድ ተከብራ የምትኖር እንስት እንደሆነች ስነግራችሁ እኔም ከተጽዕኖዋ ያልተረፍሁ መሆኔን ሳልሸሽጋችሁ ነው። ከምትኖርበት ከተማ ወደ ሌላኛው የክፍ'ላገር ከተማ በጉዳይ ተጉዛ ነበር (እርሱንም ከሳምንታት በፊት አሳውቃኛለች)፣ የዚያ ከተማ ተልዕኮዋን ጨርሳ ወደ እናት ከተማዋ ልትመለስ ሁለት ቀን ሲቀራት "ወንድምሽ አርፏልና ቶሎ ድረሺ" የሚል የስልክ ጥሪ ደረሳት። 😥
"ባርኒ ወንድሜን አጣሁት እኮ" ብላ text አደረገችልኝ። መደወል ፈራሁ! ስልኬን አስሬ እያነሳሁ መለስሁ። እንደምንም ግን ደወልኩላት። መቼ? እንዴት ምን ሆኖ? …
❤22😢8👍1👏1
7 Jul 2026, 06:52 UTC626 views15 reactionsread 6 August 2026 "የዓለም ዋንጫ!" ⚽
----▣------
ከበርናባስ በቀለ
ከሚከተሉት መካከል ስለ ዓለም ዋንጫ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው? (ታዲያ በፍጥነትና በትክክል የመለሱ የመጀመሪያዎቹ 5 ሰዎች ይሸለሙ ዘንድ ወስነናል)።
-----------
ሀ) የእግር ኳስ ስፖርቱ ተወንጫፊ ከዋክብት በዓለሙ ገጽ ፊት እየተወረወሩ የሚያበሩበት የትዕይንት መድረክ።
ለ) ዓለም የዋንጫ ጨዋታ አዘጋጅታ ልጆቿን እያጫወተች ነው፤ ልጅ ጨዋታ ይወድ የለ?
ሐ) ዓለም ዋንጫ አላት፣ በብርቱ ለሮጠላት ትሰጠዋለች።
መ) አንተ ደግሞ፣ እስቲ አታወዛግበን።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabas…
🤣12😁2😱1
30 Jun 2026, 06:03 UTC738 views15 reactionsread 6 August 2026 ⚠️
------
ከበርናባስ በቀለ
ሩጫ በዝቶብኝ ጉልበቴ ዝሎ እና አዕምሮዬ ረጅም እረፍት የሚያስፈልገው አይነት አኳኻን ውስጥ ስሆን--- ከአካላዊ እረፍቱ በላይ ለምን በዚህ ልክ ተወጣጠርሁ? ጊዜዬን እየበሉት ያሉት ነገሮች ድንበር ዘለል፣ መርኾ ተኮርና እግዚአብሔር ለአጽናፈ ዓለሙ ካለው እቅድ ጋር የሚቆራኙ ናቸው? ለሚል ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ ማግኘቱ የበለጠ ያሳርፈኛል። ከዚያም ወደ physical & mental እረፍቴ አቀናለሁ።
ባለፉት ጊዜያት ብዙውን ጊዜዬን የበላብኝ አፍርሶ መገንባት እንደሆነ ስላስተዋልሁ አሁን አዲስ ግንባታዎችን ሁሉ ማቆም አለብኝ። ባይሆን የተገነቡ ግኑኝነቶችንም ሆነ እንቅስቃሴዎቼን እየመረመርሁ በየቅድሚያቸው ማሰለፍ ይኖ…
👏9❤5👍1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @barnabasism. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.