3 Aug 2026, 03:32 UTC78 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
በዚያ እጅግ አስፈሪና ጨለማ በሆነው የቂያማ ቀን፣ አማኞች ብርሃንን ይሰጣሉ:: ይህ ብርሃን እዚህ ምድር ላይ በምናደርገው ዉዱእ ፣ ሶላት እና መልካም ስራዎች አማካኝነት በልባችን ውስጥ የገነባነው ብርሃን ውጤት ነው።
ያን ቀን በገደልና በጨለማ የታጠረውን የሲራጥ ድልድይ ለመሻገር ብቸኛው መመሪያችንና መንገዳችን ይህ ብርሃን ነው።
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!✨
#ቁርዐን
Telegram
https://t.me/beTibeb_In
Facebook
http://fb.me/61589258491936
❤4
31 Jul 2026, 03:00 UTC136 views7 reactionsread 6 August 2026 Photo
በዱንያ ላይ ወደ ጁምዓ ሶላት ቀድመን ለመድረስ የምናደርገው ጥረት፣ ያን ቀን ከአላህ ዙፋን አጠገብ ለመቀመጥና ውብ ፊቱን መጀመሪያ ለማየት ቅድሚያ ያሰጠናል::
በጀነት ውስጥ ከሁሉ የላቀውን ስጦታ እናገኝ ዘንድ ቀድመን እንገስግስ!
ያማረ ጁምዓ ይሁንላችሁ✨
#ጁምዐ
#ሰለዋት
#ሀዲስ
Telegram
https://t.me/beTibeb_In
Facebook
http://fb.me/61589258491936
❤7
27 Jul 2026, 03:05 UTC167 views8 reactionsread 6 August 2026 Photo
ሕይወት የተቆጠሩ ቀናት ስብስብ ናት!
እያንዳንዷ የምትጠልቅ ጀምበር የሕይወታችንን አማና የምናስረክብበትና ወደ ጌታችን የምንመለስበት ጊዜ መቃረቡን የምታበስር ማስጠንቀቂያ ናት። እያንዳንዱን ቀን በመልካም ተግባር፣ በአላህ ትውስታና ለሰዎች በሚጠቅም ሥራ መሙላት የነገው ስኬታችን ዋስትና ነው። ዛሬ የምናባክነው እያንዳንዱ ሰዓት ተመልሶ የማይመጣ የሕይወታችን ክፍል በመሆኑ፣ ነገ ጸጸት እንዳይገጥመን ዛሬን እንደ መጨረሻ ዕድላችን አድርገን እንጠቀምበት!
"ዛሬ ለጌታዬ ምን አበረከትኩ? ከዕድሜዬ ላይ በሄደው ቀን ውስጥ ምን ዓይነት የአኼራ ስንቅ አከማቸሁ?"
መልካም ሳምንት✨
#ጊዜ
Telegram
https://t.me/beTibeb_In
Facebook
http://…
❤8
24 Jul 2026, 04:12 UTC158 views6 reactionsread 6 August 2026 Photo
«አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፤ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ።»
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَعَلَىٰ آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَعَلَىٰ آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَعَلَىٰ آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَعَلَىٰ آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.
ያማረ ጁምዓ ይሁንላችሁ✨
#ጁምዐ…
❤6
22 Jul 2026, 09:10 UTC152 views5 reactionsread 6 August 2026 Photo
በ'በጥበብ' ኢስላማዊ ማህበር የተዘጋጀው ልዩ የክረምት መርሃ-ግብር በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል!
ትምህርቱም:-
●ከኢስላማዊ እውቀት ባሻገር የተለያዩ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን፣
●እንደ ካሊግራፊ (የአረብኛ ስነ-ጽሁፍ) እና ኢፖክሲ ያሉ የፈጠራ ብቃትን የሚያሳድጉ ጥበቦችን፣
●ለዘመኑ የሚያስፈልጉ የኮምፒውተር እና የቴክኒክ ስልጠናዎችን ያካተተ ነው::
📍አድራሻ: ቄራ: ዲታሞ ህንፃ 3ተኛ ፎቅ
Telegram
https://t.me/beTibeb_In
Facebook
http://fb.me/61589258491936
❤5
20 Jul 2026, 10:31 UTC188 views10 reactionsread 6 August 2026 Photo
እያንዳንዱ ሙስሊም ራሱንና ማህበረሰቡን ለመጥቀም እንዲሁም በምድር ላይ የአላህን ቃል የበላይ ለማድረግ በዕውቀት መበልጸግ ይኖርበታል። እውቀት የሌለው ሰው አላህን በትክክል ሊያመልክና ከጥመት ራሱን ሊጠብቅም አይችልም::
እውቀት የህይወት ዘመን ጉዞ ነው!
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!✨
#ሀዲስ
#እውቀት
Telegram
https://t.me/beTibeb_In
Facebook
http://fb.me/61589258491936
❤10
17 Jul 2026, 03:05 UTC214 views9 reactionsread 6 August 2026 Photo
አንድ ሙስሊም በምድር ላይ ሲኖር ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሚተርፍ፣ ችግርን የሚጋራና ለሰዎች እፎይታን የሚሰጥ እንዲሆን ይጠበቅበታል።
አላህ ዘንድ በደረጃ ከፍ ለማለትና የእርሱን ውዴታ ለማግኘት በአንድ ሙስሊም ወንድምህ ወይም እህትህ ልብ ውስጥ ደስታን መፍጠር፣ ከላያቸው ላይ ጭንቀትን ማንሳት፣ ዕዳ ያለበትን ሰው መርዳት ወይም የተራበን ማብላት ትልቅ ቦታ ያላቸው የአምልኮ ዘርፎች ናቸው።
የተዋበ ጁምዓን ተመኘን✨
اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
#ጁምዐ
#ሰለዋት
#ሀዲስ
Telegram
https://t.me/beTibeb_In
Facebook
http://fb.me/61589258491936
❤9
13 Jul 2026, 02:48 UTC243 views8 reactionsread 6 August 2026 Photo
«አንብብ! በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው (ጌታህ ስም)»
የሰው ልጅ የታሪክ አቅጣጫ የተቀየረባት፣ ከሰማይ ወደ ምድር የወረደች የመጀመሪያዋ የመልእክት ብርሃን..."አንብብ"!
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ✨
#ቁርዐን
#እውቀት
Telegram
https://t.me/beTibeb_In
Facebook
http://fb.me/61589258491936
❤8
10 Jul 2026, 04:41 UTC245 views8 reactionsread 6 August 2026 Photo
እውነተኛ እውቀት የሰውን ልጅ ወደ ኩራት ሳይሆን ወደ መንፈሳዊ መሸበርና ወደ ጥልቅ ፍቅር ይመራዋል፤ ምክንያቱም የጌታውን ታላቅነት በትክክል የተረዳ ልብ በፊቱ ለመቆም ይርዳል፣ ትዕዛዙንም ላለመጣስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል።
እውነተኛ አዋቂ (ዓሊም) ማለት ብዙ መረጃዎችን የሰበሰበ ወይም መጽሐፍትን በቃል የሸመደደ ብቻ ሳይሆን፣ ያገኘው እውቀት በልቡ ውስጥ አላህን የመፍራትና የመገዛት ስሜትን የፈጠረለት ሰው ነው።
አላህ ዘንድ ትልቁ አዋቂ በትምህርት ደረጃው የገፋው ሳይሆን፣ አላህን ይበልጥ የሚያውቀውና የሚፈራው ነው።
ያማረ ጁምዓ ይሁንላችሁ✨
اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
#ጁምዐ
#ሰለዋት
#ቁ…
❤8
7 Jul 2026, 06:55 UTC211 views8 reactionsread 6 August 2026 Photo
ከዛሬ 839 ዓመታት በፊት፣ እ.ኤ.አ. አሁን ባለንበት በወርሃ July ፣ በታላቁ መሪ በሳላሁዲን አል-አዩቢ (አላህ ይዘንላቸው) የሚመራው የሙስሊሞች ጦር በመስቀላውያን ጦር ላይ በሂጢን ስፍራ ታላቅ ድልን ተቀዳጀ። ይህ ድል ለ88 ዓመታት በመስቀላውያን እጅ ወድቃ የነበረችውን ከተማ (አል-ቁድስን) ነፃ ለማውጣት መንገድ የጠረገ ታሪካዊ ክስተት ነበር።
በወቅቱ መስቀላውያኑ በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል እያደረሱ ነበር። ሳላሁዲን ሙስሊሞችን በማስተባበርና ጥበብ የተሞላበት የጦር ስልት በመንደፍ ወደ ሂጢን አመራ። በጦርነቱ ወቅት ሳላሁዲን መስቀላውያኑ ውሃ
ከሚገኝባቸው ስፍራዎች እንዳይደርሱ በመከልከል በሐሩርና በጥማት እንዲዳከሙ አደረጋቸው። ይህም የጠላ…
❤8
6 Jul 2026, 11:46 UTC193 views8 reactionsread 6 August 2026 Photo
አላህ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ካስተላለፋቸው ትዕዛዞች መካከል፣ እንዲጨምርላቸው እንዲጠይቁ የታዘዙት ብቸኛው ነገር "እውቀት" ነው። እውቀት የሰው ልጅ በዚህችም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ለሚያገኘው ስኬት መሰረት ነው። እውቀት የልብ ብርሃን ነው፤ ትክክለኛውን ከስህተት ለመለየት እና ወደ አላህ የሚወስደውን ቀጥተኛ መንገድ ለመከተል ዋነኛ መሳሪያ ነው።
በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ የምናደርገውን ጠቃሚ እውቀት እየቀሰምን ወደ አላህ ይበልጥ የሚያቃርበን ልዩ የክረምት መሰናዶ በ'በጥበብ' ኢስላማዊ ማህበር ተዘጋጅቶላቹሃል::
ምዝገባ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ!
📞 0904438888
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ✨
#ቁርዐን
#እውቀት
Telegram
https://t…
❤8
5 Jul 2026, 15:36 UTC233 views6 reactionsread 6 August 2026 Photo
ክረምትን በ"በጥበብ"
በጥበብ ኢስላማዊ ማህበር በክረምቱ ወር ያዘጋጀላቹ ትምህርት በምን ይለያል?
●ከኢስላማዊ እውቀት ባሻገር የተለያዩ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን፣
●እንደ ካሊግራፊ (የአረብኛ ስነ-ጽሁፍ) እና ኢፖክሲ ያሉ የፈጠራ ብቃትን የሚያሳድጉ ጥበቦችን፣
●ለዘመኑ የሚያስፈልጉ የኮምፒውተር እና የቴክኒክ ስልጠናዎችን ያካተተ በመሆኑ ነው::
ምዝገባው ሳይጠናቀቅ ፈጥነው ይመዝገቡ!
ለመመዝገብ ከታች ያለውን ጎግል ፎርም ይጠቀሙ👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfkvCyhMcx-02UCL7iuw1CAUt7FyA3PL4sMCO9jVltZTjqBJw/viewform?usp=publish-editor
ለበለጠ መረጃ
📞 09044388…
❤6
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @beTibeb_In. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.