25 Aug 2026, 05:28 UTC814 views9 reactionsread 28 August 2026 ✥✥✥ ቅዱሳን መላእክት ✥✥✥
➛ መላእክት የሚለው ብዙ ቁጥርን አመላካች ሲሆን በነጠላ መልኣክ ይሆናል እንደ የአገባቡም የተለያዩ ሁለት
ትርጉሞችን ሊሰጥ ይችላል፡፡
መልአክ :-
1. ተመልአከ ከሚለው የግእዝ ግስ ሲወጣ አለቃ ሆነ በሚለው መሪ፣ አስተዳዳሪ፣ አዛዥ፣ አለቃ የሚለውን
ይገልፃል፡፡ (ዮሐ.፫÷ ፩) ኒቆዲሞስን « መልኣኮሙ ለአይሁድ» ይለዋል የአይሁዳውያን አለቃ ሲል፡፡ የጌታ ወዳጅ ባለራዕይ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊም በተደጋጋሚ ራዕዩን ለሰባቱ የቤተ ክርስቲያን መልአክ እያለ ሲገልጽ በዚህ ትርጉም የገባ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ (ራዕ ፩፥፳)
2. ለአከ ከሚለው ግስ ሲነሳ ላከ የሚለውን ስለሚያስገኝ መልእክተኛ ጠባቂ ተብሎ ይፈታል፡፡
➛ መላእክት…
❤9
Signed Mekuria Tesfaye
21 Aug 2026, 13:48 UTC≈1,650 views18 reactionsread 28 August 2026 Photo
✥ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ ✥
✥ ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ ✥
. ነሐሴ 16 የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ ሃገር ወደ ሃገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ዕረፍተ ሞቴን በዕረፍተ ዕለትሽ አድርጊልኝ ይህም ባይሆን በዚህ አሕዛብ ሃገር ተቀብሬ አልቅር ከሚያምኑት ሃገር እቀበር ዘንድ ፍልሰተ ሥጋዬን ከፍልሰተ ሥጋሽ ዕለት አገናኝልኝ ብሎ ተማጽኗት ነበር።
. ይህም የዕለቱ አርኬ « ሰላም ለጊዮርጊስ ተውላጠ ፃማሁ ወሕማሙ። እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። በፍልሰትኪ ድንግል ዘተቶስሓ ፍልስተ ዐፅሙ። እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ ኀቤሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ። » ተብሎ ተገልጿል ልመና…
❤17👍1
Signed Mekuria Tesfaye
21 Aug 2026, 07:07 UTC≈1,380 views8 reactionsread 28 August 2026 Photo
✥✥✥ ሰማይ ተገረመች ✥✥✥
➛ አስቀድሞ አባቷ ዳዊት « አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት» (መዝ 131፥8) ብሎ እንደዘመረው ድንግል እንደልጇ ባለትንሣኤ ከሙታን ተለይታ በልጅዋ ሥልጣን ተነስታ "ሰማይ ዳግሚት" ወደ ሰማይ ጉዞ አደረገች። ሰማይም ተገረመች አማናዊቷን ሰማይ ማርያምን ስላየች።
አስቀድሞ ሰማይ በምስራቅ መስኮቷ ወጥታ በምዕራብ መስኮቷ በመግባት በምትመላለሰው በብርሃኗ ፀሓይ ትመካ ነበረ፤ ከፀሓይ ይልቅ ሰባት እጅ የምታበራን እመኣምላክን ወደርሷ ስትመጣ ዓይታ ግን ግርማዋን አድንቃ « ይህች ሰማይ እንደዚህ ካበራች ከርሷም የተገኘው ፀሓየ ጽድቅማ እንደምን መንክር ነው ብላም ተደመመች »።
ጌታን መሸከም የማይችለው አቅሟንም አስ…
❤8
Signed Mekuria Tesfaye
19 Aug 2026, 14:23 UTC≈1,440 views3 reactionsread 28 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤3
Signed Mekuria Tesfaye
19 Aug 2026, 14:23 UTC≈1,310 views13 reactionsread 28 August 2026 "እመብርሃንን ክጄ እንጀራ ከምበላ እስከ ልጆቼ በሃይማኖቴ ጸንቼ በረሃብ ብሞት ይሻለኛል"
በሀገሩና በኃይማኖቱ ድርድር የማያዉቀዉ የጎንደር ሕዝብ እያለማ በረሀብ አይሞቱም!
አቶ ቻሌ ኃብቴ እና ወይዘሮ በቃቢል አባተ የሚባሉ ሁለቱም እጅግ የሚዋደዱና በጉልበታቸው ሠርተው የሚተዳደሩ ኦርቶዶክሳውያን ባልና ሚስት ነበሩ። በ2015 ዓ.ም የካቲት 16 ምሽት ላይ ቀን ዘንብሎባቸው የቤቱ ምሰሶ የሆነው ባልየው ባልታሰበ አደጋ ስድስት ሰዎች ተሰብስበው ጭን*ቅላቱን ደበ*ደቡትና በሞ*ትና በሕይወት መካከል ጥለውት ሄዱ በዚህም ክፉኛ ተጎድቶ ፓራ*ላይዝድ ሆኖ እጅ እግሩ ተሳስሮ አንደበቱ ተዘግቶ እየተኮላተፈ ለዓመታት በሕክምና ቆየ።
ከብዙ ድካም በኋላ ቀስ ብሎ መራመድ ሲ…
❤9👍4
Signed Mekuria Tesfaye
18 Aug 2026, 08:15 UTC≈2,230 views19 reactionsread 28 August 2026 👉 ደብረ ታቦር የተባለው ጌታ ክብሩን የገለጠበት ስፍራ ደብረ ታቦር ስለሆነ በዚሁ በዓሉ ስያሜውን አግኝቷል፡፡
👉 ቡሔ ይባላል ፡- ቡሄ ብርሃን ማለት ነው በደብረታቦር ቧ ብሎ የተገለጠውን የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል፤ የልብሱንም እንደ ነጭ በረዶ ጸዓዳ መሆን ያስረዳል፡፡
• አንድም፡- ቡሔ ማለት መላጣ (ገላጣ) ማለት ነው፡፡
ይኸውም በበዓሉ ዋዜማ ልጆች ‹‹ ቡሔ በሉ፤ ቡሔ መጣ ፣ ያ መላጣ፣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ›› ይላሉ እዚህ ላይ ቡሄ ያለው ዳቦውን ነው፡፡
• አንድም፡- ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንደሚባል ወቅቱ በሃገራችን የጸዓተ ክረምት ዋዜማ ስለሆነ የክረምቱ አፈናው ተወግዶ /ተጋምሶ/ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት…
❤19
Signed Mekuria Tesfaye
18 Aug 2026, 08:15 UTC≈1,490 views7 reactionsread 28 August 2026 ✥✥✥ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌስሑ✥✥✥
(መዝ.88÷12)
👉 በዚህ ርዕስ ሥር
1. በዓሉ የሚከበርበትን ምክንያት/
ከሐዋርያት ሦስቱ ሐዋርያት ብቻ መመረጣቸው ፤ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስ መገለጣቸው ስለምን ነው?
2. ደብረታቦር የተመረጠበት ምክንያትና ምሳሌነቱ
3. የበዓሉ መጠሪያ ስሞች (ደብረ ታቦር / ቡሄ/ ቡሔ መባሉ ስለምንድ ነው?)
4. ችቦ የመብራቱ ፣ ሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት እንመለከታለን፡፡
✔ 1. ይህ በዓል ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን የሚከበረው ጌታችን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅነቱን ያስመሰከረበት፣ ጌትነቱን እና ክብሩን የገለጠበት በመሆኑ ነው፡፡ (ማቴ.17÷1 ማር.9÷2 ሉቃ.9÷28 2ጴጥ.1÷…
👍4❤3
Signed Mekuria Tesfaye
12 Aug 2026, 17:41 UTC≈2,520 views27 reactionsread 28 August 2026 ✥✥✥ ፅንሰታ ለእግዝእትነ ✥✥✥
👉 ነሐሴ 7 እመቤታችን የተፀነሰችበት ነው። ቤተክርስቲያናችንም ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከልም ነው።
👉 አባ ሕርያቆስ ስለ እመቤታችን የመፀነስዋን ነገር ሲናገር ድንግል ሆይ በልተው ጠጥተው ጾር ሲጸናባቸው በሚያደርጉት ግንኙነት የተፀነሽ ኣይደለሽም ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ነው ብዙ ተባዙ ባለው ፈቃድ በሩካቤ ዘበሕግ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ በማለት ያደንቃል!
👉 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም " የእግዚኣብሔር ልጆች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ማኅበር እንግዲህ ይህችን ንጽሕት ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናድንቃቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግል የተባረከችይቱም ፍሬ የተፈራችባት የሩካቢያቸው ንጽሕት …
❤18🙏6🥰3
Signed Mekuria Tesfaye
8 Aug 2026, 08:10 UTC≈3,040 views17 reactionsread 28 August 2026 #፯ቱ_ዕለታት_ለእመቤታችን_ምሳሌዋ_ናቸው
➕ በዕለተ እሁድ ትመሰላለች
- በዕለተ እሁድ አሥራወ ፍጥረታት አራቱ ባሕርያት ተገኝተዋል። ከሷም ዘኮነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ እንዲለው አሥራወ ፍጥረት ጌታ ተገኝቷልና ።
➕ በዕለተ ሠኑይ ትመሰላለች
- በዕለተ ሠኑይ ከዚህ ምድር እስከ ብሩህ ሰማይ መልቶ የነበረውን ውሀ ከሶስት ከፍሎታል፣አንዱን እጅ ከላይ ሰቅሎታል ሐኖስ ነው አንዱን እጅ በዙሪያው ወስኖታል አንዱን እጅ አጽንቶ የብርሃን ማኅደር አርጎታል። ዕለቲቱ የሱዋ ጠፈር ከሱዋ የነሣው ሥጋ ብርሃን የጌታ ምሳሌ።
➕ በዕለተ ሠሉስ ትመስላለች
- በዕለተ ሠሉስ ለታብቀል ምድር ሐመልማለ ሣዕር ዘይዘራዕ በበዘርዑ ወበበዘመዱ በበአርአያሁ ወበአምሳሊሁ ባለ…
❤14🙏3
Signed Mekuria Tesfaye
6 Aug 2026, 15:15 UTC≈2,170 views10 reactionsread 28 August 2026 ✥✥✥ የጾመ ፍልሰታ ምንባባት ✥✥✥
➕ ነሐሴ 1
- አመ ዓሚሩ ለነሐሴ አቦሊ ሰማዕት ፣ ወተዝካረ ሐና እመ እግዝእትነ፣ ወዮሴፍ ወኒቆዲሞስ እለ ገነዝዎ ለእግዚእነ፡፡
☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ
- 1ኛጢሞ. 5፥1፦ ሊቃናተ ኢታመጉዕ፡፡
- 1ዮሐ. 5፥1፦ ኵሉ ዘየአምን ከመ ኢየሱስ ውእቱ መሢሕ
ሐዋ.ሥራ 5 ፥ 26:- ወእምዝ ሖረ መጋቤ ምኵራብ፡፡
- ምስባክ መዝ 118፥47-48 ፦ ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኀፈር ወኣነብብ ትእዛዘከ ዘኣፍቀርኩ ጥቀ፡፡ ወኣነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘኣፍቀርኩ
- ወንጌል ዮሐንስ.19፥38፦ ወእምድኀረዝንቱ ሰአሎ ለጲላጦስ ዮሴፍ
- በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ አው (ወይም…
❤10
Signed Mekuria Tesfaye
6 Aug 2026, 15:15 UTC≈2,710 views16 reactionsread 28 August 2026 ☞ የቅዳሴ ጊዜ የንባቡ ዓይነት የንባቡ መነሻ
- 1ኛቆሮ. 5፥11፦ ወይእዜኒ ጸሐፍኩ ለክሙ ከመ ኢትደመሩ፡፡
- 1ኛዮሐ. 2፥14፦ ጸሐፍኩ ለክሙ አበው እስመ አእመርክዎ
- ሓዋ.ሥራ 12፥18 ፦ ወጸቢሖ ተሀውኩ ሠገራት፡፡
- ምስባክ መዝ 44፥16-17፦ ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፡፡ ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር፡፡ ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ
- ወንጌል ሉቃስ.6፥20፦ ወውእቱሰ አንሥአ አዕይንቲሁ፡፡
- በዚህ ዕለት የሚቀደሰው ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ )
➕ ነሐሴ 12
- በዚህ ዕለት የሚታሰቡ :- ቅዱስ ሚካኤል አስተርአዮ ለቈስጠንጢኖስ ወነግሠ ቈስጠንጢኖስ በሮሜ ወ፳፻ ሰማዕታት ማኀበራነ ፋሲለደስ፡፡
- ምስባክ ዘነግህ መዝ…
🙏8❤7🥰1
Signed Mekuria Tesfaye
5 Aug 2026, 17:34 UTC≈2,010 views11 reactionsread 28 August 2026 Photo
የገጠሪቱ ቤተክርስቲያን የጾመ ፍልሰታ ቅዳሴ እንዳይታጎል እርዳታ እናድርግላቸው !
አድራሻው በወረቀቱ ላይ አለ
❤11
Signed Mekuria Tesfaye
Showing the 12 most recent of 26 posts we hold for @betgubae. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.