20 Dec 2025, 09:45 UTC90 views17 reactionsread 26 September 2026 አእምሮ የሕይወት መሸፈኛ ሳይሆን ሕይወትን ነጻ የማውጫ መንገድ ነው፡፡ አሁን አሁን በሄድክበት ሁሉ ሰዎች “አእምሮህን መቆጣጠር አለብህ” ይላሉ፡፡ አእምሮህ ግን የሚያስፈልገው ነፃ መውጣት እንጂ ቁጥጥር ሊደረግበት አይደለም፡፡ አእምሮ እንቅፋት ሳይሆን፣ ትልቅ ዕድል ነው... አእምሮ እንቅፋት የመሆኑ ችግር የሚፈጠረው የአእምሮን መሰረታዊ ባህሪይ ሳትረዳና ሳታውቅ፣ ልትመራው ስትሞክር ነው፡፡
ዋነኛው የአእምሮ ችግር ሥነ ምግባር ነው፡፡ ሌላኛው ትልቁ ችግር ደግሞ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ትክክልና ስህተት የሚባሉት ነገሮች በአእምሮ ላይ መጫናቸው ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ እና መጥፎ የሆነ የሚለውን ሀሳብ አስተምረውሃል፡፡ ጥሩና መጥፎ በጣም ጠንካራ የሆኑ የማንነት ነጥቦች …
🥰6❤4👍4😍3
Signed Wudassie
10 Dec 2025, 12:25 UTC91 views15 reactionsread 26 September 2026 ትክክለኛ ጓደኛ ማለት ከድሮም ጀምሮ የምታውቀው ሰው ሳይሆን ፀባይህ ሲቀየር አብሮህ የሚቀረው ነው፣ ትክክለኛ ጓደኛ ማለት ጮክ ያለውን ሳቅህን ሳይሆን የረዘመውን ዝምታህን ሚያስተውለው ነው፣ ለማይፈልግህ ሰው ደስታ ስትለፋ የተረዳህ ሰው ነው ጓደኛ ማለት፣ ያለ ምላሽ እንደምትሰጥ እና ወድቀህ እንደምትነሳ ያስተዋለህ ነው ጓደኛ ማለት፣ ማብራሪያም ሆነ ማስረጃም አይፈልግም የውስጥህን ለመረዳት፣ ምክንያቱም እሱ ካንተ ሚጠብቀው አሪፍ እንድትሆን ሳይሆን እራስህን እንድትሆን ነው ሚፈልገው፣ ንግግርም ቀንሶ በህይወት ውጣ ወረድ ጊዜም ስታጣ አይርቅህም፣ እዛው አብሮህ ይሆናል፣ ሁሌም ባያወራህም ሁሌም ባያይህም ያስብሃል ይጨነቅልሃል፣ ሳታወሩ ቀናቶች ሊያልፋ ይችላሉ ከዛም…
❤6👍3🥰3😍3
Signed udassie
9 Dec 2025, 05:34 UTC71 views19 reactionsread 26 September 2026 አንዳንዴ ለእኛ ከቀረቡት ሰዎች ይልቅ የራቁን ሰዎች አሳምረው ያውቁናል። ከአንድ እናት ተወልደው በአንድ ጣሪያ ሥር ከአደጉ ወንድምና እኅት በላይ አራምባና ቆቦ ያሉ ሰዎች ይሳሳባሉ። ልብ ለልብ ይግባባሉ። እንጀራ ጠቅልለን የምናጎርሰውን ሰው ሆድ አናውቅም። አንዳችን የአንዳችንን ልብስ ለብሰን ስንሳሳቅ የምንተዋወቅ እንመስላለን።
እንደ ወንድምና እኅት የወረስናቸው ዓይኖችና ጆሮዎች ተመሳሳይ ናቸው። እርስ በእርስ ግን አንተያይም። አንሰማማም። ዓይኖቻችን የሩቅ ሰው ያያሉ። ጆሮዎቻችን ባይተዋሩን ያደምጣሉ። በሥጋ እንጂ በመንፈስ አልተዛመድንም።
📓ትዝታሽን : ለእኔ ትዝታዬ : ለአንቺ
😍7🥰5❤4👍3
Signed udassie
23 Nov 2025, 18:16 UTC91 views16 reactionsread 26 September 2026 ተስፋ መቁረጥ የሀዘን የቅርብ ጓደኛ ነው። ይህ ተስፋ መቁረጥ ግን የአንድ ነገር አለመሳካት አይደለም፤ ከሱም በላይ ነው። የሕልውናን ትርጉም መካድ፣ የሁሉም ነገር ከንቱ መሆን ስሜት ነው። ከፊታችን ያለው ዓለም ባዶ መድረክ ይመስለናል፣ አኛም በጨለማ ውስጥ ተደብቀን በዝምታ ብቸኝነታችንን የምንመለከትበት ተመልካች ነን። ይህ ስሜት ማንኛውንም ደስታ ወይም ብርሃን የማየት ችሎታን ያደበዝዛል፣ ሁሉንም ነገር ግራጫ ያደርገዋል።
በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነን ፍርሃት ይጨመራል የሚመጣውን ሳይሆን አሁን ያለውን የሀዘን ዘላለማዊነት ፍርሃት። ይህ ስሜት መቼም ቢሆን ላይለቀን እንደሚችል ማሰብ ሌላኛው አስፈሪ ነገር ነው። ይህ ህመም የራስህ የሕይወት አካል ሆኖ ሌላ ማንኛውን…
😍5❤4👍4🥰3
Signed udassie
15 Oct 2025, 09:18 UTC121 views16 reactionsread 26 September 2026 አንዳንዴ ህይወት ውስጥ እንዲህ ያጋጥማል እንዳሰብከው ሳይሆን አንተ እንደጠበከው ፍፁም ተቃራኒ ሆኖ ነው ሚገኘው ከጎንህ ላለው በርቶ ላንተ ይጨልማል ሌት ከቀን እየጣርክ ትርፍህ ድካም ሆኗል ያቀድከው ያለምከው አልሳካ ብሎህ መጣ ያልከው ቀርቶ ደግ ያልከው ከፍቶብህ የኔ ያልከው ወዳጅ የሩቅ ሰው ሆኖብህ ውስጥህ ብቸኝነት ተሞልቶ ባዶነት ድንግርግር ብሎህ ትርጉሙ የህይወት በቃ ሁሉም ነገር ስልችት ብሎሀል ከተስፋ መቁረጥ ስር ካፍፉ ቆመሀል ልብ በሉ ህይወት ይቀጥላል ጨለማን ባናውቅ ኖሮ እኮ የብርሀንን ዋጋ ባልተገነዘብን ነበር ማጣትን ባናይ ኖሮም የማግኛት ትርጉም በቅጡ ባልገባን ነበር የደግ ሰዎችን ግምት አንድታቅ የሚያደርጉህም የክፉወች መኖር ነው አይ…
❤7🥰4😍3👍2
Signed Wudassie
13 Oct 2025, 10:44 UTC85 views17 reactionsread 26 September 2026 ረጃጅም ህንጻዎች ትናንሽ ትግስቶች፣ ሰፋፊ መንገዶች፣ ጠባብ አመለካከቶች፣ የምናወጣው ብዙ የሚኖረን ጥቂት፣ብዙ እንገዛለን ጥቂት እንደሰታለን፣ ትላልቅ ቤቶች ትናንሽ ቤተሰቦች፣ የተሻለ ምቾት ጥቂት ጊዜ፣ ብዙ ዲግሪ ትንሽ ማመዛዘን(ግንዛቤ)፣ ብዙ እውቀት ትንሽ ጥበብ፣ ብዙ አዋቂነት ብዙ ችግሮች፣ ብዙ መድኃኒት ትንሽ ጤነኝነት ስለ ጥሩ አኗኗር ተምረናል እንዴት እንዴት እንደሚኖር ግን አልተማርንም ለህይወት እድሜ ጨምረንለታል ለእድሜ ግን ህይወት አልጨመርንበትም መከባበር በመናናቅ መተዛዘን በመጠፋፋት ህሊና በሆድ ተተኩ ጨረቃ ላይ ደርሰን ተመለስን ግርግዳ የሚለየውን አዲሱ ጎረቤታችንን መተዋወቅ አቀበት ሆነብን ከምድራችን ውጪ ያለውን ህዋ ተቆጣጠርን በውስጣችን …
👍6🥰5❤3😍3
Signed Wudassie
10 Oct 2025, 08:15 UTC72 views15 reactionsread 26 September 2026 አእምሮ የሕይወት መሸፈኛ ሳይሆን ሕይወትን ነጻ የማውጫ መንገድ ነው፡፡ አሁን አሁን በሄድክበት ሁሉ ሰዎች “አእምሮህን መቆጣጠር አለብህ” ይላሉ፡፡ አእምሮህ ግን የሚያስፈልገው ነፃ መውጣት እንጂ ቁጥጥር ሊደረግበት አይደለም፡፡ አእምሮ እንቅፋት ሳይሆን፣ ትልቅ ዕድል ነው... አእምሮ እንቅፋት የመሆኑ ችግር የሚፈጠረው የአእምሮን መሰረታዊ ባህሪይ ሳትረዳና ሳታውቅ፣ ልትመራው ስትሞክር ነው፡፡
ዋነኛው የአእምሮ ችግር ሥነ ምግባር ነው፡፡ ሌላኛው ትልቁ ችግር ደግሞ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ትክክልና ስህተት የሚባሉት ነገሮች በአእምሮ ላይ መጫናቸው ነው፡፡ ሰዎች ጥሩ እና መጥፎ የሆነ የሚለውን ሀሳብ አስተምረውሃል፡፡ ጥሩና መጥፎ በጣም ጠንካራ የሆኑ የማንነት ነጥቦች …
👍6❤5🥰4
Signed Wudassie
7 Sept 2025, 07:26 UTC104 views15 reactionsread 26 September 2026 እግዚአብሔር ጸሎታችን አይዘነጋም ግን it
might take some times የጠየቅነውን እስኪሰጠን ወይም ከሆነ አመታት በፊት እግዚአብሔርን የጠየቅነው ጥያቄ ይኖራል ያ ጥያቄ ደግሞ mindset understanding and maturity level ይጠይቃል እነዚህ ነገሮች ደግሞ ዝምብለን በቀልድ የምናልፈው ሳይሆን Hustle እና ብዙ መውጣት መወረድ ይኖረዋል እግዚአብሔር በዛ ውስጥ ሲያሳልፈን ደግሞ እየሰራን ነው ማለት ነው ለጸሎታችን መልስ ሊሰጠን እያዘጋጀን ነው !
እኛን ለጥያቄዎቻችን መሸከም የምንችልበት ጥንካሬ ሊሰጠን ስለሚፈልግ ነው ነገሮች የሚዘገዩት or የዘገዩ የሚመስሉን
እንጂ እንደጠየቅነው ወዲያው ቢሰጠን ወይ ልንጠፋበት እንችላለን ወይ ልና…
👍5😍5❤3🥰2
Signed udassie
19 Aug 2025, 06:02 UTC124 views17 reactionsread 26 September 2026 ምንምን መናገር..
አንዳንድ ነገሮች ምስክር አያስፈልጋቸውም ማንም ማረጋገጫ አይስጥበት ብቻህን ታመመው ከመጀመሪያው ያልነበሩ ሰዎች ናቸው አሁን ላንተ ምስቅልቅል መፍትሄ አይሉት ፍርድ እየሰጡ የተቸገርከው.. እነሱም ልክ ናቸው አንተም የራስህን ነገር አድርግ ሰላምን እንጂ ፍፁምነትን አትፈልግ, ፍፁምነትን ሳታገኝ ሰላምህን ደሞ ላታገኝ ይሆንና ግራ ይገባሃል ያኔ ነው የመኖር ምክንያት የሚሉት ከባድ ጥያቄ የሚፈጠረው.. ማሰብ መልካም ማሰላሰል ጥሩ ሆነው ሳለ አንተ የያዝከው ጭንቀት ግን ተመችቶሃል.. ያርግልህ ባሻዬ ይመችህ.. ያለህበትን ምስቅልቅል ተቀብሎ የሚያኖርህ ቤት ካለህ እድለኛ ነህ ከሌለህ ደሞ መቃብርህን ስትናፍቅ ጊዜ ይቆጠራል.. የሄደ አይመጣም ያ…
👍7❤4🥰3😍3
Signed udassie
12 Aug 2025, 07:28 UTC130 views22 reactionsread 26 September 2026 እንዲህ ነው ወይ....?
ህይወት ልክ እንደ ትራፊክ መብራት እና መብራቱን ከበው መስቀልኛ መንገድ ላይ እንደቆሙ መኪኖች ናት። ህይወት በሆነ አጋጣሚ ያገናኘህ አንተ ቀይ ላይ ሆነሆ ለሱ አረንጓዴ ሲበራ ጥሎህ ይሄዳል። ቀይ የበራብን ግን ባለንበት ቋመን አለን.... አዎን አብሮህ ጎንለጎን እየተጓዘ የነበረ ወዳጅህ ለሱ አረንጓዴ በርቶ አንተን ቀይ መብራት ውስጥ ያለኸውን የሚጠብቅበት ምክኒያት የለም
❤10👍6🥰3😍3
Signed udassie
11 Aug 2025, 07:09 UTC123 views22 reactionsread 26 September 2026 በነገራችን ላይ ሰው ማጣትን ወይ ደሞ ከዜሮ መጀመርን አደለም ሰው ምን ይለኛል ትላንት አግኝቶ አጣ እባላለሁ ትላንት ሳረጋቸው የነበሩ የቅንጦት ነገሮች ሲቀሩ በሰዎች ዘንድ እታማለው ሚለውን ነው ሚፈራው ግን አንዳንዴ አጥቶ መመለስም ትልቅ ትምህርት ነው በአገኘንበት ጊዜ የሰራናቸው ስህተቶች
ግልፅ ሁነው እናገኛቸዋለን በአገኘንበት ጊዜ መጥሮ የሆንበት እና ለውድቀታችን መነሻ የሆነውን ስህተት እንረዳዋለን መልሰን ብናገኝ እንኳን የአጣንበት ጊዜ ቀጥቶ አስተምሮናል እና ድጋሚ ያንን ስራ አንደግመውን
ህይወት ፈትና ነው ምታስተምረው
❤7👍7😍5🥰3
Signed udassie
10 Aug 2025, 11:58 UTC106 views21 reactionsread 26 September 2026 ሁሉም እስካልረሰበት ድረስ አያውቀውም...
የሰው ህመም የሚገባህ በቦታው ሆነህ ስታየው ብቻ ነው! ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል እንዲሉ አበው ከዳር ሆኖ መፍረድ በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡ እየተዝናናህ በአጠገብህ የአምቡላንስ ጩኸት ስትሰማ 'ለምን ያደነቁረናል' ብለህ ትናደዳለህ አንድ ቀን ግን የአንተ የሆነን ሰው ሲጭን "እባክህ ጥሩንባውን አስጩኽና መንገድ አስከፍት ቶሎ እንድረስ' ብለህ ትማፀናለህ....የሃዘን ቤት ምስር ይጣፍጣል ነው ያልከኝ? ልክ ነህ ይጣፍጣል..ጣዕም አልባ መሆኑ የሚገባህ አንተ ቤት ውስጥ ሲሰራ ነው!
👍10🥰4😍4❤3
Signed udassie
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @cloudss_17. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.