2 Aug 2026, 12:25 UTC247 views1 reactionsread 7 August 2026 #ታላቅነት_የሚገኘው_በትሑት_ነው
ወደ ክብር የሚወስደው መንገድ ትህትና ነው፡፡ ይህን በጎነት ከየት እናገኘዋለን? ትህትና ወደሚኖርበት ወደ መልካም ማደሪያ መሄድ ትፈልጋለህ? በዚያም በየደረጃቸው በሀብታቸው የታወቁ፤ በኹሉም የሕይወት ዘርፍ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን እናገኛለን፡፡ በሕይወታቸውም ላይ "ትህትና" የሚለውን ቃል በብዕርና በቀለም ይጽፋሉ፡፡ የተንቆጠቆጡ አለባበሶች፤ የተንቆጠቆጡ ቤቶች ከንቱነትን ይወልዳሉና ብዙውን ጊዜ ሰዎች በትዕቢት ወጥመድ ይወድቃሉ፡፡ ኾኖም በትህትና ውስጥ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች ምንም ያህል አገልጋዮች ቢኖሯቸውም፤ የራሳቸውን እሳት ያቀጣጥላሉ የራሳቸውን እንጨት ይፈልጣሉ፤ የራሳቸውን ምግብ ያዘጋጃሉ በግላቸውም እንግዶቻ…
❤1
Signed Sirak Solomon
1 Aug 2026, 09:24 UTC209 viewsread 7 August 2026 ጉባኤ ኒቅያ
ለዐራት መቶ ዓመታት ያህል ቤተ ክርስቲያን በብዙ አቅጣጫ የተለያዩ ችግሮች ደርሰውባት እጅግ ስትሠቃይ ኖራለች፡፡ ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ አንዱ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የዶግማ ትምህርት ልዩነት መፈጠሩ ነው፡፡ በወቅቱም ውስጥ እንደነ ጳውሎስ ሳምሳጢ፣ ሰባልዮ የመሳሰሉት የተነሱበት ነበር፡፡ በተለይም አርዮስ ‹‹ወልድ ፍጡር ነው›› ብሎ በመነሣቱ ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዓመታት እንድትታወክና እንድትበጠበጥ መንሥኤ ሆኗል፡፡
አርዮስ የተወለደው በ፪፻፷ ዓ.ም አካባቢ በሰሜን አፍሪካ በሊብያ ነው፡፡ የትውልድ ሐረጉ ግን ከግሪክ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አርዮስ መሠረታዊ ትምህርቱን በሊብያ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ እስክንድርያ በመጓዝ በእስክንድርያ ከፍተኛ ትምህርት ቤት…
Signed Tom 2020
29 Jul 2026, 15:04 UTC365 views1 reactionsread 7 August 2026 #ጥሩ_ሕልም_አላየሁምና_አይሂዱ
✍🏽ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ "እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲ…
❤1
Signed Sirak Solomon
27 Jul 2026, 14:26 UTC245 viewsread 7 August 2026 Photo
#አልተውህም
ይህ በሁኔታ ከሚቀየር በምክንያት ከሚወድ ሰው የተገኘ ቃል አይደለም። ምንም ምን የሚቀይረው የሌለ መውደዱ በሁኔታ ላይ ያልሆነ መውደዱ የሁሌ እንዲሁ ከሆነ ከአምላካችን የተነገረ ቃል ነው።
እናት የወለድችውን ልጇን ልትረሳ ልትተው እንደማትችል ሁሉ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን የማይተወን በሰውነታችን ያለውን ድካም የሚረዳልን አባታችን አምላካችን እግዚአብሔር አለልንና እንበርታ!
ነገሮች የከበዱ ቢመስሉም ሁሉም ነገር ከእርሱ ጋር ቀላል ይሆናል ደግሞ ይህም የሚያልፉ ሳይመስሉን እንዳለፉ ትላንቶቻችን ያልፍና ተመስገን እንላለን እንበርታ!
“እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ…
Signed Tom 2020
26 Jul 2026, 11:49 UTC274 views1 reactionsread 7 August 2026 እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል፣ ለቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት እየሉጣ: ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን: አደረሳችሁ::
ቅድስት ኢየሉጣ እናታችን በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩና በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳት አንዷ ናት:: በወቅቱ ቅዱስ ቂርቆስ የሚባል ደግ ልጅ ወልዳ ባሏ ባለመኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር:: የዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር ከመነገር በላይ ነው:: በዛው ልክ ደግሞ መከራው በጸጉራቸው ቁጥር ልክ ነበር::
ከሮም ግዛት በአንዱ ከቅዱስ ልጇ ጋር የምትኖረው ቅድስት ኢየሉጣ የስደቱ ዘመን ሲመጣ እርሷም እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ተሰደደች:: እስክንድሮስ የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ግን ያለችበት ድረስ ተከትሎ እንድትያዝና እንድ…
👍1
Signed Sirak Solomon
26 Jul 2026, 11:45 UTC150 viewsread 7 August 2026 Photo
እንኳን ለቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት እየሉጣ: ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
ቅድስት ኢየሉጣ እናታችን በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩና በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳት አንዷ ናት:: በወቅቱ ቅዱስ ቂርቆስ የሚባል ደግ ልጅ ወልዳ ባሏ ባለመኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር:: የዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር ከመነገር በላይ ነው:: በዛው ልክ ደግሞ መከራው በጸጉራቸው ቁጥር ልክ ነበር::
የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት: ተራዳኢነት አይለየን:: የቅዱሳኑም በረከታቸው ትድረሰን::
Signed Zelalem NurelegnZ
24 Jul 2026, 14:28 UTC245 views2 reactionsread 7 August 2026 #ምን_ብዬ_ልጸልይ?
በግሪክ ሀገር ሁለት ሴት ልጆቹን ያሉት አንድ አባት ነበር። በአንድ ዓመት ብቻ የሚበላለጡትን እነዚህን ሕጻናት እንደ አባትም እንደ እናትም ሆኖ ተንከባክቦ ማሳደግ የዚህ ሰው ዋነኛ ሥራው ነበር።
ስለዚህ ወጥቶ በገባ ቁጥር ልጆቹን የሚያስደስት ነገር እየገዛ፣ የሚጠይቁትን እያሟላ በድሎት ያኖራቸው ነበር። የራሱን ሕይወት ወደ ጎን ትቶ ለልጆቹ መኖሩ ያለ ዋጋ አልቀረም። ሁለቱም ልጆቹ በጤንነት አድገው ዕድሜያቸው ለጋብቻ ደረሰ።
አባት የለፋባቸው ልጆቹን ከመዳሩ በፊት ብዙ መሰብ ነበረበት። አስተዋይ ነበርና ብዙ ሽማግሌ ቢላክበትም ልጆቹን ለመሥጠት የወሰነው ግን በጥንቃቄ ነበር። ስለዚህ ልጆቹ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እንዳይቸገሩ በማሰብ …
❤2
Signed Sirak Solomon
23 Jul 2026, 09:45 UTC505 viewsread 7 August 2026 #ከሌላዉ_ጥፋት_መማር_ትልቅ_ዕዉቀት_ነዉ
መነኮስ አባ አርሳንዮስ በገባበት ገዳም ዉስጥ እግዚአብሔርን እያገለገለ ሲኖር አንድ ቀን ከገዳሙ ሕግ ዉጭ የሆነ ነገር ይፈጽማል፡፡ ጥፋቱ ከገዳሙ አበምኔት ይደርስና አበምኔቱ አስበዉ ብገስጸዉ ያፍራል፣ ዝም ብል ጥፋቱ ጥፋት ሳይመስለዉ ሊቀር ነዉ አሉና፡፡ የሱን ረድዕ ጠርተዉ እንዲህ አሉት፡፡ "አርሳንዮስ ያጠፋዉን ጥፋት እኔ እያየሁህ በእርሱ ፊት አንተ አጥፋ ከዛ በጥፊ እመታሃለሁ፡፡ ያኔ እርሱ በአንተ ጥፊ ይማራል አሉት፡፡" እንደተመካከሩት በአርሳንዮስ ፊት ረድኡ የእርሱን ጥፋት አጠፋ አበምኔቱም ተቆጥተዉ በጥፊ መቱት በዚህ ግዜ ነገሩን የተከታተለዉ አርሳንዮስም "ይህች ጥፊ የኔ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
እግዚአብሔር …
Signed Sirak Solomon
18 Jul 2026, 11:42 UTC341 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ንስሐ
"የሰው አይን ሊያይህ ይችላል፣ የሰውም አንደበት ሊወቅስህ ይችላል፤ ነገር ግን ከገዛ ሕሊናህ የምታመልጥበት ምንም ስፍራ የለም።
ንስሐ ማለት የሕሊናህን ዳኝነት በእግዚአብሔር ምሕረት መፍታት እንጂ የኃጢአትህን እዳ በራስህ ላይ መደርደር አይደለም።"
#ቅዱስ_አምብሮስ
የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽
Telegram:
☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
❤1
Signed Zelalem NurelegnZ
18 Jul 2026, 11:32 UTC307 views1 reactionsread 7 August 2026 #ራስህን_ጠይቅ
ቤትህ ውስጥ ከፍተህ የረሳኸው ባንቧ ቢኖርና ድንገት ሌሊት ከእንቅልፍህ ስትነቃ መሬቱ እንዳለ በውኃ ተጥለቅልቆ ብታገኝ በቅድሚያ ምን ታደርጋለህ? የፈሰሰውን ውኃ ለመጥረግ ወይስ የሚፈሰውን ቧንቧ ለመዝጋት ነው የምትቸኩለው?
ቧንቧውን ሳትዘጋ መሬት ላይ ያለውን ውኃ ለማፈስ ብትሞክር ትርፉ ድካም ነው። ቀኑን ሙሉ ስትዝቅ ብትውል ቤትህ የሞላውን ውኃ አታጎድልም። እናስ? ቧንቧውን ዝጋዋ!
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ መፍትሔ በማታገኝበት ነገር ላይ ጊዜህን አታባክን። ለዚህ የሚዳርገኝ መነሻው ምክንያት ምንድን ነው? ብለህ ራስህን ጠይቅ። አእምሮህ ውስጥ የሞሉትን ክፋቶች ከመቁጠር በላይ እነዚያ ክፋቶች የገቡበትን አንድ ቀዳዳ ወይም ሽንቁር ለማወቅ ጣር…
❤1
Signed Tom 2020
17 Jul 2026, 15:12 UTC496 views1 reactionsread 7 August 2026 #ሰድበውኛልና_ልበቀላቸው_አትበል
አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ ''ሰድበውኛል'' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ ''ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው'' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን …
❤1
Signed Tom 2020
15 Jul 2026, 09:27 UTC507 views1 reactionsread 7 August 2026 #እኔ_የምፈልገው_የቅርጫት_ውሃ_ነው፡፡
✍🏽👉🏼በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጀመረ፡፡
አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡
ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫ…
❤1
Signed Sirak Solomon
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @degusamraw. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.