11 Aug 2026, 15:59 UTC302 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ነሀሴ 5 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦
🟢ኢትዮጵያ እያካሄደች በሚገኘው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
🟢ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
🟢የብሔራዊ ባንክ በነገው እለት የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
🟢የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ48 ሚሊዮን ደንበኞቹን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የ3ኛ ዙር የሳይበር ደህንነት ወር ንቅናቄ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
🟢በአዲ…
❤1👍1
11 Aug 2026, 13:55 UTC334 viewsread 12 August 2026 Photo
ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
ይህ የተነገረው በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሳውዲ አረቢያ ቱሪስት አስጎብኚ ቡድንን ተቀብሎ ባወያየበት ወቅት ነው፡፡
በዚሁ ጊዜም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸው የኢትዮጵያ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ተከትሎ በዘርፉ የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሳውዲ አረቢያ ቱሪስት ቡድን አባላት በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች እንደሆነ …
11 Aug 2026, 13:16 UTC336 views1 reactionsread 12 August 2026 Photo
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን ጥቃት በመስጋት ከቱርክ በምግብ መስተንግዶ መኪና እና በምስጢር በረራ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነግሯል፡፡
በቅርቡ ወር አዲሱን ኤየር ፎርስ ዋን አውሮፕላናቸውን ተጠቅመው ለኔቶ ጉባኤ ወደ ቱርክ የተጓዙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከጉባኤው በኋላ በቀድሞው ፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላናቸው ወደ ሀገራቸው መጓዛቸው ነበር በወቅቱ የተገለጸው፡፡
ሆኖም ትራምፕ በካሜራ ፊት ወደ ድሮው ኤየር ፎርስ ዋን ፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላናቸው ሲገቡ ከታዩ በኋላ እንደገና ወርደው በምስጢር በምግብ መስተንግዶ ወይም ኬቴሪንግ መኪና አማካኝት ወደ ሁለተኛና አነስተኛ የፕሬዝዳንቱ ወታደራዊ አውሮፕላን መዛወራቸው እና በብሪታንያ በኩል ወደ ሀገራቸው መጓዛቸው ነው …
❤1
11 Aug 2026, 13:11 UTC289 viewsread 12 August 2026 Photo
የብሔራዊ ባንክ በነገው እለት የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
ባንኩ ነገ ነሐሴ 6 በሚያደርገው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 125 ሚሊየን ዶላር እንደሚያቀርብ ገልጿል።
የብሔራዊ ባንክ በነሐሴ እና መስከረም ወራት የግማሽ ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ መግለፁ ይታወሳል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
11 Aug 2026, 12:58 UTC285 views1 reactionsread 12 August 2026 Photo
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች :-
✅በኮሎምቢያ የደረሰውን ርዕደ መሬት ተከትሎ ከ2700 በላይ ዜጐች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።
✅የሶሪያ ፍ/ቤት የቀድሞ የሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ በሌሉበት በሞት እንዲቀጡ ፍርድ ሰጠ።
✅የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል በመጠቀም ጥቃት እየፈፀመች ነው ብለዋል።
✅በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቀጠለው የኢቦላ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2ሺ ተሻግሯል።
✅የየመኑ ሁቲ በቀይ ባህር በሚንቀሳቀስ አንድ አነስተኛ መርከብ ላይ በፈፀመው ጥቃት 3 መርከበኞች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
…
❤1
11 Aug 2026, 12:46 UTC261 viewsread 12 August 2026 Photo
የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በኮሚሽኑ ምክር ቤት በተለዩ ስምንት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አጀንዳዎቹ 500 አባላት ባሏቸው ስምንት የስራ ቡድኖች ምክክር እየተደረገባቸው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት 500 አባላት ያሉት አንድ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ እየተመካካረ ይገኛል፡፡
ኮሚሸኑ ባወጣው መግለጫ በሃይማኖት ጉዳዮች እና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሲመካካሩ የቆዩት ሁለ…
11 Aug 2026, 12:28 UTC467 viewsread 12 August 2026 Photo
በአዲስ አበባ በሚካሄደው 6ኛው ዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ፣ ቴክኖሎጂና ኮስሞቲክስ ኤክስፖ ከ150 በላይ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ከህዳር 24 እስከ 26 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር በሚካሄደው ኤክስፖው በርካታ የውጭ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ነው ያስታወቀው።
በኤክስፖው የማምረቻ ዘርፍ፣ የምግብ ማቀነባበሪያ፣ የብረታብረት፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የፕላስቲክና ማሸጊያ ምርቶች እና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ አምራቾች፣ ነጋዴዎችና አቅራቢዎች እንደሚሳተፉም ተገልጿል።
ኤክስፖው የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎችን በማገናኘት የገበያ ዕድሎ…
11 Aug 2026, 12:22 UTC323 viewsread 12 August 2026 Photo
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ48 ሚሊዮን ደንበኞቹን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የ3ኛ ዙር የሳይበር ደህንነት ወር ንቅናቄ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
የባንኩ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ደህንነት ምክትል ፕሬዚዳንት ሥዩም ዳምጠው በበጀት ዓመቱ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ የዲጂታል ግብይቶች መከናወናቸውን ጠቅሰው በእነዚህ ግብይቶችም ከ22 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚደርስ ገንዘብ መንቀሳቀሱን ገልጸዋል።
ይህ የግብይት መጠን የአገሪቱን 70 በመቶ የፋይናንስ ግብይት የሚሸፍን መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ይህንን የገንዘብ ዝውውር ከሳይበር አደጋዎች ለመጠበቅ በመጪው ጥቅምት የ3ኛ ዙር የሳይበር ደህንነት ወር ንቅናቄ እንደሚካሄድ አስረድተዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ንቅ…
Live stream finished (25 minutes)
Live stream started
11 Aug 2026, 10:13 UTC359 views1 reactionsread 12 August 2026 Photo
የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ነሀሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የእኩለ ቀን የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች
፦
🟢ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ማስገኘቱን ገልጸዋል፡፡
🟢በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺ 708 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
🟢ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ።
🟢በአማራ ክልል በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ…
❤1
11 Aug 2026, 09:56 UTC310 viewsread 12 August 2026 Photo
በአማራ ክልል በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
በዚሁ ጊዜም በክልሉ የተሰበሰበው ገቢ በተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች እና የጸጥታ ችግሮች ውስጥ ታልፎ በተከናወነ የገቢ አሰባሰብ እንቅስቃሴ በመሆኑ አበረታች ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ያቀደው ቢሮው ከመደበኛ ገቢ ከ82 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ከከተማ አገልግሎ…
Showing the 12 most recent of 68 posts we hold for @ebstvnews. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.