7 Aug 2026, 14:47 UTC329 views9 reactionsread 8 August 2026 2/12/2018
ዮሐንስ 8:1-12
ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር። ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦ “መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት፡” አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ…
❤9
6 Aug 2026, 17:44 UTC661 views4 reactionsread 8 August 2026 File
ወፌ ሰንብታ ሰንብታ መጣች በፍልሰታ
❤4
6 Aug 2026, 15:13 UTC601 views11 reactionsread 8 August 2026 01/12/2018
ዮሐንስ 19:38-ፍጻሜ
ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት። በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ። ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት........
…
❤11
5 Aug 2026, 14:58 UTC649 views8 reactionsread 8 August 2026 30/11/2018
ማርቆስ 4:35-ፍጻሜ
ያንጊዜም ሲመሽ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ወደ ማዶ እንሻገር” አላቸው። ሕዝቡንም አሰናበተና በታንኳ ወሰዱት፤ ከእነርሱም ጋር ሌሎች ታንኳዎች ነበሩ። ጽኑ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፤ ከሞገዱም የተነሣ ውኃው ታንኳውን እስኪሞላው ድረስ ማዕበሉ ወደ ታንኳው ይገባ ነበር። እርሱ ግን በታንኳው በስተኋላ በኩል ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ቀስቅሰውም፥ “መምህር ሆይ፥ ስንሞት አያሳዝንህምን?” አሉት
ተነሥቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕርዋንም “ዝም በዪ፥ ጸጥ በዪ” አላት ፤ ነፋሱም ዝም አለ ፍጹም ጸጥታም ሆነ። “እንዲህም አላቸው፥ “እናንተ ደካሞች፤ ምን ያስፈራችኋል? እንዲህስ እምነት የላችሁም?” ታላቅ ፍርሀትንም ፈ…
❤8
4 Aug 2026, 15:31 UTC640 views10 reactionsread 8 August 2026 29/11/2018
ሉቃስ 12:1-13
በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው። ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። ለእናንተም ለወዳጆቼ እላችኋለሁ፥ ሥጋን የሚገድሉትን በኋላም አንድ ስንኳ የሚበልጥ ሊያደርጉ የማይችሉትን አትፍሩ። እኔ ግን የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎን እላችኋለሁ፥ እር…
❤10
4 Aug 2026, 13:24 UTC558 views2 reactionsread 8 August 2026 የዕወቀት ባለቤት ጥበብን የሚያናግር በጥልቅ ጨለማ ውስጥ ተሰውሮ የነበረውን የገለጽክልን የኃይልህን ከፍታ ለሚሰብኩ የደስታ ቃልን የምትሰጥ ።
ቀድሞ ያሳድድ የነበረ ጳውሎስን በብዙ ቸርነትህ የጠራኸው የተመረጠ ዕቃም ያደረግኸው አንተ ነህ በዚህም ወደድኸው ሐዋርያ ይሆን ዘንድ የምትጠራ የመንግሥትህንም ወንጌል የሚያስተምር ይሆን ዘንድ።
አምላካችን ክርስቶስ ሆይ ሰውን የምትወድ አንተ ነህ ። ቸር ሆይ ያለ ሥራ ዕውቀትን ካንተ የማይለይ ንጹሕ ሕሊናንም ስጠን ።
ዛሬም ከርሱ ዘንድ በኛ ላይ የተነበበች ክብርት የምትሆን የትምህርትህን ልክ እናውቅ እናስተውል እንረዳም ዘንድ ።
የሕይወት ራስ ሆይ አንተን እንደመሰለ እኛም እንደሱ በምግባር በሃይማኖት እሱን እንመ…
❤2
3 Aug 2026, 16:23 UTC613 views7 reactionsread 8 August 2026 28/11/2018
ማቴዎስ 19:1-23
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ ከገሊላ ተነሥቶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ደረሰ። ብዙዎች በሽተኞችም ተከተሉት፤ በዚያም ፈወሳቸው። 'ፈሪሳውያንም ሊፈትኑት ወደ እርሱ መጥተው፥ “በማናቸውም በበደለችው ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ለሰው ይገባልን?” አሉት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “አላነበባችሁምን? በመጀመሪያ የፈጠራቸው እርሱ ወንድና ሴት አደረጋቸው።” እንዲህም አለ፥ “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ሚስቱን ይከተላል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ። እንኪያስ ሁለት አይደሉም፤ አንድ አካል ናቸው እንጂ፤ እግዚአብሔርም አንድ ያደረገውን ሰው አይለይ።” እነርሱም፥ “እን…
❤7
2 Aug 2026, 17:56 UTC726 views19 reactionsread 8 August 2026 ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ ኃጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ፡፡
ያዕቆብ 5:19-20
❤19
2 Aug 2026, 17:22 UTC748 views16 reactionsread 8 August 2026 ዕብራውያን 2:17-18
ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው። እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።
❤16
2 Aug 2026, 16:22 UTC836 views5 reactionsread 8 August 2026 27/11/2018
የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ዮሐንስ 10:34-ፍጻሜ
ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “እኔ፦ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ፡’ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ‘ትሳደባለህ፡’ ትሉታላችሁን? እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።” እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ። ዮሐንስም በ…
❤5
1 Aug 2026, 16:30 UTC843 views9 reactionsread 8 August 2026 ዘሰንበተ ክርስቲያን
ማቴዎስ 8:1-ፍጻሜ
ከተራራም ሲወርድ ብዙ ሰዎች ተከተሉት። "እነሆ፥ አንድ ለምጻም ሰው መጥቶ፥ “አቤቱ! ከወደድህስ እኔን ማንጻት ይቻልሃል” እያለ ሰገደለት። 'እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈቅዳለሁ ንጻ” አለው፤ ያንጊዜም ከለምጹ ነጻ። 'ጌታችን ኢየሱስም፥ “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፣ ነገር ግን ሂድና ራስህን ለካህን አስመርምር፤ ምስክርም ሊሆንባቸው ሙሴ እንደ አዘዘ መባህን አቅርብ” አለው።
ወደ ቅፍርናሆም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ መጥቶ፦ “አቤቱ! ልጄ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተጨነቀ በቤት ተኝቶአል” ብሎ ለመነው። ጌታችን ኢየሱስም “እኔ መጥቼ እፈውለዋለሁ” አለው። የመቶ አለቃውም መልሶ፥ “አቤቱ!…
❤9
31 Jul 2026, 14:25 UTC848 views9 reactionsread 8 August 2026 25/11/2018
ማርቆስ 13:5-14
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች፦ ‘እኔ ነኝ፡’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ …
❤8👍1
Showing the 12 most recent of 21 posts we hold for @ethiobookclub2. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.