26 Aug 2026, 02:53 UTC≈2,190 views20 reactionsread 2 September 2026 Photo
ለፖሊስ የተሰጠ የእምነትቃል
=====/////=====
በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/መሠረት አንድ ተከሳሽ ለፖሊስ የሚሰጠው የእምነት ቃል ለምርመራ ዓላማ ሲባል በምርመራ ጊዜ የተገኘ ማስረጃ በመሆኑ የቀረበውን ክስ ለማስረዳት የሚችል ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆን አለመሆኑ በፍ/ቤት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚገባው እንጂ ከወዲሁ ተቀባይነት አለው ተብሎ ድምዳሜ የሚወሰድበት ስላለመሆኑ፤
በሰ/መ/ቁ 152038 (ሕዳር 28ቀን 2011ዓ.ም)ቅጽ 23
❤20
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
25 Aug 2026, 17:20 UTC≈2,360 views6 reactionsread 2 September 2026 Photo
የማስረጃ ምዘና መርኅን ስለመጣስ:-
ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ (የሰው ምስክርም ሆነ የሰነድ) መርምረውና መዝነው ፍሬ ነገርን የማጣራት ኃላፊነት አለባቸው:: (ሰ/መ/ቁ. 208495)
በተለይም፣ የቀረበን የሠነድ ማስረጃ ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ወይም ሳይመረምሩ በሰው ምስክሮች ቃል ላይ ብቻ ተመሥርቶ የሚሰጥ ውሳኔ የማስረጃ ምዘና መርኅን የሚጥስና መሠረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው:: (ሰ/መ/ቁ. 208495 -30/5/2013 ዓ.ም ውሳኔ ተሰጥቷል።👇
https://t.me/ethiolawtips
❤6
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
21 Aug 2026, 17:36 UTC≈3,880 views11 reactionsread 2 September 2026 File
https://t.me/ethiolawtips
☝️☝️☝️☝️☝️
👍9❤2
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
21 Aug 2026, 15:17 UTC≈3,010 views20 reactionsread 2 September 2026 Forwarded from @JuraLegalUpdateFile
File, posted without a caption
❤14👍6
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
9 Aug 2026, 06:31 UTC≈5,440 views23 reactionsread 2 September 2026 Photo
በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ በተሰጣቸዉ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዉክልና ስልጣናቸዉ በቀጥታ ያዩዋቸዉን የፈዴራል ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ስልጣን ያላቸዉ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑ በክልሉ እንዲደራጁ የተደረጉት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ናቸው ተብሎ ተወስኗል፡፡👇
https://t.me/ethiolawtips
❤22🔥1
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
2 Aug 2026, 11:51 UTC≈6,510 views39 reactionsread 2 September 2026 በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1196(1) መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ሰው የንብረቱ ባለቤት ለመሆኑ የሕግ ግምት የሚወሰድ በመሆኑ፣ ይህ ግምት ሊፈርስ የሚችለው ካርታው ከሕግ ውጪ መሰጠቱ ወይም ሰነዱን የመስጠት ሥልጣን በሌለው አካል የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ በሰው ምስክርነት ወይም ገንዘብ አውጥቻለሁ በሚል ክርክር ብቻ ሊፈርስ አይችልም።
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 (1 እና 2) መሠረትም የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጠበቀው በሕጋዊ መንገድ በተያዘ ይዞታ ላይ ሲሆን ብቻ ነው። በመሆኑም በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስት በወላጅ ስም በተመዘገበ ይዞታ ላይ ገንዘብና ጉልበት በማፍሰስ ቤት ቢገነቡ እንኳ፣ ይ…
❤25👍14
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
30 Jul 2026, 07:47 UTC≈5,010 views13 reactionsread 2 September 2026 የወንጀል ክስ ይርጋ በኢትዮጵያ
********
ወንጀል ፈፃሚዎች ለፈፀሙት ጥፋት በሕግ ፊት መጠየቃቸውና ተገቢውን ቅጣት መቀበላቸው ተገቢና አስፈላጊም ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ አንድ እንደተመለከተው በወንጀል ሕጉ መሰረት ወንጀል የተደረጉ ድርጊቶች እና የሚያስከትሉትን ቅጣት በመደንገግ ሰዎች ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ አሰቀድሞ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ቢሆንም ቅድመ-ማስጠንቀቂዎች በቂ ባልሆኑ ጊዜ ወንጀል ፈፃሚዎች ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲታቀቡና ለሌሎችም ማስተማሪያ እንዲሆኑ ማድረግን ግቡ ያደረገ ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ግን በወንጀል ሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ ሊመሠረት እና አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብ የሚገ…
❤13
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
30 Jul 2026, 07:47 UTC≈5,510 views21 reactionsread 2 September 2026 ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም።
ማጠቃለያ
የወንጀል ክስ በአንድ በኩል ተጎጂዎች ፍትሕ የሚያገኙበት የሕግ ሂደት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በወንጀል የተጠረጠሩ ወይንም የተከሰሱ ግለሰቦች ነፃነት በሕግ የሚገደብበት ነው። በዚሁ መሠረት የወንጀል ክስ መመስረቻ ጊዜ ገደብ በሕግ ወስኖ ማስቀመት በሁለቱ ተፃራሪ መብቶች መካከል ሚዛን ለመጠበቅ የሚያስችል ነው። ስለሆነም ማንኛውም ክስ በሕግ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ ይገባል፡፡
ምንጭ ፍትሕ ሚኒስቴር ገፅ
❤16👍5
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
29 Jul 2026, 13:41 UTC≈4,230 viewsread 2 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed ጠበቃ Henok Taye/0916-79-85-85
Showing the 9 most recent of 9 posts we hold for @ethiolawtips. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.