1 Aug 2026, 05:41 UTC≈3,210 views117 reactionsread 12 August 2026 + አለመቁረብ ምን ያጎድላል? +
የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አዲስ አበባ መጥተው በቀደሱበት ጊዜ ሕዝቡ ጥቅጥቅ ብሎ ቅዳሴ መሳተፉን አይተው ተደስተው ሳያበቁ፥ የሚቆርበው ምዕመን ቁጥር እጅግ ትንሽ መሆኑን ተመልክተው በወቅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ለነበሩት ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “ሕዝቡን እየቀለዳችሁበት ነው፤ ሕዝቡም እናንተ ላይ እየቀለደባችሁ ነው” እንዳሏቸው ይነገራል። አቡኑ እውነታቸውን ነው። ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ መቁረብ ካለመፈለግ በላይ፥ ካህን ሆኖም አስተምሮ ካለማቁረብ በላይ ቀልድ ማግኘት ይከብዳል።
በጥንት ዘመን አባቶች ሰላምታ ሲለዋወጡ ‘የጸሎት ሕይወትህ እ…
❤96🙏18🔥3
1 Aug 2026, 05:40 UTC≈1,430 viewsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
5 May 2026, 06:53 UTC≈3,210 views104 reactionsread 12 August 2026 Photo
+ የደካማው ጸሎት +
ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን በመሃል እጅህ ይዘህ ሳለ ለእኛ ሕይወት ታስባለህ። ከሞቃቷ ፀሐይ ይልቅ ሙቀቷ የሚያቃኝለው ደካማ ፍጥረት፥ ከመሬቱ ይልቅ ወደ መሬት ገብቶ ከአፈር የሚዋሐደው የሰው ልጅ ጉዳይ ትኩረትህ መሆኑን ማሰብ እጅን በአፍ ያስጭናል።
በዚህ አድካሚ ዓለም ስንኖር፥ አንተ እንደምትወደን ከማሰብ በላይ የሚያጽናና ነገር የለም። ለክብር ተፈጥረን በመዋረድ፥ ለንጽሕና ተፈጥረን በማደፍ ሕይወታችን እንዳይደመደም በጸጋህ ጠብቀን። ሰውን ወዳጅ እና ይቅር ባይ የሆንክ አምላካችን ሆይ፥ የዓለም ጨው መሆን እንዳቃተን አይተህ፥ ድንጋይ ናቸው ብለህ አትጣለን፥ ታገሰን እንጂ። የዓለም ብርሃን መሆን እንዳልቻልን አይተህ፥ ከዕንቅብ በታች አታስ…
❤82🙏20👍2
1 May 2026, 05:12 UTC≈3,400 views101 reactionsread 12 August 2026 + ዓይንህ ማንን ያያል? +
ክርስቶስ ከመረጣቸው አሥራ ሁለት ደቀ-መዛሙርት መካከል ሦስት ዓይነት ሰዎችን እናገኛለን።
የመጀመሪያው ዮሐንስ ነው። ዮሐንስ ከመጠራቱ አንስቶ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችንን የተከተለ ደቀ መዝሙር ነው። ፍቅሩ ፍጹም ነው። የተጠራበትን አገልግሎት የሕይወት ጥሪው አድርጎ በመውሰድ በጽናት እስከመጨረሻው ድረስ የተጓዘ ነው። ሁለተኛው ድግሞ ጴጥሮስ ነው። ጴጥሮስ እድሜው ገፋ ካለ በኋላ የተጠራ ደቀ መዝሙር ነው። ብዙ እድሜውን በዓለማዊ ነገር አሳልፏል። ብዙ ባክኗል፥ ብዙ አጥቷል፥ በመጠራቱ ደግሞ ብዙ አትርፏል። ጴጥሮስ ራሱን መልካም ደቀ መዝሙር አድርጎ ያስብ የነበረ፥ ክርስቶስን ‘አላውቀውም’ ለማለት ግን ትንሽ ነገር የበቃው ሰው ነ…
❤81🙏12💯3👍2🕊2🔥1
1 May 2026, 05:12 UTC≈2,070 views3 reactionsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
🙏3
28 Apr 2026, 05:19 UTC≈3,140 views116 reactionsread 12 August 2026 + የእኔ ቤት ይቀርባል +
አንዲት እናት ቁጭ ብላ ለልጇ መጽሐፍ ቅዱስ ታነብላታለች። ይህ የዘወትር ተግባራቸው ነበር። እናት ካነበበች በኋላ ለልጇ ‘እስቲ አሁን የሰማሽውን በራስሽ አገላለጽ ንገሪኝ’ የማለት ልማድ ነበራት። ከእለታት በአንዱ ቀን ከኦሪት ዘፍጥረት እያነበበች እያለች የጻድቁ ሄኖክ ታሪክ ጋር ደረሰች። “ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።” (ዘፍ 5፡23-24) የሚለውን ካነበበች በኋላ ‘እስቲ ይህንን በራስሽ አገላለጽ ንገሪኝ’ ብላ እድሉን ለልጇ ሰጠቻት።
ልጇም እንዲህ በማለት በራሷ መንገድ ገለጸችው።
“የውልሽ እናቴ… ሄኖክ ከ…
❤94🙏17🔥4💯1
28 Apr 2026, 05:19 UTC≈1,840 viewsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
20 Apr 2026, 08:11 UTC≈3,140 views94 reactionsread 12 August 2026 +የአህያ መስዋእትነት +
ለረዥም ጊዜ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ" እየተባለ ሲተረት እናውቃለን። ተረቱ ለሌላው ካለማሰብ የሚመጣን ራስ ወዳድነት የሚያጎላ ተደርጎ ይነገራል። በእርግጥ አህያ ማኅበረሰቡን አገልጋይ ሆና ሳለ፥ ራስ ወዳድ ሆና መሣሏ የሚገርም ነው። ተረቱ ግን የሚያንጸባርቀው እውነት ከአባባሉ ተለምዷዊ ትርጉም እጅግ የራቀ ነው።
በድሮ ዘመን በትልቅነቱ ከግራር እና ከዋርካ የሚተልቅ 'ሰርዶ' የሚባል ዛፍ ነበር ይባላል። ዛፉ ለብዙ አገልግሎት ስለሚውል ዝሆን እየገነደሰው፥ አህያ ደግሞ እየተሸከመች ታጓጉዘው እንደነበረ ይነገራል። ዘመን ሲገፋ ግን አህያም አቅሟ እየደከመ፥ ወገቧም እየተላጠ መጣ። ይህንን ያስተዋለው አንበሳ እንስሳቱን …
❤67🙏12😢5🥰4😁4🤔2
20 Apr 2026, 08:11 UTC≈2,330 views0 reactionsread 12 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
12 Apr 2026, 06:16 UTC≈4,060 views122 reactionsread 12 August 2026 Photo
ክርስቶስ ተነስቷል!
አዎ! ለዘመናት ሕዝብን ከአሕዛብ ሳይለይ የገዛውን ሞት ድል አድርጎታል! ድንጋዩን የሚያንከባልል ሳይፈልግ መቃብሩን ባዶ ትቶት ሄዷል! እኛም ከሞቱ ጋር የምንተባበር፥ ከትንሣኤውም ጋር እንተባበራለንና፥ እጅግ ደስ ይለናል!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል! ደስ ይበላችሁ! ደስ ይበለን!
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!
❤86🙏22🥰12🔥2
23 Feb 2026, 06:31 UTC≈6,190 views43 reactionsread 12 August 2026 Photo
+ በዐቢይ ጾም የነቢያቱን ቋንቋ ይማሩ! +
መጽሐፍ ቅዱስ በሦስት ጥንታዊ ቋንቋዎች ተጽፏል። ብሉይ ኪዳን በዕብራይስጥ እና በአረማይክ፥ ሐዲስ ኪዳን ደግሞ በግሪክ ቋንቋ የተጻፈ ነው። እነዚህ ቋንቋዎች የመጽሐፍ ቅዱስ እናት ቋንቋዎች ተብለው ይጠራሉ። ከእነዚህም ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የበዛውን ክፍል የሚይዘው የዕብራይስጥ ቋንቋ ነው። ዕብራይስጥ ታላቁ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ሕግ የተቀበለበት ቋንቋ ነው። ዕብራይስጥ በኦሪት ድንኳን አምልኮ የተፈጸመበት ቋንቋ ነው። ዕብራይስጥ ዳዊት ድንቅ የሆነውን መዝሙሩን የዘመረበት፥ ልጁ ሰለሞንም ምሳሌዎቹን የከተበበት ቋንቋ ነው። የዕብራይስጥ ቋንቋ ስለ ክርስቶስ ትንቢት የተናገሩ ነቢያት ትንቢታቸውን ያሰሙበትም ቋንቋ ነው።…
❤37🙏6
10 Feb 2026, 10:32 UTC≈4,630 views107 reactionsread 12 August 2026 Photo
አግፕያ (Ϯⲁⲅⲡⲓⲁ) የቅብጥ ቃል ሲሆን፥ የሰዓታት ጸሎት የሚል ትርጉም አለው። የግብጽ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዋነኛነት የሚጠቀሙት የጸሎት መጽሐፍ ነው። ከጠንካራዎቹ የግብጽ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሕይወት ጀርባ አግፕያ አለ ብንል ውሸት አይሆንብንም። መጽሐፉ የሰባቱን ዐበይት ሰዓታት ጸሎቶችን በማካተቱ፤ አንድ ክርስቲያን በቀን ሰባት ጊዜ ጸሎት ማድረስ አለበት የሚለውን መታዘዝ ለሚፈልግ ሁነኛ መጽሐፍ ነው። በየአንዳንዱ ሰዓት የመግቢያ ጸሎቶችን፥ ከመዝሙረ ዳዊት የሚደገሙ መዝሙራትን፥ የወንጌል ንባብ፥ ሊጦን እና የመሳሰሉትን ይዟል። ጸሎታችሁን ቅርጽ አስይዞ ለማስቀጠል ጥሩ መርጃ ነው።
ዶ/ር ሥርግው ገላው የጀርመንኛውን ቅጂ ወደ አማርኛ ጥሩ አድርገው ተርጉ…
❤84🙏22🤬1
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @fresenbett. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.