6 Aug 2026, 15:08 UTC44 views3 reactionsread 8 August 2026 ፍልሰታ
1. ሐዋርያት ጾሙን ለምን ጾሙት?
ጾመ ፍልሰታ ማለት ምን ማለት ነው?
«ፍልሰታ» የሚለው ቃል «ፈለሰ» (ከቦታ ወደ ቦታ ተዛወረ/ተሻገረ) ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን፣ «ጾመ ፍልሰታ» ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ከሞተች በኋላ ከምድር ወደ ሰማይ የመፈለሷን (የማረጓን) ምስጢር በማሰብ የሚጾም ጾም ነው።
ለምን እንጾማለን?
👉የሐዋርያትን አርአያ ለመከተል፦ ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ አይተው ለመባረክ ያበቃቸው ዘንድ «እሱ(ቅዱስ ቶማስ)ያየውን እኛ ሳናይ» ብለው ያደረጉትን ጾምና ጸሎት አርአያ በማድረግ።
👉 የእመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገት ለማሰብ፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእመቤታችንን ሥጋ ከ መቃብር አውጥቶ ወ…
❤3
5 Aug 2026, 04:35 UTC51 views2 reactionsread 8 August 2026 ✨ በጾም ውስጥ ስጋህን ሳይሆን ኃጢአትህን ግደለው! ✨
🥰2
1 Aug 2026, 17:52 UTC72 viewsread 8 August 2026 ✨✨✨🌿🌿✨✨✨🌿🌿✨✨✨🌿🌿
የክርስቶስን አሳብ የተረዱ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከእርሱ የተማሩት ከእርሱ ጋር የተነጋገሩትና እርሱን ያደመጡት እንኳ የዚህን መልካም አስተማሪያቸውን አሳብ የሚቃረን የራሳቸው የሆነ አስተሳሰብ ነበራቸው፡፡
✨✨✨🌿
ጌታችን በአንድ ወቅት ወደ ሳምራውያን መንደር በገባ ጊዜ በዚያች በኃጢአተኞች ከተማ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሊቀበሉት አልወደዱም፡፡ በዚህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሐዋርያት ሁለቱ ዮሐንስና ያዕቆብ “ጌታ ሆይ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን?” ብለውት ነበር። ጌታ ግን ከገሰጻቸው በኋላ
“ምን ዓይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ አታውቁም፡፡ የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አ…
29 Jul 2026, 03:51 UTC64 viewsread 8 August 2026 Photo
✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯
ሐምሌ ፳፪ በዚህች ቀን ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡
የከበረ ቅዱስ ዑራኤል ተረዳኢነቱ አይለየን
✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯✨🕯
28 Jul 2026, 05:38 UTC59 views1 reactionsread 8 August 2026 ☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
"እናቴ ሆይ ነፍሴ በአንቺ ዘንድ ትክበር። ስለ ቸርነትሽ እናቴ ነሽ ፤ ስለ ንግሥትነትሽም እመቤቴ ነሽ ፤ ስለ ልጅሽ የመድኃኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ ፤ እንደ ወደቅሁ እቀር ዘንድ አትርሽኝ"
✨አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ✨
🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜
❤1
26 Jul 2026, 04:59 UTC71 viewsread 8 August 2026 ✨✨✨💐💐✨✨✨💐💐✨✨✨💐💐
‹‹በእሳትና በውኃ መኻከል አሳለፍኸን›› (መዝ.፷፭፥፲፪)
ሥራው ግሩም የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር ማዳንም መግደልም የሚችል የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ (መዝ.፷፭፥፫) በእርሱ የሚታመኑት ቅዱሳን ሰማዕታት የሚደርስባቸውን መከራና ፈተና ሁሉ በጽናት፣ በልበ ሙሉነት የሚያልፉት ለዚህ ነው፡፡
እሳት ለቅዱሳን ሰማዕታት ጌጣቸው ነው፡፡ በመልክአ ሥላሴ ‹‹የሰማይ ግምጃ ብርሃን ሸማኖች የሆናችሁ ሥላሴ ሆይ ልብሰ ምሕረታችሁ የሰማዕትነት ልብስን ይሁነኝ፤ የእስጢፋኖስ ልብስ ደንጊያ በእኔ ላይ የለምና፤ የሕፃኑ ቂርቆስ ጌጡ የሚሆን እሳትም በእኔ ላይ የለምና›› ብለን የምንጸልየውም ለዚህ ነው፡፡ (መልክአ ሥላሴ፡- ለአትያጺክሙ)
ወርቅና ብር በ…
24 Jul 2026, 17:30 UTC60 viewsread 8 August 2026 ✨✨✨🍂✨🍂✨🍂
ኃጥእ በደለኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ! ወደ ቤተክርስቲያን መጥተህም ንስሓ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡ “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ የሚጠይቅህ ድካምና ጥረት እንደ ምን ያለ ነው? “በድያለሁ [ይቅር በለኝ]” ለማለት የሚጠይቅህ ዓይነት የሕይወት መንገድ ወይም እንደ ምን ያለ መከራ ነው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት ኃጥእ ነኝ ብለህ ራስህን ባትጠራ፥ ዲያብሎስ በዚህ እንደማይነቅፍህ አስበህ ነውን?
✨✨🍂
በፍጹም! እንዲያውም ንስሓ ባትገባ ይህን ከዲያብሎስ የሚመጣ ነቀፋ እንደሚኖር ጠብቅ፡፡ የከሳሽ ግብሩ ንስሓ እንዳትገባ መከልከል በዚያ ንስሓ ባልገባህበት በደልም አ…
15 Jul 2026, 08:34 UTC102 views2 reactionsread 8 August 2026 ✨✨🌱✨🌱✨✨🌱✨🌱✨✨🌱✨🌱
✨✨🌱 ከእግዚአብሔር መማር✨✨🌱
ዕውቀትን ፈጽሞ መቀበል የማይችሉ አንዳንድ አላዋቂ ሰዎች አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ከሰዎች የሚማሩ አሉ። እነዚህኛዎቹ የበለጠ አላዋቂዎች ናቸው፡፡ በትክክል ተምረዋል ወይም አዋቂዎች ናቸው የሚባሉት ግን በቀጥታ ከእግዚአብሔር የተማሩት ናቸው፡፡
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ብዙ ዓይነት ዕውቀቶችን ሰጥቶት ነው:: ከዚያ የበለጠ ዕውቀትን በፈለገ ጊዜም እግዚአብሔር ይጨምርለት ነበር። ሰው በዚህኛው መንገዱ ቢገፋበት ኖሮ ፍጹም አዋቂ ስለሚሆን ከሕይወት ዛፍ: በመብላት ለዘላለም ሞትን ሳያይ ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን …
❤2
12 Jul 2026, 04:00 UTC104 views1 reactionsread 8 August 2026 ✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝✞✞✞
❖ ሐምሌ ፭ ❖
✞✞✞✝ እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝
=>ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን
ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን
ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ:
ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::
+" ✝ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት✝ "+
=>የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን
ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ
ማለት ነው::
¤በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ
አድጐ
¤ሚስት አግብቶ ዕድሜ…
❤1
10 Jul 2026, 12:17 UTC89 viewsread 8 August 2026 Photo
“የተዘጋውን በር ሁሉ የሚከፍት ቁልፍ
እግዚአብሔር ነው።’’
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
3 Jul 2026, 09:31 UTC117 views1 reactionsread 8 August 2026 ✨✨✨🌿✨🌿✨🌿✨✨✨
✨ለነፍሳችን ኹለተኛዋ ነፍስ ✨
ወዳጄ ሆይ! እምነት ለነፍስህ ኹለተኛዋ ነፍስ እንደሆነች መርምርና እወቅ፡፡ ሥጋ በነፍስ እንድትቆም የነፍስም በሕይወት መኖር በእምነትህ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ እምነትህን ብትክድ ወይም ከራስህ ብታርቃት ነፍስህ ምውት ትሆናለች፡፡
በዚህም መሠረት የሚሞት ሥጋችን በነፍስ ላይ ጥገኛ እንደሆነች ነፍሳችንም በእምነት ላይ ጥገኛ ናት፡፡ እምነትም በእግዚአብሔር አብና በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን ባደረገን በእውነተኛ ልጁ ላይ ጥገኛ ናት፡፡
በዚህም እውነት ሰው ነፍሱን በሰማያት ካሉት ጋር ያገናኛታል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው በነፍሱ በሕይወት ይኖራል፡፡ በሥጋ ሰውነቱም ያያል ይመለከታል። እንዲሁ እኛም በእምነት በፍቅር…
❤1
2 Jul 2026, 14:27 UTC102 views1 reactionsread 8 August 2026 ደምጸ እገሪሁ ለዝናም
የዝናም ኮቴው ተሰማ
ከሰኔ 26 - መስከረም 25 ዘመነ ክረምት ይባላል።
እግዚአብሔር እነዚህን 3 ወራት የልምላሜ እና የመልካም ፍሬ ወራት ያድርግልን!
❤1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @gamechu_ye. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.