18 Aug 2026, 05:15 UTC≈1,010 views3 reactionsread 19 August 2026 4 years ago a friend of mine sent me this song with a caption "a song about death".
❝"ሞት አይቀርም" የሞኝ ስብከት ይመስላል። "የምናውቀውን ነገር ለምን ትነግረናለህ?" ትሉኝ ይሆናል። "የምታውቁትን ነገር ለምን አልነግራችሁም?" ብዬ እመልሳለሁ። የምናውቀውን ትረካ ውበት÷ የምናውቀውን ገላ ሙቀት÷ የምናውቀውን ፍቅር ስበት÷ የምናውቀውን ልብ እምነት÷ የምናውቀውን ቦታ ትርፍ÷ የምናውቀውን ሰው እቅፍ . . . ስንፈልግ የምንኖር አይደለንም ወይ? አለማወቅን እያሳደድን ዕውቀትን የምናደርግበት የአፍላ ጦረኝነት ዘመንስ አላለፈምን? ሲያረጁ ትዝታን ማውጋት ግድ አይደለምን?
.
.
ጌታዬ! እንደምን አሉ? እንደምን…
❤2🌚1
18 Aug 2026, 05:14 UTC987 viewsread 19 August 2026 File
File, posted without a caption
14 Aug 2026, 17:11 UTC91 views6 reactionsread 19 August 2026 ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ
እንደም'ነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ ..
ለእልፍ አእላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፀሎት ቤታችንን እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ ..
አይንህን ካየነው
ሁለት ሺህ ዘመን እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ
እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
እንደውም እንደውም..
"በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሺህ ዘመን ገትሮን ከጠፋ
በቀጠሮ ሰአት መምጣት ከተሳነው
.. እግዜር ሀበሻ ነው"
እያሉ ያሙሃል
እኔ ምን …
❤4🤔2
14 Aug 2026, 17:11 UTC85 views2 reactionsread 19 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👏2
10 Aug 2026, 17:42 UTC93 views2 reactionsread 19 August 2026 File
በገባዖን ሰማይ ÷ እምነቱን ተጠቅሞ ÷
ፀሐይዋን አስቁሞ
ተዋግቷል ኢያሱ ፤
እስኪ ተሻል ከ'ሱ!
ጭር ባለው ሌሊት ÷
ከምትወዳት ልጅ ጋር ÷ በስልት ደንሱ!..
.
.
~ ሃብታሙ ሃደራ
🔥2
5 Aug 2026, 08:32 UTC98 views3 reactionsread 19 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
🔥2👀1
1 Aug 2026, 20:19 UTC87 views2 reactionsread 19 August 2026 https://open.substack.com/pub/solyanabekele/p/an-ode-to-mikaya?r=5kveqf&utm_campaign=post&utm_medium=web
🔥2
1 Aug 2026, 08:22 UTC97 views4 reactionsread 19 August 2026 Photo
❝ግጥም
በመንተባተቤ የማያሾፍብኝ ÷ ዕብደቴን የሚረዳልኝ ÷ በሐጥያቶቼ የማይኮንነኝ ይልቁኑ እስክነፃ የሚታገሰኝ ÷ "ምን ይለኛል?" ብዬ ሳልሰጋ ምስጢሬን የምነግረው ÷ በነውሬ የማያሸማቅቀኝ ÷ ቀርፋፋ ዕድገቴን ሳይሰለች የሚጠብቅ ÷ የሚያጫውተኝ ÷ አመሌን የሚሸከምልኝና ነፃ የምሆንበት የቅርብ ጓደኛዬ ነው።
ወለዬዎች ከእንዲህ አይነቱ የልብ ጓደኛ ጋር አብሮ ሲቀማመጡ ስሜቱን እንዲህ በማለት ይገልፁታል
"እንዲህ ያለም የለም!"❞
እንዲህ ያለ አንድ ግጥም አይደለም አንድ የሚወድቅ ቃል የሌለው መፅሀፍ ከመፅሀፍ ቅዱስ በቀር ማግኘት አስቸጋሪ ነውና አይቅርባችሁ..
🔥4
31 Jul 2026, 05:31 UTC96 views2 reactionsread 19 August 2026 Photo
A shaft of light shot upward from the steel.. my eyes were blinded. I was conscious only of the cymbals of the sun clashing on my skull..
The stranger —Albert camus
🐳2
29 Jul 2026, 18:37 UTC95 views6 reactionsread 19 August 2026 ናፍቆት መላ መላ
ናፈቅሽኝ አቦ!
÷ብዬ የፃፍኩት
ኩራት ሲሰማኝ ÷ ቀድጄ ጣልኩት።
( ... )
ናፈቅከኝ በጣም
÷ብለሽ የፃፍሽው
ልምምጥ መስሎሽ
ወርውረሽ ጣልሽው።
የፍቅር ብርሃን ÷ እንዳልተሰማን
ቅር እንዳላለን ÷ እንዳልናፈቅን
በአዲስ ወረቀት ÷ ፀብ ተላላክን።
(... እንበልና ...)
እኒያ ወረቀቶች...
ቀደን የጣልናቸው
የክረምት ጎርፍ አገናኛቸው።
እስኪ አስቢያቸው...
ደራሽ ተሳፍረው ÷ ሆነው ጎን ለጎን
እርስ በርሳቸው ÷ ተያይተው ቢሆን
ምን ይሉን ይሆን?
ሃብታሙ ሃደራ
👏2😭2❤1🔥1
28 Jul 2026, 15:28 UTC80 views4 reactionsread 19 August 2026 ይህ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ ነው!
🔥4
28 Jul 2026, 14:52 UTC90 views3 reactionsread 19 August 2026 File
ሳጣሽ ያጣሁት ምኔን ነው?
አንቺን አይደለም እኔን ነው።
🔥3
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @houseofqirit. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.