4 Aug 2026, 09:17 UTC37 views2 reactionsread 6 August 2026 ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል።
«ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ።
«እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።
ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
«ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?» ይለኛል።
«ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?»
«አይ ሻማው ይሁን በቃ!» ይላል እየተቅ…
❤1😢1
Signed Betsegaw
12 Jun 2026, 19:08 UTC142 views3 reactionsread 6 August 2026 አንድ ጓድኛዬ የሁለት አመት ፍቅረኛው ታማበት ፀበል ነገር ይዟት ይሄዳል ወደ ገዳም!
እንደወሰዳትም "አንተ የseyጣን ነገር ነው መለፍለፍ ጀመረች ሳምንት እንቆያለን" ብሎ ደወሎ አሳወቀኝ!
በመጨረሻም በሳምንቱ ከፀበል መመለሱን ነገሮኝ እንገናኝ ብሎኝ ተገናኝን...
ያው እኔም እንዳገኘውት እንዴት ሆነች ተሻላት ወይ ምናምን ብየ ጠየኩት!
"አዎ!...ግን የሷን ነገር አታውራብኝ " ምናምን አለኝ
ነገሩ ግራ ሲገባኝ ምን ተፈጥረ? ምናምን ስለው ...መለያየታቸውን ነገረኝ!
ግራ ገብቶኝ የታመመች ልጅ ወስደህ ፀበል አስጠምቀሃት (seytan ኬዙ ሲሻላት ) ለምን ተለያያችሁ?... ስለው
እሱም ቀጠለና "ባክህ ከፀበል ስንወጣ 'ይቅርታ መለያየት አለብ…
🤣2❤1
Signed Betsegaw
11 Jun 2026, 07:27 UTC127 viewsread 6 August 2026 😉 ስሚ man ያች diaspora'ራዋ ወሰደችኝ እኮ, ቁንጅናዬን ይንሳኝ! ኤሄን ጭዌ ለራሱ ከdenver colorado ሆኜ ነው ምፅፍልሽ
እንዴዴዴዴ አላስታወስካትም ልጅቱዋን? እንዲያውም የሆነ ክብሮ hotel ቀጥራኝ lobster ካልጋበዝኩህ ብላኝ በuria ማዳበሪያ ይሁን በdape ማዳበሪያ ይሁን, በምን እንደፋፋ የማይታወቅ ግድንግድ በረሮ ካልበላህ ብላኝ ደንግጬ ያመለጥኩዋት ቸከስስስ? እኔ ልብላው እሱ ይብላኝ ማይታወቅ ምግብ አቅርባቡኝ!!!? ......እንዴዴዴዴ እሺ በሌላ ቀን ቀለል ያለ ምግብ ልጋብዝህ ብላ ሩዝ በ chopestick አቅርባልኝ ልበላ እንደምንም የያዝኩትን ሩዝ ልጎርስ ስል እንጨቱ አዶልጦኝ እንጥሌን ያስቦጠጠችኝ??? አዎዎዎ እሱሱሱዋ…
Signed Betsegaw
4 Feb 2026, 08:34 UTC247 views3 reactionsread 6 August 2026 Photo
ያንድ ምሽት አሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)
በሺህ ፈረስ ጉልበት፥ በሺህ ግመል አቅም
ሺህ ጊዜ ቢራመድ፥ ሰው ከቤቱ አይርቅም::
ስጥል ዋልኩኝና፥ ስወድቅ አመሸሁ
ትግሉ ሲበረታ ፥ ወደ ቤቴ ሸሸሁ ፥
ሌቱ ጣራየ ላይ ፥ እንደ እንጀራ ሰፋ
እፍ አልኩት ኮከቡን ፥ እንደ ኩራዝ ጠፋ::
እንግዲህ ምን ቀረኝ?
ምንድነው ያማረኝ?
ወገግ
ፈገግ -ልበል?
ፊትሽን አስቤ?
አልጋ ላይ ልንበልበል
እንቅልፍን ከጎሬው ፥ እንደ ጋኔን ስቤ?
ወዲህ ውብ ትውስታ፤ ወዲያ ንጹህ አልጋ
የቱ ይመረጣል? ያም ተድላ፥ ያም ጸጋ
ገላ ሲስለመለም፤ ልብ ይቀሰቀሳል
ለጊዜውም ቢሆን
እንቅልፍ እና ፍቅር መከራን ያስረሳል።፨
❤3
Signed Betsegaw
30 Jan 2026, 07:22 UTC206 views2 reactionsread 6 August 2026 Photo
ከንጹህ ቆዳ የተሰሩ ወብ ቦርሳዎች
$ 2500 birr
🛵 ነጻ ዴሊቨሪ
በብዛት ለሚረከቡ ቅናሽ ይደረጋል።
ሌሎች ቦርሳዎችን እርስዎ በሚፈልጉት ዲዛይን እንሰራለን።
አድራሻ ቦሌ
ይደውሉልን 0944354184
🥰2
Signed Betsegaw
25 Jan 2026, 16:22 UTC218 viewsread 6 August 2026 📗" ማንበብን የሚያውቅ ተራራን እንደሚወጣ ሰው ነው።
በወጣበት ልክ የሚያየው ነገር እየሰፋለት ይሄዳል።
እማራለሁ ብሎ ዘወትር ማንበብ ዕለት ዕለት ወደ ከፍታ እንደ መውጣት ያህል ነውና ብዙዎችን ነገሮች እንደ ማየት ነው።"
👉ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል👈
Signed Betsegaw
12 Nov 2025, 13:05 UTC360 views6 reactionsread 6 August 2026 ዝንብን ያስናቃት አፈጣጠሯ ሳይሆን አዋዋሏ ነው::
አዋዋል እንምረጥ🙌
❤4🥰2
Signed Betsegaw
5 Nov 2025, 14:34 UTC403 views9 reactionsread 6 August 2026 ከታላቅ ወንድሜ ጋር ነው የምኖረው።
የቤት ኪራይ እና የአስቤዛ ወጪ በእርሱ ነው። የእኔ ኃላፊነት የራሴ ወጪዎች ብቻ ነበሩ። ደሞዝ እንደተጨመረልኝ ያወቅኩ ቀን በቃ ማን ይቻለኝ...'አንተ ማን ስለሆንክ ነው ይኼን ሁሉ ወጪ የምታወጣው? እኔ ለማን ሆነና ቀን ከሌት የምሮጠው?' ተይ ግድ የለሽም ቢለኝም...የማንም ልቅምቅም የሰው ልክ አያውቅም ..ዘራፍዬዬዬ ምናምን ብዬ ወጪህን የምጋራ ነኝ አልኩ....ማን ይቻለኝ የዛን ቀን አካሄዴ ሁሉ ተቀየረ ...የቤቱን ቁልፍ ጣቴ ላይ እያሽከረከርኩ መሄድ ጀመርኩ(የባለቤትነት ስሜት ተሰማኛ)
በአንተ የአስቤዛ ዘመን እኮ የተመጣጠነ ምግብ በልተን አናውቅም...አመዳችን ቡን ብሎ የሚያየን ሁሉ ወላጅ አልባ እየመሰልነው ምፅ እያ…
❤9
Signed Betsegaw
5 Nov 2025, 14:34 UTC288 viewsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Betsegaw
9 Oct 2025, 10:03 UTC396 views4 reactionsread 6 August 2026 “ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች”
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በOctober 22, 1925 ጋንዲ (Mohandas Gandhi) በየሳምንቱ በሚያሳትመው Young India በተሰኘው የዜና መጽሔቱ ላይ “ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች” (The Seven Social Sins) የተሰኘን ጽሑፍ አስፍሮ ነበር፡፡
እነዚህ ዘመን-ዘለል እውነታዎች የግላችንንና የሕብረተሰባችንን ወቅታዊ ልምምድ በመገምገም ለማስተካከል ድጋፍ እንደሚያደርጉልን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
1. ስራ የሌለው ብልጽግና (Wealth without work)
2. ሕሊና የሌለው ደስታ (Pleasure without conscience)
3. ባህሪይ የሌለው እውቀት (Knowledge without character)
4. ግብረ-…
❤4
Signed Betsegaw
2 Jun 2025, 07:15 UTC615 views4 reactionsread 6 August 2026 የጥቁር ልብስ ልክፍት
« ለቅሶ አለብኝ... ልብስ ምረጥልኝ» ብላ የተከፈተ ቁምሳጥኗ ፊት ለፊት አቆመችኝ። የተጠቀጠቀ የጥቁር ልብስ መአአአአአት።
'ይጥቆር እንጂ ደግሞ ለለቅሶ ልብስ መረጣ የምን ቅብጠት ነው። ' አልኩ በሆዴ ... ታዝቤያት። እጄን በግዴለሽነት ሰድጄ አንዱን ጥቁር ጎተትኩትና ፊቷ ዘረጋሁት። ቀሚስ ነበር።
“ ውይ ... ይሄንን ቀሚስማ ሰዓሊው ወዳጄ ሲሞት ለቅሶ ደርሼበታለሁ ፤ አልለብስም።»
«ለለቅሶ የለበስሽውን ቀሚስ አትደግሚም? »
«ሀዘን ይደገማል? » ጥያቄዬን በጥያቄ። «በል ሌላ ምረጥ!»
ምን አከራከረኝ፤ ያነሳሁትን ወለል ላይ ጥዬ ሌላ ጥቁር መዘዝኩ። ባለአንገት ሹራብ።
«ዘፋኙ ጓደኛዬን ቀብሬበታለሁ እሱን። ቀይር»
ሆሆ…
👍2❤1😨1
Signed Betsegaw
29 May 2025, 13:12 UTC466 views5 reactionsread 6 August 2026 ዕድሜዋ ወደ አርባዎቹ እየገሰገሰ ነው....በህይወት ውጣውረድ የዛለ ፊቷ አሁንም ድረስ ድንቡሽቡሽነቱን አላጣም። ዘውትር ለብሳት በምትዞረው አንድ ሺቲ ሙሉ ከተማውን ከጫፍ እስከ ጫፍ ታካልለዋለች። ካልነኳት ማትነካ ብቸኝነትንና ባይተዋርነትን የመረጠች ብቸኛ ነፍስ ናት። ፀጉሯን ማንጨብረር ወይም እንደ 90ዎቹ አፍሮ አርጎ ማቆየት ያስደስታታል። በዛ ድንቡሽቡሽ ገጿ እና ሺ ሀሳብ ቢያጠቃውም ፍንክች ባላለ ሰውነቷ እዚህም እዛም ትባዝናለች።
.
" ሰሚራ " ማህበረሰቡ እብድ የሚል ቅፅላ ሰጥቶ ቢያገላትም ፤ ለኔ ግን የተነጠቀችው ወጣትነት ፤ የተነጠቀችው ህልሟ ጎልቶ ይታየኛል። እደርስበታለሁ ካለችበት ፤ እኖረዋለሁ ካለችው ህይወት ተብትቦ ያደናቀፋት ማህበረሰብ ቀፅላ…
❤4👍1
Signed Betsegaw
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @maninet1. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.