7 Aug 2026, 08:54 UTC516 views84 reactionsread 8 August 2026 ፍልሰታ..!
አልላቀቅ ያለንን ክፉ አመል እና እንተወዋለን ብለን ስንቴ የማልንባቸው እና ወስነን እንደገና ለተመለስንበት ልማድ እና ሱስ በእውነት እመቤታችን ትንቀልልን በዚህች ጾም። ሳታቋርጡ ጸልዩ፣ ጹሙ፣ ህዋሳቶቻችሁን እና ፍላጎታችሁን ገድቡት፣ ንስሐ ግቡ፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀበሉ።
በተለይ ወጣቶች ይህችን የጾም ወቅት ጌታ ይርዳን ምንለወጥበት ይሁንልን።
https://t.me/orthodox_chrstianity
❤64🥰7👏3😇3😭3❤🔥2👍1🔥1
6 Aug 2026, 19:19 UTC926 views88 reactionsread 8 August 2026 🥹🥹🥹
ወፌ ሰንብታ ሰንብታ፥ መጣች ለፍልሰታ፥
ሀገርሽ የት ነው? ኤፍራታ፥ አሳድሪኝ ማታ፤
ይናፍቀኛል ሌሊት፥ የሰማይ እልፍኝ ሌሊት፥
ወፌ የ'ኔ እመቤት፤ [×2]
በክንፍሽ ጥላ ጋርደሽኝ፥
ከልጅሽ ስፍራ ወስደሽኝ፥
እንዳልቆምብሽ በግራ፥ እንዳያሰቃየኝ መከራ ፥ ወፌ ነፍሴን አደራ [×4]
እያሉ እናቶቻችን በዝማሬ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ይቀበላሉ። እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላም እና በጤና አደረሰን!
https://t.me/orthodox_chrstianity
❤60🥰17❤🔥5😍3🔥2😭1
6 Aug 2026, 09:18 UTC899 views31 reactionsread 8 August 2026 ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላችሁ ...!
በትናንትናው ስብርባሪ ውስጥ ሆነው የነገውን አዲስ ቀን ተስፋ ለማድረግ ለሚታገሉ ልቦች አሉ። አንዳንድ ጊዜ የሕይወት አውሎ ነፋስ ከበድ ይላል፤ የምንሸከመው ሕመም ከእኛ አቅም በላይ የሆነ ይመስላል። ነገር ግን እግዚአብሔር የረሳችሁ እንዳይመስላችሁ። እርሱ ዕንባችሁን ያያል፤ የልባችሁን ፀጥተኛ አውሎ ነፋስና እንግልት ሁሉ ያውቃል። ከዚህ ውጣ ውረድ በኋላ፣ ከዚህ ከበደኝ ከሚል ጭንቀት በኋላ የሚመጣ አንድ ትልቅ የመጽናናት ዘመን አለ። በልባችሁ ውስጥ ያለውን ባዶነት በሰላም፣ በስብርባሪያችሁ ላይ ደግሞ አዲስ ውበት የሚያደርግበት ጊዜ ደርሷል።
የዛሬው የታከታችሁ መንገድ ያልቃል፤ ሰማያዊው እፎይታ ደግሞ…
❤26🥰3😭2
6 Aug 2026, 04:45 UTC867 views41 reactionsread 8 August 2026 ፍልሰታን እንዴት እንጹም ???
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለተወዳጇ ተናፋቂዋ ልጅነታችንን ለምታስታውሰን ጾመ ማርያም 🥰
እንግዲህ ፍልሰታ በቤተክርስቲያናችን እንዲጾሙ ከተደነገጉ 7ቱ አጽዋማት መኻል አንዱ ነው፥ እናም ይህችን 16 የጾም ቀናት እንዴት እናሳልፍ ?
፩- ህዋሳትን ማጾም፦
ዓይናችንን በፈቃዳችን ክፉ ከማየት መከልከል፥ ጆሯችንን በፈቃዳችን ክፉ ከመስማት መከልከል፥ አፍንጫችንን በፈቃዳችን ፍላጎት ቀስቃሽ የሆኑ ሽታዎችን ከማሽተት መከልከል፥ እግራችንን በፈቃዳችን ወዳልተገባ ቦታ ከመሄድ መከልከል እና እጃችንንም በፈቃዳችን ያልተገባ ነገር ከመንካት በመከልከል ማለት ነው።
፪- ከቅዳሴ መሳተፍ እና ቅዳሴውን ማጣጣም፦
ቅዳሴ ሰማይና ምድር በአምልኮ…
❤33❤🔥4🥰4
5 Aug 2026, 19:31 UTC692 views26 reactionsread 8 August 2026 ዕድሜ በቁጥር ቢቆጠርም መጨረሻው አንድ መንገድ ነው። ዋናው ጥያቄ 'ምን ያህል ኖርን?' ሳይሆን 'ለማይቀረው ዕለት ለነፍሳችን ቤዛ የሚሆን ምን አዘጋጀን?' የሚለው ነው።
እንሞታለን ሁሉንም ነገር ጥለነው እናልፋለን !
https://t.me/orthodox_chrstianity
😢17❤9
5 Aug 2026, 11:29 UTC739 views26 reactionsread 8 August 2026 'በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለአብ የምናቀርበው እያንዳንዱ ጸሎት ከክርስቶስ ልብ ፈልቆ ወደ እኛ ልብ የሚፈስ አንድ አይነት መንፈሳዊ ኃይል ነው። ይህ በውስጣችን ሰርጾ በመግባት በነፍሳችን ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ያርፋል። ወደ አባታችን ቤት እስኪያደርሰንም ድረስ ከእኛው ከራሳችን በላይ ከፍ ከፍ ያደርገናል።'
[✍️አባ ማቴዎስ ምስኪኑ ፥ Orthodox Prayer Life]
https://t.me/orthodox_chrstianity
❤22🥰3😍1
5 Aug 2026, 05:27 UTC768 views45 reactionsread 8 August 2026 Photo
ዛሬ የባባ ቄርሎስን መታሰቢያቸውን ምናደርግበት እና ምናስብበት ቀን ነው። ባባ ካደረጉት ተዓምር መካከል ለአንዲት ልጅ ያደረጉትን ተዓምር ከዚህ በታች ተርጉሜዋለው።
በ1989 (እ.ኤ.አ) ታናሽ እህቴ በጽኑ የአለርጂ በሽታ ትቃጠል ነበር፤ ይህም በቆዳዋ ላይ የሚወጡትን እብጠቶች ደም እስኪወጣቸው ድረስ እንድትፋቅ ያደርጋት ነበር። ሁኔታዋ የሚያክሟትን ሐኪሞች ጨምሮ ለሚያያት ሁሉ የሚያስጠላ ነበር። ቆዳዋ ተመርምሮ በርካታ መድኃኒቶች የተጻፉላት ቢሆንም የ37 የቆዳ ሕክምና (Dermatologist ) ምርመራ ምንም ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም።እኛ ስንሰደድ እህቴ ገና የ5 ዓመት ልጅ ስለነበረች ስለ ባባ ቄርሎስ አታውቅም ነበር፤ ስለዚህ እሳቸው ስለ እሷ እንዲ…
❤36❤🔥8🔥1
4 Aug 2026, 17:00 UTC967 views43 reactionsread 8 August 2026 ሞት ⚰⚰ !!
ባንወደውም ዕለት ዕለት የምንጓዘው ወደ ሞት ነው፣ ሞት የኋላ ዕዳ ነው። የሚገርመው ሟች ሰው ሰውን መግደሉ ነው። ከቃሉ ያልተማረ ከሞትም አይማርም።
ለእነ እገሌ ያልሆነ ዓለም ለእኔ ይሆናል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። የፍርድ ቤት ጥሪ ከአገር ቢወጡ ያመልጡታል፣ የምርቃት ጥሪ ካልፈለጉ ይቀሩበታል ፥ የሞት ጥሪ ግን ያለ ምክንያት ይሄዱበታል።
ያን ቀን እንቢ ላንል ዛሬ ለንስሐ እንቢ ማለታችን ይገርማል። ሞት እያንዣበበን ንስሐ ካልገባን መቼ ልንገባ ነው ? እነ እገሌ በሞኝነት ሞተው እኛ በብልጠት አልቀረንምና ንስሐ እንግባ፣ እንታረቅ ።
እግዚአብሔር ትክክለኛውን የፍርድ ሚዛን ለሞት አስጨብጦታል። ባንወደውም ዕለት ዕለት የምንጓዘው ወደ ሞት ነ…
❤34😢7❤🔥1🥰1
4 Aug 2026, 12:29 UTC800 views26 reactionsread 8 August 2026 Posted without readable text
❤26
4 Aug 2026, 06:17 UTC985 views42 reactionsread 8 August 2026 አብዛኞቻችን የንስሀ አባት የሉንም ቢኖሩንም ካገኘናቸው ዓመት አልያም ሁለት ዓመት ሆኖናል። መንገድ ላይ ስናገኛቸው ለመደበቅ ሞክረናል ሲፈልጉን ሸሽተናል ሲቀርቡን ርቀናል፣ ሲጠጉን ከፍቶናል፣ ሲመክሩን ጨንቆናል፣ ሲያናግሩን ለይምሰል 'እሺ እሺ' ብለን ፀጉራችንን ዳብሰናል...!
የራሳችንን ዶክተር ይዘን ከህመማችን ጋር መለያየት ላልፈለግን ለኛ ለሚስኪኖቹ መድኃኒታችን ምን ይሆን ??
ንስሐ ግቡ ህያው የሆነውን የጌታን ሥጋ እና ደም ተቀበሉ፣ ክርስቶስንም ልበሱ ወጣትነታችንን በከንቱ አናሳልፍ ዛሬ ካልነቃን ነገ ከረፈደ እናለቅሳለን !
https://t.me/orthodox_chrstianity
❤33❤🔥6🥰3
3 Aug 2026, 17:23 UTC848 views52 reactionsread 8 August 2026 ጌታ ቢፈቅድ
በጣም ብዙ ብልህ ሰው ልታውቁ ትችላላችሁ። ነገር ግን ''ጌታ ቢፈቅድ'' በምትል ቃል ሕይወቱን ከሚመራ ሰው በላይ ብልህ የለም!
ጌታ ቢፈቅድ የምንለው የህይወታችን እስትንፋስ ሰጪው እርሱ በመሆኑ ነው። ባልሰጠን ነገር ላይ የሚያዝበት አካል የለም ስለዚህ በሰጠን ህይወት ላይ ሊያዝበት የሚችለው ጌታ ነው።
የሚሰራትን፤ የሚከውናትን ስለ ነገው ሰለ ወደፊቱ ተግባሮቹ በሙሉ 'ጌታ ቢፈቅድ' እያለ ተስፋውን በሰው፣ ተስፋውን በገንዘብ ሳይሆን ተስፋውን በእግዚአብሔር ያደረገን ሰው መቼም ልትበልጠው አትችልም።
“ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።”
[ ✍️ያዕቆብ 4፥15]
https://t.me/orth…
❤38🥰14
3 Aug 2026, 15:55 UTC791 views22 reactionsread 8 August 2026 ከጋብቻ በፊት ሚደረግ propose በነገራችን ለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተከለከለ እና ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ውጭ ነው።
ቤተክርስቲያን የምታውቀውና የምታከብረው ብቸኛ የቃል ኪዳን ማሰሪያ (Propose) በነፍስ አባት መሪነትና በቤተሰብ ምርቃት አልፎ፣ በቤተ መቅደስ በቅዱስ ቁርባን የሚታተመውን ታላቁን ምስጢር ብቻ ነው።
ከዚህ ውጭ ከባህልም ከቤተክርስቲያንም ውጭ ነው !
https://t.me/orthodox_chrstianity
❤🔥12❤10
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @orthodox_chrstianity. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.