31 Jul 2026, 06:47 UTC263 views4 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7
📖 ከዛሬው ንባቤ ያገኘኋቸው 5 ወርቃማ አባባሎች ✨
አንዳንድ አባባሎች ጥቂት ቃላት ሆነው ሳለ፣ የብዙ ዘመናት ልምድና ጥልቅ እውነትን ይዘው እናገኛቸዋለን። ከዛሬው ንባቤ ልቤን የነኩትን አምስት እውነቶች አካፈልኳችሁ፦
1️⃣ «ሊሄድ የፈለገ ሰበቡ ብዙ ነው።»
2️⃣ «ካለቀ በኋላ አስተያየት የሚሰጥ ብዙ ነው።»
3️⃣ «ሰዎች ይሁዳ መባልን ይጠላሉ፤ መሆንን ግን አይፈሩም።»
4️⃣ «ከሐሰተኛ ተስፋ ጥሩ ተግሣጽ ይበልጣል።»
5️⃣ «የከዳ ወዳጅን መቅጣት ለሚያውቀውም ለሚያየውም መልካም አይደለም፤ ሥራው ይግለጠው እንጂ ስለ ከዳን ሰው ማውራት ተገቢ አይደለም።»
💭 ከእነዚህ አባባሎች መካከል የእርስዎን ልብ የበለጠ የነካው ወይም ጥልቅ መልእክት አለው ብለው ያ…
❤4
30 Jul 2026, 12:45 UTC316 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7Poll
የኅሩያንን ሕይወት» መጽሐፍ ለማሳተም በቀን በ225 ብር (ለ1 ወር) የሚሳተፉ 10 የቅድስና አርበኞች አባል ለመሆን ዝግጁ ነዎት? (ቦታው ለ10 ሰዎች ብቻ የተወሰነ ነው!)
- ✋ እኔ ዝግጁ ነኝ! (ከ10ሩ አንዱ እሆናለሁ)9%
- ✅ የአንድ ጊዜ መዋጮ አደርጋለሁ በቋሚነት ሳይሆን91%
Shares as published. No per-option vote count is published by Telegram, so none is shown.
30 Jul 2026, 11:31 UTC285 views0 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7
«10 የቅድስና አርበኞች ፍለጋ፦ በቀን በ225 ብር "የኅሩያንን ሕይወት" እናሳትም!» 💪📖
✨ 67,500 ብር ሲታይ ትልቅ ቁጥር ይመስላል አይደል? 🤔
ግን እስኪ ነገሩን ቀለል አድርገን በሒሳብ እንስበረው፤ በእርግጥ በጣም ትንሽ ነው! 👇
▪️ 67,500 ብር ለ1 ወር (30 ቀን) ሲካፈል ➔ በቀን 2,250 ብር
▪️ 2,250 ብር ደግሞ ለ10 ሰው ሲካፈል ➔ በቀን 225 ብር ብቻ!
ይህ ማለት በቀን የአንድ ቡና ወይም ቁርስ ያህል (225 ብር) ለ1 ወር ብቻ በቋሚነት በማዋጣት «የኅሩያንን ሕይወት» መጽሐፍ አሳትመን ለትውልድ ማብቃት እንችላለን! 📖🔥
🎯 አሁን የሚፈለጉት፦
ይህን ታላቅና ቅዱስ ዓላማ በጋራ ለማሳካት የወሰኑ 10 የቅድስና አርበኞች ብቻ …
30 Jul 2026, 06:23 UTC258 views2 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7
ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ቁጥር 4
ጥያቄ፦
"ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ወሲብ መጥፎ ከሆነ፣ ታዲያ ለምን በጣም ደስ የሚል ጥሩ ስሜት ይሰጣል?"
መልስ፦
አንድ ድርጊት የሚያስገኘው ሥጋዊ ደስታ ወይም ጥሩ ስሜት ብቻውን የድርጊቱን ትክክለኛነትና ሥነ-ምግባራዊነት ሊወስን አይችልም።
1. ስሜትና ሥነ-ምግባር የተለያዩ ናቸው
የስሜት ደስታ መልካምነትን አይገልጽም፦ አስገድዶ ደፋሪዎች ወይም ሕፃናትን የሚያንገላቱ አካላት ከድርጊታቸው ሥጋዊ ደስታን ያገኙ ይሆናል፤ ነገር ግን ድርጊታቸው እጅግ አሰቃቂና ኃጢአት መሆኑን ማንም አይጠራጠርም።
ሕመም ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም፦ በአንጻሩ፣ አንድ ሰው ለሌላው ሲል ሕይወቱን አሳልፎ ሲሰጥ ከፍተኛ ሥቃይና ሕመም ይደርስበታል። ነገ…
❤2
29 Jul 2026, 14:39 UTC231 views3 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7
ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ቁጥር 3
ጥያቄ፦
"ዘመኑ ተቀይሯል፤ ሰዎች በወሲብና በሥነ-ምግባር ረገድ የየራሳቸው የሆነ የተለያየ እሴትና እይታ (values) ቢኖራቸው ምን ችግር አለው? መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት ዘመን አሁን አኗኗራችን ስለተቀየረ፣ በወሲብ ጉዳይም ቢሆን የሰዎችን የተለያየ ፍላጎትና እይታ መቀበል የለብንም?"
መልስ፦
"ዘመኑ ተቀይሯል" በሚል ምክንያት መልካምና ክፉን፣ እውነትና ሐሰትን እንደ አመለካከታችን ለመተርጎም መሞከር ትልቅ አደጋ አለው። "የሰዎችን የተለያየ እሴት መቀበል አለብን" የሚለው አስተሳሰብ መጨረሻው የት እንደሚያደርስ በጥልቀት ማሰብ ያስፈልጋል።
1. የሥነ ምግባር አንጻራዊነት (Relativism) አደጋ
አንድ በዩናይትድ ስቴ…
👍1👏1🙏1
29 Jul 2026, 14:10 UTC219 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7
ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ቁጥር 2
ጥያቄ፦ "አንዲት ገና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጀመረች ጓደኛ አለችኝ። ከጋብቻ በፊት ወሲብ መፈጸም ጥሩ እንደሆነና እሷም ልታደርገው እንደሆነ እያወራችኝ ነው። ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ወሲብ ጉዳቱ ምንድን ነው? ለእሷስ እንዴት ማስረዳት እችላለሁ?
መልስ፦ ጓደኛሽ በውስጧ በጥልቀት የምትፈልገው የብዙ ወንዶችን አካላዊ ግንኙነት ሳይሆን እውነተኛ ፍቅርን፣ ትኩረትን እና ደኅንነትን ነው። ብዙ ወጣቶች ለጊዜያዊ ፍላጎታቸው ሲሉ "እወድሻለሁ" ሊሉ ይችላሉ፤ እሷም እንደተወደደች በማሰብ አካሏን አሳልፋ ለመስጠት ልትነሣሣ ትችላለች።
ነገር ግን ልቧ ከዚያ በላይ ትልቅ ዋጋ አለው! ወሲብ በራሱ መጥፎ ስለሆነ ሳይሆን እውነተኛ ፍቅር…
❤1
28 Jul 2026, 06:24 UTC291 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7
📌 ለጥያቄዎቻችሁ መልስ
1) አንድ ወንድ ከጋብቻ በፊት ከጾታዊ ግንኙነት (ወሲብ ከፈጸሙ) በኋላ ለምን ይሸሻል?
አንድ ወንድ ለአንዲት ሴት ጥልቅ ፍላጎት እንዳለው አሳይቶ፣ አብሯት ከተኙ በኋላ ግን እንደማያውቃት የሚሆነው ለምንድን ነው?
እንዲህ ዓይነቱ ወንድ የሴቷን ልብ የመጠበቅና የመንከባከብ ምንም ዓይነት ፍላጎት የለውም። የእርሱ ግብ አካላዊ ፍላጎቱን (ሴክስ) ማርካት ብቻ ሲሆን፣ የእሷ ግብ ደግሞ ጥልቅ የልብና የስሜት መቀራረብ ነበር። እርሱ የፈለገውን አግኝቷል! እሷን ለማግኘት ያደረገው የጉጉትና የፍለጋ ውድድር ተጠናቋል፤ ለእሷ የነበረውም አክብሮት አብሮ ጠፍቷል። እሷ ለእርሱ ማራኪ ሆና የታየችው ልትገኝ የማትችልና ሩቅ ሆና ሳለች ብቻ ነበር።
በ…
❤1
27 Jul 2026, 10:03 UTC409 views0 reactionsread 7 August 2026 Photo
📚 ትውልድን የመታደግ ጥሪ — ለ«ኅሩያን ሕይወት ማሳተሚያ» 📚
«የጨለማው ዓለም ለኃጢአት ሥራ በጀት አለው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ደግሞ ለጽድቅ በጀት አለው!»
ሰላም ወጣቶች! 👋
ይህን ትውልድ ከመንፈሳዊ ውድቀትና ከሱስ ለማዳን በሚደረገው ታላቅ ተጋድሎ ውስጥ የእናንተ እገዛና አብሮነት እጅግ ወሳኝ ነው!
የ «የፖርኖርሽኝ» መጽሐፍ ሁለተኛ ዕትም ገበያ ላይ ውሏል። ይህንን መጽሐፍ በመግዛትና በማሰራጨት ለኅሩያን ሕይወት ማሳተሚያ አገልግሎት ታላቅ ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።
🔥 በዚህ ትውልድን የማትረፍ ሥራ ላይ ሁላችንም እንረባረብ!
እንዴት መተባበር እንችላለን?
💰 ገንዘብ ያላችሁ፦ መጽሐፉን በመግዛት፣ እንዲሁም ለሌሎች ወጣቶች በስጦታ በማበርከት…
27 Jul 2026, 05:00 UTC407 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
ሰላም ቅዱሳን! እንዴት ናችሁ? 🙏 በወሲባዊ ቅድስና ዙሪያ የጻፍኩትን ሁለተኛ መጽሐፍ ለማሳተም የገንዘብ ድጋፍ በደንብ ያስፈልጋል💸። እስከአሁን የተደረጉት ቅድመ ሽያጮች በቂ አይደሉም። ስለሆነም፣ በገንዘብ በመደገፍ ለትውልድ መታነፅ አሻራችሁን ማኖር የምትፈልጉ ሁሉ በዚህ አካውንት 1000297589548 መላክ ትችላላችሁ💳። ለትውልድ መታነጽ ስለምታበረክቱት አስተዋጽዎ ጌታ ይባርካችሁ🙏✨
ይኽን መልእክት ለብዙዎች እንዲደርስ ቻናሉንም ሼር አድርጉት።
❤1
26 Jul 2026, 13:16 UTC445 views9 reactionsread 7 August 2026 ✨ እውነተኛው የክብራችን ልኬት
ቅዱስ ሆኖ የኖረ ሰው ወደ ኃጢአት አዘቅት ሊወድቅ እንደሚችል ሁሉ፣ በኃጢአት የወደቀ ሰውም ወደ ቅድስናና ንጽሕና የመመለስ ተስፋ አለው። በእውነት ንጹሕ ለመሆን ልብን ፍጹም አድርጎ ወደ እግዚአብሔር ማቅናት ግድ ይላል።
በእግዚአብሔር ፊት፣ በንስሐ የተመለሰችው አመንዝራ በፍትወትና በምኞት ከተሞላችው ድንግል ይልቅ ይበልጥ የጠራችና ንጹሕ ናት።
ዘወትር ልናስታውሰው የሚገባው ትልቅ እውነት ቢኖር፦ የዋጋችንና የክብራችን ልኬት እግዚአብሔር እኛን በሚያይበት አመለካከት ላይ የተመሠረተ እንጂ፣ ሰዎች በሚያዩን ወይም እኛ ራሳችንን የምንመዝንበት መነጽር አለመሆኑን ነው!
❤9
18 Jul 2026, 05:41 UTC603 views3 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7Photo
የመጨረሻ ቅድመ ሽያጭ ላይ እንገኛለን። ያላዘዛችሁ ፈጥናችሁ እዘዙን። ከቅድመ ሽያጭ በኋላ የመጽሐፉ መሸጫ ዋጋ ይጨምራል።
Cbe: 1000297589548
telebirr: 0986552076
600 Etb/ $25
❤3
9 Jul 2026, 09:36 UTC818 views15 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @puritymatters7
ብዙዎች ዝሙትን የሚሸሹት እግዚአብሔርን ከማፍቀርና በርሱ ከመደሰት የተነሣ ሳይሆን፣ “ነገ ትዳሬ እንዳይበላሽ፣ ወሲባዊ ርካታዬን እንዳላጣው” በሚል ጥቅም ተኮር ፍልስፍና (Utilitarianism) ነው። ኀጢአትን የሚሸሹት አምላክን ስለሚያሳዝን ሳይሆን፣ የኅሊና ወቀሳንና የጥፋተኝነት ሥቃይን ለመሸሽ ብቻ ነው (Hedonistic avoidance)። ወይም ደግሞ ፍቅረ ሥላሴ እና ትኲስ መለኮታዊ ኅብረት በሌለው፣ ፍርሃትና ደረቅ ግዴታ በነገሠበት የሕግጋት እስር ቤት ውስጥ ሆነው ቅድስናን ለመጠበቅ ይውተረተራሉ (Deontological Legalism)። ይኽ ግን መንፈሳዊ ድንቁርና ነው። ክርስቲያናዊ ቅድስና ጥቅመኛም፣ ስሜት አሳዳጅም ወይም ደረቅ የሕግ ግዴታም አይደለ…
❤15
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @sexualpurity. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.