27 Aug 2026, 07:23 UTC769 views21 reactionsread 29 August 2026 Photo
❝ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወአስተበርክ ክሡተ
ቅድመ ማኅበራንኪ እሉ እንዘ እቀውም ድርገተ
ፈጻሚተ መፍቅድ ማርያም እስእለኪ ስእለተ
ጸግውኒ እግዝእትየ ለዓለመ ዓለም ሕይወተ
እምእደ እኩያን አጽራርየ አድኅንኒ ሊተ❞
...
በእነዚህ የአንቺ ማኅበር በሚሆኑ ጉባኤያተኞችሽ መካከል በአንድነት እየቆምኩ በሥዕልሽ ፊት እሰግዳለሁ፤ በግልጽም እንበረከካለሁ፡፡ የልቤን መሻት የምትፈጽሚልኝ ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ፤ እመቤቴ ሆይ፥ ለዘለዓለሙ ሕይወትን ስጪኝ፥ ከክፉ ጠላቶቼ እጅም አድኚኝ።🙏
እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓል 21🥰
📍 የ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ጉባኤ📍
❤19🙏2
23 Aug 2026, 13:56 UTC≈1,710 views27 reactionsread 29 August 2026 የሚያውከን ነገር የለም፡፡
ለእኛ ለኦርቶዶክሳዊያን ድንግል ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገር የነበራትን የክብር አቀባበል በሕሊናችን ከማሰብ በቀር ምንም የሚያውከን ነገር የለም፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ድንግልን ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? እዚህ ‹ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ› ብሎ ሰላምታ ያቀረበላት ይህ መልአክ ጸጋን የተሞላችው ወደ እርሱ ስትመጣ ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን?
ቅድስት ኤልሳቤጥስ አሁንም ‹ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?› ብላት ይሆን? መጥምቁስ ዳግም በሰማይ በደስታ ዘልሎ ይሆን? ነቢያቱ ድንግልን እንዴት ተቀበሏት? ኢሳይያስ ‹ትፀንሳለች› ያላትን ድንግል ሲያያት ምን ይል ይሆን?
ሕዝቅኤልስ ‹የተዘጋችዋ ደጅ› ወደ እርሱ ስትመ…
❤26🥰1
22 Aug 2026, 08:48 UTC≈1,810 views40 reactionsread 29 August 2026 Photo
እንኳን ለፍልሰታ ለማርያም በሰላም አደረሳችው
"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል፤ የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ፀጋ ግን የለኝም።
እናቴ ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ …
❤36🙏4
21 Aug 2026, 12:31 UTC≈1,560 views25 reactionsread 29 August 2026 Photo
"... እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ወተወልደ እምኔኪ ቃለ ጽድቁ ለአብ፤ማርያምሰ ተሐቱ ዉስተ ከርሡ ለአዳም፤ከመ ባሕርይ ፀዓዳ፤ ፆረቶ እግዝእቱ ለአዳም ..."
ዋይዜማ ዘነሐሴ ኪዳነ ምሕረት
"... እመቤቴ እልሻለሁ ፤ የጌታዬ እናት እልሻለሁ ፤ የአብ የጽድቅ ቃል ክርስቶስ ካንቺ ተወልዶልና ፤ ማርያም በአዳም ሰውነት ውስጥ እንደ ነጭ እንቊ ታበራ ነበር ፤ የአዳም እመቤት ጌታን ተሸከመችው ..."
📍 የ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ጉባኤ📍
❤23🙏2
18 Aug 2026, 19:33 UTC≈2,020 views19 reactionsread 29 August 2026 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
📚በእንተ ፍልሰታ ለማርያም📚
✨ቅዳሴ ማርያም✨
⚡️አባ ሕርያቆስ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም⚡️
ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኀያል እመንበሩ፡፡
የሰው ፍቅር ከክቡር ከልዑል ባሕርዩ ወደዚህ ዓለም አመጣው:: አንድም የሰው ፍቅር ከብርሃናማው ዓለም ወደ ጨለማው ዓለም፥ ከሰፊው ዓለም ወደ ጠባቡ ዓለም ስቦ አመጣው፡፡ አንድም በቁሙ ከልዑል ዙፋኑ ጎትቶ አወረደው፡፡
ወአብጽሖ እስከ ለሞት፡፡
ለሞትም አደረሰው፤ አንድም ምን አደረገው ያልከኝን እንደሆነ ከዚህ ሁሉ ያደረሰው ማን ሆኖ ፍቅረ ደቂቀ ዕጓለ እመሕያው ነው እንጂ::
ኦ ላህም ዘኢይትሄየል በቀርኑ ለእለ ይስሕብዎ፡፡
ሲስቡት ሲጎትቱት በቀንዱ የማይበረታታ ላህም ምን ይረቅ …
❤15🙏4
15 Aug 2026, 06:49 UTC≈2,610 views19 reactionsread 29 August 2026 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
📚በእንተ ፍልሰታ ለማርያም📚
✨ቅዳሴ ማርያም✨
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይሠምሩ።
ሠምሩ ሲል ነው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይህን ዓለም እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ካለመኖር ወደ መኖር ካለመታየት ወደ መታየት አምጥተው የበቃ የነቃ አድርገው ፈጠሩ፤ ወርእየ እግዚአብሔር ኵሎ ዘፈጠረ ከመ ሠናይ እንዲል፡፡
አንድም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይኄልዩ᎓᎓ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አዳምን እንፍጠር ብለው አሰቡ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይትናገሩ፡፡ ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ ብለው ተናገሩ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠምሩ፤ አዳምን ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከአምስተኛ ባሕርየ ነፍስ ፈጠሩ፡፡
አንድም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይኄ…
❤18✍1
13 Aug 2026, 08:51 UTC≈2,580 views34 reactionsread 29 August 2026 Photo
❝ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ — ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም። በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ❞
— ቅዳሴ ማርያም
ድንግል ዘርዕ ዘይወጽእ እምስካበ ተዓዳዌ ሕግ ይከውን ለቅጥቃጤ ወለሙስና ባለው ፈቃድ የተጸነሽ አይደለሽም። አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ።
❝ክቡር አውስቦ በኵለሄ ወለምስካቦሙኒ አልቦ ስዕበት❞
ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡
[አንድም]:
❝እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ ወበዓመፃ ወለደተኒ እምየ❞ እንዲል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት (መዝ. ፶)፡ በልተው ጠጥተው በሚያደርጉት ፈቲው ጽነት የተጸነሽ አይደለሽም። ለአብርሃም ❝ብዝኁ ወተባዝኁ ... ❞ ባለው ፈቃድ…
❤31✍3
8 Aug 2026, 08:57 UTC≈3,250 views9 reactionsread 29 August 2026 Photo
ዛሬ ማታ 2:00 በ ጭራሽ አይቀርም share በማድረግ ለሁል እናዳርስ
ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት መከታተል ትችላላችሁ!
👉Link👈
መልካም የ ሱባኤ እና የ ፆም ጊዜ ይሁንልን!!
የ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ጉባኤ!!
❤9
6 Aug 2026, 23:37 UTC≈3,180 views53 reactionsread 29 August 2026 File
እንኳን ለጾመ ማርያም አደረሳችሁ
እንደምታውቁት በዚህ ጾም ሌሊቱን ሙሉ ሰአታት በተባለው የቅዱስ አባ ጊዎርጊስ ዘጋስጫ ምስጋና እግዚአብሔርን እያመሰገንን እናድራለን ። ሰአታቱ ብዙ ቦታ ከማታ 4 ሰአት እስከ ጠዋት 11 ነው በዋነኝነት ካህናት እና ዲያቆናት ናቸው የሚቆሙት ፤ ሲነጋ ደግሞ መሪጌቶች ስብሐተ ነግህ ያደርሳሉ ፤ ከዛ ረፈድ ሲል የመጽሐፍ መምህራን ውዳሴ ማርያም ይተረጉማሉ ... ከዛ ወደ ቅዳሴ
እና በተቻለን አቅም ሌሊት በሰአታት ቀን በቅዳሴ ለመትጋት እንሞክር ።
ከተወደደች እመቤታችን ረድኤት፤ በረከት፤ ፍቅር አይለየን ።
❤46🙏6🔥1
6 Aug 2026, 06:12 UTC≈3,280 views34 reactionsread 29 August 2026 ፍልሰታን እንዴት እንጹም ???
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለተወዳጇ ተናፋቂዋ ልጅነታችንን ለምታስታውሰን ጾመ ማርያም 🥰
እንግዲህ ፍልሰታ በቤተክርስቲያናችን እንዲጾሙ ከተደነገጉ 7ቱ አጽዋማት መኻል አንዱ ነው፥ እናም ይህችን 16 የጾም ቀናት እንዴት እናሳልፍ ?
፩- ህዋሳትን ማጾም፦
ዓይናችንን በፈቃዳችን ክፉ ከማየት መከልከል፥ ጆሯችንን በፈቃዳችን ክፉ ከመስማት መከልከል፥ አፍንጫችንን በፈቃዳችን ፍላጎት ቀስቃሽ የሆኑ ሽታዎችን ከማሽተት መከልከል፥ እግራችንን በፈቃዳችን ወዳልተገባ ቦታ ከመሄድ መከልከል እና እጃችንንም በፈቃዳችን ያልተገባ ነገር ከመንካት በመከልከል ማለት ነው።
፪- ከቅዳሴ መሳተፍ እና ቅዳሴውን ማጣጣም፦
ቅዳሴ ሰማይና ምድር በአምልኮ…
❤26🙏8
5 Aug 2026, 03:06 UTC≈2,910 views16 reactionsread 29 August 2026 📍ምፅዋት 📍
ምፅዋት ማለት ዝም ብሎ የተረፈንን ወይም ያነሰንን ገንዘብ ለሌላው መስጠት ብቻ አይደለም። ምፅዋት የፍቅር፣ የርህራሔ እና የሃይማኖታዊ ተግባራዊ መገለጫ ነው። የእኛ የሆነው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ተረድተን፣ ከእኛ ለጎደላቸው ወንድሞችና እህቶች የማካፈል ግዴታችን ነው።
ሊቁ ቅዱስ አባ ይሩማሲስ [ጄሮም] [st.jerome]እንዲህ ይለናል ስለ ምጽዋት
“የሚምሩ ብፁዓን ናቸው ምሕረትን ያገኛሉና” እና “ውሃ የሚንበለበለንን እሳት ያጠፋል ምጽዋትም የኃጢአትን ማስተሰረያ ያደርጋል” የሚሉ ሐረጎች በከንፈሮቿ ላይ ያለማቋረጥ ይወጡ ነበር። ....እና ምጽዋትን ስጡ ... እና እነሆ ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው;" ዳንኤልም ለንጉሥ ናቡከደነፆር…
❤16
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ pinned a photo
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @wku_gg_media. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.