3 Aug 2026, 11:49 UTC728 views13 reactionsread 8 August 2026 Video
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ተማሪዎቹ እየደረሰባቸው ስላሉ የመብት ጥሰቶች አቤቱታ ለማቅረብ ከ20 በላይ ተቋማት ዘንድ ሄዶ ነበር። ቅሬታዎቹ፤ ብሎም የተቋማቱ ምላሽ ምን ነበር ስለሚለው በቅርቡ በትንታኔ የሚቀርብ ይሆናል።
እስከዚያ https://www.tiktok.com/@aaumsu/video/7669761759632264469?is_from_webapp=1&sender_device=pc በመግባት መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ እናድርግ።
እኛ የጥያቄ አለን ትውልዶች ነን!
https://t.me/EHEMSU
🔥7❤4🤬2
26 Jul 2026, 05:36 UTC≈1,490 views13 reactionsread 8 August 2026 Video
"ሴኩላሪዝም አልጠራልንም። ሴኩላሪዝም Atheism (ሀይማኖት የለሽነት) የሚመስላቸው አሉ። አንድ ተማሪ አልሐምዱሊላህ ሲል ሴኩላሪዝም የተጣሰ የሚመስላቸው አሉ። በምሳ ሰዓት አንድ ተማሪ ሶላት ልስገድ ሲል ልምን አትሰግድም ይባላል። ምን አገባው? ይህ እኮ ሰብዓዊ መብቴ ነው።" - አልዩ ሰዒድ (በፌደራል መጅሊስ የትምህርት ክፍል ዳይሬክተር)
ከበር አውልቀነው የምንገባው ሀይማኖት የለንም። ሴኩላሪዝም የትምህርት ስርዓቱን ከሐይማኖት ተፅዕኖ ነፃ ያወጣል እንጅ፤ በሴኩላሪዝም ስም እኛ ከሀይማኖት ነፃ እንድንሆን አንገደድም።
ለሁላችንም የሚሆን ቻለንጅ፦
መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZSXwfPJ2n/ በመግባት ኮ…
❤13
25 Jul 2026, 06:31 UTC≈1,370 views15 reactionsread 8 August 2026 Video
በፈረንሳይ ሀገር ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲገቡ ሒጃባቸውን ጥለው እንዲገቡ ይገደዳሉ። ልክ በአክሱም እንደተደረገው፤ በጉንችሬ እንደተደረገው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሊደረግ መመሪያ እንደወጣለት ማለት ነው። የሀይማኖት ነፃነት መብት የት ነው? የመማር ነፃነት የት ነው? ሰብዓዊ መብት የት ነው? ዛሬ ኒቃብን ካስወለቁ ነገ ፀጉር ግለጡ ማለታቸው አይቀርም። ሆኖም ግን ፈፅሞ አይሆንም!!!
ቻሌንጅ ለሁላችን፦
መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ በቲክቶክ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት እናድርግ። ሊንኩ https://vt.tiktok.com/ZSXcA1HkJ/ ነው።
ይህ በዚህ መንገድ ትንሹ ሀላፊነታችን ነው !
ወደ ተግባር !!
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስ…
❤8🔥7
24 Jul 2026, 12:55 UTC≈1,170 views9 reactionsread 8 August 2026 Video
"የሀይማኖት ጉዳዮች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አጀንዳ ይሆን ዘንድ ሕዝበ ሙስሊሙ ታግሏል። ሙስሊም ተማሪዎችም ዘርፈብዙ የሆነ ንቅናቄ አድርገዋል። ሀገራዊ ምክክሩ እንደተቋጨ የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄዎች ዘላቂ፣ ፍትሐዊ እና ተፈፃሚ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል።" - ሙሐመድአሚን ካሳው
ቻሌንጅ ለሁላችን፦
መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ በቲክቶክ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት እናድርግ። ሊንኩ https://vt.tiktok.com/ZSX7DFQ2R/ ነው።
ይህ በዚህ መንገድ ትንሹ ሀላፊነታችን ነው !
ወደ ተግባር !!
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !
https://t.me/EHEMSU
❤5🔥4
Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union pinned a photo
23 Jul 2026, 02:56 UTC≈1,160 views8 reactionsread 8 August 2026 Photo
በአምቦ ዩኒቨርስቲ የወሊሶ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድን በጋራ እንገንባ !!!
መስጂዱ በጥቂት ተማሪዎች እና በኸይር ሰሪዎች ርብርብ ከተጀመረ 13 አመታትን አስቆጥሯል። አሁን ላይ ግራውንዱ ወደ መጠናቀቅ ሄዶ ሁለተኛው floor ተጀምሯል። እንደዚሁም ሆኖ የታችኛውን ክፍል በመጋረጃ ከፍለው ነው የሚጠቀሙት። የጁምዓ ቀን እና ረመዳን ሲገባ ግን ከቦታ ጥበት አንፃር ለሁሉም ሰጋጅ አይብቃቃም። ይህ መስጂድ ተጠናቆ የታሰበለትን ዘርፈብዙ አገልግሎት ለሁሉም ይሰጥ ዘንድ ብዙ ሚልዬን ብሮች ያስፈልጋል። ይህ ይሆን ዘንድም ከቻልነው፤ በአቅማችን ልክ አስተዋፅዖ እንድናደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የአላህን ቤት ዱንያ ላይ የገነባ አላህ የአኼራ ቤቱን ይገነባለታል። የ…
❤5🥰3
17 Jul 2026, 09:05 UTC≈1,880 views17 reactionsread 8 August 2026 በሀገራዊ ምክክር ላይ የሕዝበ ሙስሊሙን አጀንዳዎች ይዘው ለቀረቡ ተወካዮች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የተላለፈ መልዕክት፦
ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት እና የሀገራችንን እጣፋንታ በውይይት ለማስመር የተጀመረው እና ለ30 ቀናት የሚቆየው ሀገራዊ ምክክር በታሪክ ስለሀገራዊ ችግሮቻችን ውይይት ለማድረግ የመጣ ታሪካዊ እድል፤ በአግባቡ ከተጠቀምንበት ደግሞ ጥያቄዎቻችን በውይይት ምላሽ የሚያገኙበት የድል መድረክ ነው። በተለይም ከ8ቱ የምክክር አጀንዳዎች 4ተኛ እና 5ተኛ የሆኑት የሀይማኖት ጉዳዮች፤ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነት እና ሰብዓዊ መብቶች አጀንዳዎች ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከትምህርት ቤቶች ጀምሮ በሴኩላሪዝም እና መሰል የዳቦ…
❤16🤣1
15 Jul 2026, 07:20 UTC≈2,780 views19 reactionsread 8 August 2026 Video
"ሕልሜ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቀላቀል ቢሆንም ኒቃብን የሚከለክልን መመሪያ ማውጣቱ እና በኒቃቢስቶች ላይ የሚደርሰው እንግልት ግን ሌላን እንዳስብ እያደረገኝ ነው። ስለሆነም የሚመለከታችሁ አካላት መብታችንን አስከብሩና ሕልማችንን እናሳካ።" - ከ Moonlight አካዳሚ እንደ አጠቃላይ አንደኛ ወጥታ የወርቅ ተሸላሚ የሆነችው ኒቃቢስቷ አስማ አህመድ
ዩኒቨርስቲው ያወጣው ጨቋኝ መመሪያ ተፅዕኖ በውስጡ ከሚማሩት ተማሪዎች አልፎ ሕልማቸውን በዩኒቨርስቲው ለመማር ለሚያደርጉት ጭምር ነው። "ኒቃብን ለብሶ መማር አይቻልም!" - የሚልን መመሪያ ሲያወጣ ኒቃባቸውን ለብሰው የሚማሩትን ሁሉ ወደ ዩኒቨርስቲው አትምጡ የሚል መከልከያ እያስቀመጠ ነው። ለዚህም ነው ጥ…
😭14❤5
2 Jul 2026, 19:34 UTC≈2,400 views14 reactionsread 8 August 2026 Photo
በመመረቂያ ቀኗ ሽልማቷን የተነፈገችው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሁዳ በቀለ ዝርዝር ጉዳይ ምንድን ነው? ከተማሪዋ አንደበት ያዳምጡ። የዩኒቨርስቲው ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አቋምስ ምንድን ነው? የጀመዓው ምክትል አሚር ማብራሪያ ሰጥቷል። የሚጠበቀው መፍትሔስ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው ዳስሷል።
ሙሉውን https://youtu.be/MO2v5Kn7_Uo?si=VHIlLQLiVbYuynz5 በሙባረክ ፖድካስት ያዳምጡ። ለሌሎችም share ያድርጉ።
@EHEMSU
👍5🔥5❤3👏1
2 Jul 2026, 11:00 UTC≈2,190 views30 reactionsread 8 August 2026 Photo
የአምቦ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ 3.93 በማምጣት ሰቃይ ሆና ሳለ በሽልማት መድረክ ላይ ሽልማቷን ለተነፈገችው ተማሪ ሁዳ በቀለ እውቅና ሰጠ!!!
ተማሪ ሁዳ (መቅደስ) በቀለ በ2018 ዓ.ል ከአምቦ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ተሸላሚ የነበረች ቢሆንም ዩኒቨርስቲው በተማሪዎች ምረቃ እለት እውቅናም ሽልማትም ሳይሰጣት አልፏል። ይህ መሆኑ በተማሪዋ ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና ከመፍጠር ባሻገር የተፈጠረው ክፍተት በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ ፈጥሯል። ይህንንም ተከትሎ ዩኒቨርስቲው ለአንድ ሚዲያ በሰጠው ቃል የተፈጠረው የቴክኒክ ችግር መሆኑን ተከትሎ ቢሮ ጠርቶ ይቅርታ እንደጠየቃት አሳውቋል።
ሆኖም ግን ማህበረሰቡ የጠየቀው ጥ…
👍22❤5🎉3
1 Jul 2026, 13:58 UTC≈2,490 views44 reactionsread 8 August 2026 Video
ዛሬም ኒቃባቸውን በአደባባይ አውልቀው እንዲገቡ ተገደዋል!
በትላንትናው እለት የ12ተኛ ክፍል ኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በአብርሆት ቤተመፅሐፍት እየተፈተኑ ባለበት ከ20 በላይ ሙስሊም ተማሪዎችን "ኒቃባችሁን ካላወለቃችሁ አትገቡም!" - ተብለው ጓደኞቻቸው ውስጥ እየተፈተኑ እና በትምህርት ሚኒስቴሩ ሚንስትር ብርሃኑ ነጋ እየተጎበኙ ለ3 ሰዓታት ያክል ከውጪ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር። የሗላ ሗላ እንዲገቡ ቢደረግም ኒቃባቸውን አውልቀው እና ጥለው በማስክ ነበር። መፍትሔ እንደሚመጣ የተገለፀ ቢሆንም በዛሬው እለትም በተመሳሳይ ኒቃባቸውን በአደባባይ እያወለቁ እንዲገቡ ነው የተደረጉት።
ይህ ግልፅ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው። ይህ ግልፅ የሆነ የሀይማኖ…
🤬25😢17❤1👍1
1 Jul 2026, 12:00 UTC≈2,340 views35 reactionsread 8 August 2026 Photo
አምቦ ዩኒቨርስቲ ምላሽ ሰጥቷል። ዩኒቨርስቲው 3.93 በማምጣት ከሁሉም ተማሪ ቀዳሚ ብትሆንም በመመረቂያ አዳራሽ ሽልማቷን ስለተነፈገችው እህታችን ሁዳ (መቅደስ) በቀለ ለABDII SABAA ሚዲያ ምላሽ ሰጥቷል። ሚዲያው እንደገለፀው በስልክ ላቀረበላቸው ጥያቄ "የተፈጠረው ችግር ሀይማኖትን መሰረት አድርጎ አይደለም። የሲስተም ችግር ነው። ይህንንም ተከትሎ ተማሪዋን እና ቤተሰቧን ጠርተን ይቅርታ ጠይቀናታል። ሜዳልያም እንዲሰጣት ሆኗል። መሰል ስህተቶች እንዳይደጋገሙም አበክረን እንሰራለን።" - ብሏል።
አሁንም ቢሆን ዩኒቨርስቲው ጥያቄያችንን አልመለሰም። ጥያቄዎቻችን የሚከተሉት ናቸው።
፨ በአደባባይ የተነፈገችውን ክብር እና ሽልማት በአዳባባይ ይቅርታ በመጠ…
👍32❤3
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @EHEMSU. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.