23 Jul 2026, 14:35 UTC444 views14 reactionsread 7 August 2026 Photo
ለቅዳሜ ምሽት ቀጠሮ እንያዝ... በርዕዮት ኪን ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
አራት መጽሐፍትን በኢንተርኔት እንመርቃለንተ
ህይወት ተፈራ ፥ ይፍቱስራ ምትኩ ፥ አድህኖም ምትኩ እና እኔ አለን።
ደጋሹ Tewodros Tsegaye ነው።
ቴዲና የርዕዮት ቡድን ስለ ሚያዘጋጀው ድግስ ማብራሪያ ያስፈልግ ይሆን? ጥሩ ድግስ እንደሚሆን ሁላችንም እናውቃለን።
ቅዳሜ ሐምሌ 18 ከምሽቱ 12 ፡30 ጀምሮ እንገናኛለን!
❤10👍2🔥2
22 Jul 2026, 15:56 UTC476 views25 reactionsread 7 August 2026 ቀጣይ አመት ምግብ ይኖረን ይሆን? አይርበንም ይሆን? እንጃ ብቻ
ዛሬ ጠዋት ከቤት ስወጣ ወደ ሰማይ አንጋጠጥኩ። ይህ ሰሞንኛ ልማዴ ነው። በየጠዋቱ ሰማዩን አየዋለሁ። "ዛሬ ይዘንብ ይሆን?" እላለሁ።
ድንገት የገበሬ አመል አመጣሁ። መዝነብ አለመዝነቡ የሚያስጨንቀው ሰው ሆንኩ።
ልጅ እያለሁ ፥ ቤተሰቦቼ ከዘመድ አዝማድ የሚያደርጉት ውይይት ላይ የማይረሳ ጥያቄ ነበር። "እናንተጋ ይዘንባል?" ይባባላሉ። "እናንተጋ ይዘንባል ወይ?" የሚለው ጥያቄ አይቀሬ ጥያቄ ነው።
ከልጅነት ከፍ ባልኩበት እድሜ የጥያቄው ዋጋ አይገባኝም ነበር። ሰዎች ወሬ ለማስቀጠል ብቻ የሚወራወሩት ጥያቄ ይመስለኝ ነበር።
"ይዘንባል ወይ?" የሚለው ጥያቄ ግዙፍ ነው። ጥያቄው ስለዘንድሮ ቢ…
👍11😢9🥰3❤2
20 Jul 2026, 14:12 UTC533 views14 reactionsread 7 August 2026 ትውልድ አይደናገር ፥ እኛም እንናገር
እግር ኳስ ቅሪላ ማልፋት ብቻ አይደለም። የጠገበ ፈረንጅ እርግጫም አይደለም። እግር ኳስ የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። የግለሰቦች ተሰጥኦ ፥ የቡድን ስራ ፥ የአመራር ጥበብ ፥ ስነልቦናዊ ጥንካሬ ፥ የአእምሮ ፍጥነት ፥ የአካል ብቃት ፥ አልሸነፍ ባይነት... ወዘተ ተጣምሮ እግር ኳስን ይፈጥራሉ። ከላይ ከተጠቀሱት ያለ አንዱ ዘመናዊ እግር ኳስ የለም።
እግርኳስ እንደ ቡድን ከፍታው ላይ ሲደርስ የጋርዲዮላን ባርሴሎና ይመስላል። እንደ ግሰለሰብ የእግር ኳስ ከፍታ ልዮ ሜሲ ነው።
ሊዮኔል ሜሲ ፥ የማይገረሰስ ንጉሥ!
ለመጀመሪያ ጊዜ ሜሲን ያየሁት የዛሬ 21 አመት ነበር። እንደሁልጊዜው ከአባቴጋ ኳስ ልናይ ሄደን…
❤6👍5👏2🥰1
20 Jul 2026, 14:11 UTC404 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤3😁1
20 Jul 2026, 13:53 UTC434 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
ዛሬ አትሮኖስ ነበርን። ስለ መጽሐፌ "ዙፋን ልፊያ" አወራን። ጥሩ ውይይት ነበረን። በበጎ አስተያየቶች ልቤ ሞቋል፥ እንዲታረም በተነገሩኝ ነጥቦች ተምሬበታለሁ። እንኳን ተወያየን
ፎቶ ፥ ዶክተር ፍርድአወቀ ማሞ (የቀይ ባርህ ሲቀላ መጽሐፍ ደራሲ) ፣ አርቲስት ዘላለም ምፅላል (ሱዳን ምንልታዘዝ ድራማ ላይ)፣ ሊዲያ ተስፋዬ (ደራሲ) ፣ ተስፋዬ አድሃኖም (Phd የነገረመለኮት እና የቋንቋ መምህር) እና ተስፋአብ ተሾመ
❤5👍1
18 Jul 2026, 17:09 UTC563 views6 reactionsread 7 August 2026 Video
Video, posted without a caption
👍6
15 Jul 2026, 21:47 UTC795 views18 reactionsread 7 August 2026 Photo
🤔
😁18
15 Jul 2026, 21:12 UTC760 views12 reactionsread 7 August 2026 "የሜሲ ቡድን ተሸነፈ" ብለው ተስፋ ካደረጉ በኋላ አርጀንቲና ማሸነፏ ያረካል።
ተስፋቸው ገደል ሲገባ ደስ ይላል።
መጀመሪያ የፖርቱጋል ደጋፊ ነበሩ፥ ቀጥለው ፈረንሳይ ፥ ቀጥለው እንግሊዝ...
ሜሲን ሊያስቆም ይችላል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ደግፈዋል። የሜሲ እግሮች ተስፋቸውን ደጋግሞ ቀምቷል።
እየመሩ ተስፋ አድርገው ሲሸነፉ ደስ ይለኛል
(በነገራችን ላይ ሜሲ የምንፈልገውን ሁሉ ሰጥቶን ጨርሷል። በዚህ አለም ዋንጫ ሜሲን በመጥላት የነሆለሉ በስኬቱ ሲበሽቁ ማየቱ ነው የሚያስደስተኝ
❤5👎3🔥3👏1
15 Jul 2026, 17:44 UTC680 views26 reactionsread 7 August 2026 አርጀንቲና በኢ-ፍትሐዊ መንገድ ብታሸንፍ ደስ ይለኛል።
ኦፍ ሳይድ ጎል አግብተው ቢፀድቅ ፥ የማያሰጥ ፔናሊቲ ተሰጥቷቸው ቢያገቡ ፥ እንግሊዝ ንፁህ ጎል ቢሻርባት ደስ ይለኛል።
ለምን?
ሜሲን የሚጠሉ ሰዎች በደንብ መናደድ አለባቸው። ጨጓራቸው ሲላጥ ማየት እፈልጋለሁ!
👎14❤7👏4🤔1
15 Jul 2026, 15:00 UTC676 views11 reactionsread 7 August 2026 ጡቴ መውረድ የጀመረ ይመስለኛል። መቀመጫዬ እንደ ድሮው እንዳልሆነ ይታወቀኛል። ጉንጮቼ ማዲያት ማውጣት ጀምረዋል። ከናፍሮቼን ሲጃራ አጥቁሯቸዋል። እያረጀው ይሆን?
የከፋ ቀን ይመጣል። በተፈጥሮዬ ውብ የነበርኩበት ቀን አልፎ በሜካፕ ጉልበት እንኳን ማማር የማልችልበት ቀን ይመጣል። . . . አረጃለሁ።
መክሰም አልፈልግም። በፍጹም መክሰም አልፈልግም። ተወልጄ ሳልጨርስ መሞት አልፈልግም። ኑሮዬን ሳላጣጥም ዘመኔ እንዲያከትም አልሻም።
በህይወቴ ዛሬ የሚባል ቀን ኖሮኝ አያውቅም።
የሆነ ወቅት ላይ ስለ ነገ ሳስብ ዛሬዬ አመለጠኝ።
ትላንት ያለ ልክ በተስፋ እና ህልም ውስጥ ገብቼ የአሁን ሃያልነት ተረሳኝ። ነገ ያልኩት ቀን ሲደርስ ደግሞ ተስፋ ካደረግናቸው ህል…
❤7👍2😢2
11 Jul 2026, 16:06 UTC757 views10 reactionsread 7 August 2026 "እናቴ ሦስቴ አግብታ ሦስቴ ፈታለች። ከእህቴ እና ከወንድሜ ጋር አባት እንደማንጋራ ታውቂያለሽ። እናቴ አዲስ ሕይወት በጀመረች ቁጥር በትዳሯ እንደምትፀና የምትወራረድ ቢሆንም፣ አዲሱ ሕይወት ብዙም ሳይቆይ መዝመም ይጀምርና የመጠገን እድልን ሳያገኝ ይፈርሳል።ይህ እንዴት ሆነ?››
‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››
‹‹ወንድሜ ለትዳር ምንም አይነት መጓጓት እንዳልነበረው ታውቂያለሽ... እማማና ዘመዶቿ ወትውተውት ካገባ በኋላ በሦስት ዓመቱ ተፋታ። ከትዳሩ መፍረስ በኋላ ለገዛ ልጁ እንኳን ግድ የለሽ ሆኖ የተገለለ ኑሮ እየገፋ እንደሆነ ታውቂያለሽ።... ይህ እርግማን አይደለም?››
‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››
‹‹እህቴ ቁጥብ እና በራስ መተማመን ያላት ሴት …
👍7❤3
9 Jul 2026, 14:43 UTC841 views17 reactionsread 7 August 2026 ጡቴና ዳሌዬን ወደ ገንዘብ ለመመንዘር ተሰለፍኩ። ውበቴን ሸጬ ገንዘብ ለመቀበል ወደ ገበያ ወጣሁ። በገበያ መካከል እርቃኔን ቆምኩ።
"ይሄን የመሰለ ውበት ኖሮሽ እንዴት ትቸገሪያለሽ?" አሉኝ። ቆንጆ ሴት ችጋር ሊያገኛት አይገባም ሲሉኝ አመንኳቸው። ውበት እና መከራ ደመኛ እንደሆኑ ሰበኩኝ፥ ስብከታቸው በዝግታ ወደ ልቤ ሰረገ።
መሰረታዊ ፍላጎቴ የተሟላ ነበር። መኪና ባይኖረኝም የታክሲ ተቸግሬ አላውቅም። ምግብ ባላማርጥም አልራብም። ቤት ባይኖረኝም የቤት ኪራይ መክፈል አይቸግረኝም። በባንክ የምቆጥበው ባይተርፈኝም እዳ ገብቼ አላውቅም። በፍስሃ ክንዶች ባልንተራስም ሃዘን አይደቁሰኝም።
ችጋር እንደሚደቁሰኝ የነገሩኝ ሌሎች ናቸው። ውበቴን ባዳነቁ አፍታ "አንቺን…
👏8👍3❤2🥰2🔥1😢1
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @Tfanos. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.