29 Jul 2026, 07:47 UTC14 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @ezreal_1
በአንድ ቅዳሜ ምሽት በካርኒቫል ውስጥ የሚጨፍሩትን በግማሽ እርቃናቸውን ያሉ ልጃገረዶችን በሴሰኝነት የሚመለከቱ ሰዎችን አያለሁ፣ በእሁድ ጠዋት ደግሞ በካርኒቫሉ ሌላኛው ጫፍ ለድንኳን ወንጌላውያን ኦርጋን ስጫወት፣ እነዚህኑ ሰዎች ከሚስቶቻቸው እና ከልጆቻቸው ጋር በቤተክርስቲያን ወንበሮች ላይ ተቀምጠው እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንዲላቸው እና ከስጋዊ ፍላጎት እንዲያነጻቸው ሲጠይቁ አያለሁ። እና በሚቀጥለው ቅዳሜ ምሽት ወደ ካርኒቫሉ ወይም ወደ ሌላ የሥጋዊ ደስታ ቦታ ይመለሳሉ።
በዚያን ጊዜ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን በግብዝነት ላይ እንደምታድግ፣ እና የሰው ልጅ ሥጋዊ ተፈጥሮም ማሸነፉ እንደማይቀር አወቅሁ!
@ezreal_1
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
20 Jul 2026, 07:34 UTC26 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ
ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡
ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ…
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
28 Jun 2026, 18:16 UTC46 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @Oct13wed
#ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ወደ ሂወትህ ሲመጡ እነዚህን ሶስት ነገሮች አስብ
1. እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደነበር
2. እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ
3. ነገም ሁሌም እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደሚኖር❤️
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
14 Jun 2026, 08:35 UTC64 viewsread 6 August 2026 https://t.me/tarekachin
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
13 Jun 2026, 20:25 UTC65 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
.....በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ስንብት የሚባል ነገር ትልቁ የነፍስ ፈተና ነው። አብዛኞቻችን ቻው ማለት ወይም መሰናበት እንደ ቀላል ጉዳይ ይታያል። ለአንዳንዶቻችን ግን ስንብት ቀላል የቃላት መለዋወጫ ሳይሆን በልብ ውስጥ የነበረን አንድ ውብ ገጽ በግድ የምንዘጋበት ያንኑ ቅርርብ በአንድ ቃል የምናቋርጥበት እጅግ ከባድ ስሜት ነው። ቻው ብለን....
ለሰዎች... መሰናበት ሲያቅተን እንደ መጥፎ ባህሪ ወይም እንደ ቸልተኝነት ሊቆጠር ይችላል። ነገር ግን ይህ ስሜት የሚመጣው ከመውደድ ነው። አንድን ሰው መሰናበት ማለት ያ ሰው በህይወታችን የነበረውን ድርሻ በአንድ ጊዜ የምንገታበት የጋራ ጊዜያችንን ወደ ትዝታነት የምንቀይርበት ሂደት ነው። መለያየትን ለመቀበል የ…
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
23 May 2026, 17:02 UTC57 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
ሙሉ ደቂቃ ቁጭ ብዬ ኳስ ያየሁበትን ቀን እምብዛም አላስታውስም። ነገር ግን በተለይ ሃይስኩል እያለሁ በአጋጣሚ ሳልፍ አልያም ደግሞ መሄጃ ከሌለኝ ሻይ እየጠጣሁ ሀይላይት አይ እንደነበር ግን በደምብ ትዝ ይለኛል። ልጅ እያለሁ በራሱ ታላላቆቼ ብስራት ኤፍ ኤም ከፍተው ሲሰሙ ግን እማልክደው የልጅነት ሀቅ ነው። መሰለ መንግስቱ ያወጣው ዘፈን ዛሬም ጆሮዬ ላይ አለ።
''እግርኳስን በሬድዮ ተመልከቱ።
መሰ...............ለ መንግስቱ!..'' የሚል ድምጽ....
በዚህ መሃል ግን አርሰናል ከሌሎች ክለቦች በተሻለ ለእኔ ጎልቶ እንዲታይ የሆነበትን ምክንያት ግን እነሆ....
ልጅ እያለሁ ከማልረሳቸው ኵነቶች አንዱ በታላላቅ ወንድሞቼ የሚደረገው የአርሰናል እና …
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
20 May 2026, 03:08 UTC42 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
ህእ!
+++++++
ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ትዳር ነው።
ባል ስቅታ ይዞታል። ከነጋ ለሶስተኛ ጊዜ እንደ አዲስ ሲጀምረው ክፉኛ ተበሳጨ።
“አረ ማናባቱ ነው ስሜን ሲያነሳና ሲጥል የዋለው? ህእ! ” አለ ለሚስቱ።
“ስኳር ቃምክበት?” አለችው።
“አዎ።”
“ደረቅ እንጀራ በላህበት?”
“ህእ! አዎ”
“ቀዝቃዛ ውሃ ጠጣህበት?”
“አዎ”
"በረዶ ያለው?"
"ህእ! አዎ አልኩሽ እኮ"
“እሺ ትንፋሽህን ይዘህ ሞከርከው? ”
“አዎ ”
“እና አሁንም አልቆመልህም?”
“ህእ! አልቆመልህም? እያየሽኝ አይደል? አሁንም እያነቀኝ? ህእ! "
ትኩር ብላ አየችው።
ከቅድሙ አሁን ንጭንጭ አብዝቷል።
“እንጃ እንግዲህ” አለች። “እስቲ የፈረደበትን ቻት-ጂፒቲን ሌላ መፍትሄ ጠይቀው?”…
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
13 May 2026, 05:31 UTC51 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
አኩኩሉ አልነጋም
አኩኩሉ አልነጋም
ዐይኑን ለጨፈነ በቶሎ አይነጋም
ገልጦ ሲቃኝ ብርሃን ናፍቆ
ሁሉም ጠፍቷል ተደብቆ
ሺ ቢለፋ ሊያገኛቸው
ማይገኙለት ብዙ ናቸው
.
ህይወትም እንዲያው ናት
ጨፍነው እስኪገልጡ ቆማ አትጠብቅም
ለብርቱ ነው እንጂ
አውቆ ለታወረ ቦታ ሰጥታ አታውቅም
አኩኩሉ አኩኩሉ ያ ጨዋታ ያ ልጅነት
ላስተዋለው መስታወት ነው
ብርቱ ከሰነፍ የሚለይበት
ህይወት ቆማ አትጠብቅም
ለበረታ ፀሃይ አጠልቅም
አይጋረድ ዐይናቹ
አንድ እናንተው ያላችውት ለራሳቹ!
.
አኩኩሉ አኩኩሉ
ሳይረፍድ ግለጡ
ቶሎ በሉ!🔥🤫
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
11 May 2026, 20:37 UTC62 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
አሻጋሪዎቹ!
የጎጆ ቤት ጨዋታ።
እንዲህ ባለ የግንቦት ወር ነበር ያረፉት:- የቡታጅራ መንገድ: መንገድ መሆን እንደሚችል ሳይታሰብ ገና ድሮ እርሳቸው በባዶ እግር ሄደው: ለገዳሙ ቤተሰብ ቀለብ እህል፣ በርበሬ ጭነው በአህያ እየነዱ ይወስዳሉ።
ከአዲስ አበባ ሰባት ቤት ጉራጌ ምሁር ኢየሱስ ድረስ በእግር እየተጓዙ ጉዳይ ያስፈጽሙ ነበር:- አባ ፈቃደሥላሴ (አባ ፈቃደ፣ በሀገሬው አጠራር "አቦች") ዘምሁር ኢየሱስ ገዳም።
ይህንን በማደሪያቸው የሳር ጎጆ እሳት አቀጣጥለው ሻሂ እያፈሉ ያጫውታሉ።
በዚያ እርጅና በጎጆዋ ውስጥ ካለው ቆጥ የተፈለጠ እንጨት አውርደው፣ እሳት አቀጣጥለው የሀገሩን ቅዝቃዜ ሲረቱ ማየት ግር ሊል ይችላል። ለእርሳቸው ድንቅ አይደለም…
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
23 Apr 2026, 07:18 UTC77 views2 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
አንችም በሐይማኖትሽ....
አንችም በሐይማኖትሽ እኔም በሐይማኖቴ....
የሚለው ግጥም ግን በእውነተኛው አለም ከቶ አይሰራም እቴ
እኔም ካንቺ ፍቅር አንቺም ከኔ መውደድ እየተላመድን
አንቺ ሌላ አምላክ እኔም ሌላ ጌታ ደግሞ ከወደድን...
እዚህጋር ተሸዋወድን...
እሺ ከዚያስ... ምን ሊሆን ፍጻሜው?
የትስ ቦታ ሊሆን ፍቅራችን መድረሻው?
ካልወሰድሽኝ በኒቃ ካላገባሁሽ በተክሊል
ለቅዳሴ አብረን ካልነቃን ሶላት ካልወጣን አዛን ሲል
ልጆችሽ ቁርአን ካልቀሩ ልጆቼ ካልሄዱ አብነት
የሼሁም የቄሱም ትምህርት አይሄድም መቼም በአንድነት።
ሰደቃ ካልሰራሽ፣ አስራቴ ካላጸደቀሽ የኔ
ለልጄ ክርስትና ቀን ከሌለሽ ከጎኔ...
በአንድ ጣራ እየኖርን ሁለት ጌታ ስናመሰግን
ፍቅራ…
❤2
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
7 Mar 2026, 18:00 UTC106 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @misteriouslife
አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች...
✍️እስራኤል ሰይፉ
እነዚህ ጠርሙሶች ግን ለምን አስር ሆኑ? ማንስ ነበር አስር እንዲሆኑ የወሰነው? አሁን ላይ ሲገባኝ ግን ይህን ሃሳብ ሲያመጣው በህይወቱ ብዙ ነገሮችን ሞክሮ አንዱም ያልተሳካለት ሰው ይመስለኛል።
መስበር አሁን ምኑ ያስደስታል?
ጭራሽ ደግሞ ዜሮ ይቀራል ብሎ መደሰት...
ምን ይሉታል አሁን?
መሰበሩ ሊያሳዝነን ሲገባ ጭራሽ በዞሮው መጨፈር?
ያው አባባሎች ከህይወታችን ከተማርናቸው ትምህርቶች መካከል ዋናውን ጨምቀን አይደል የምናወጣው?
... ሲመስለኝ እንደዛ የተቀዳ ነገር ነው ይሄም። ከባዶ ሰው የተቀዳ አይነት ነገር...
ገብረ እግዚአብሔር እባላለሁ። በሙሉ ስሜ ግን ማንም ጠርቶኝ አያውቅም።…
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
18 Nov 2025, 17:14 UTC155 viewsread 6 August 2026 https://t.me/ezreal_1
Signed የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @our_thoughtes. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.