6 Aug 2026, 18:37 UTC82 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
'44'
አንድ ሰሞን ያፈቅሮት የነበረ ሰው፣ ዛሬ ዛሬ ስምዖት ሲጠራበት ይዘገንነው ይሆናል። ለመወደድ ጊዜ እንዳገኘው ሁሉ ለመጥላትም ጊዜ ያገኛል። እርሶም ከወደዶው ወደ አልወደደዎ፣ ከጠላዎት ወደ አልጠላዎት ይገለበጣሉ። ጊዜ ኃያል ነው። የሰዎችን ስሜትና ማንነት ይለውጣል። በነበሩበት አይቀሩም። የማይገነዘቡት ለውጥ አካል ነው። ቢገደሩም ፈቀቅ ይላሉ። የሰውን እጅ ባያዩም የጊዜን ጠምዛዥ እጆች አንጋጠው ያያሉ። ስፍራ ያስለቅቆታል። ግራ ዘመሞች ቀኝ ይዘምማሉ፣ ቀኝ ዘመሞች ግራ ይዘምማሉ። ጊዜ መስታወት ነው። ሁሉንም ያሳይዎታል። መሐል ሰፋሪዎችም የእግዜርም የሰይጣንም ናቸው።
ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬ ላንቺ
❤4
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
28 Jul 2026, 17:33 UTC490 views6 reactionsread 6 August 2026 አዋላጅና አዋቂ ሰው ያየውን ሁሉ አይናገርም።
ያወቁትን ሁሉ መናገር እውቀት አይደለም የእውቀት ማነስ ምልክት ቢሆን እንጂ. . . አንዳድ እውቀቶች ለአንተ አዲስ ሲሆን ለምትነግረው ሰው ያረጀ ሊሆን ይችላል።
አእምሮህ የመዘገበውን ሁሉ አፍህ አይናገር አንዳዱን እራስህ ጋር አብስለህ ለራስህ ተጠቀምበት።
❤6
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
26 Jul 2026, 17:15 UTC141 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤4
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
23 Jul 2026, 18:40 UTC592 views5 reactionsread 6 August 2026 «አንዳንዴ ሌላ ህይወት አልማለሁ። ለሰዎች ማን መሆኔን የማላስረዳበት። ከእንግዲህ ምንም አለመጻፍ፤ በተሰበረ መስታወት እራሴን ማየት አልፈልግም። ሙሉ ለሙሉ ብቻዬን የምሆንበትን ቦታ አልማለሁ። ማለቂያ የሌለው ምድረበዳ ላይ እንደተዘረጋ ባህር እኔ እና ድመቴ በዝምታ ተቀምጠን አልማለሁ። ህልም ግን ህልም ነው። በአዕምሮአችን በኩል ያለከልካይ ከፍተን የምንዘጋው በር ነው። አብዛኛው ሰው ከህልሙ ይሸሻል። እውን እንዳይሆን በፍርሃት የታጠረ የሃሳብ ምስል ብቻ ሆኖ ይቀራል። እኔ ግን አየዋለሁ፣ እኖረዋለሁ፣ የኖርኩትን ጽፌ ቀስ አድርጌ እለቀዋለሁ. . .»
:~ቻርለስ ቡኮውስኪ
❤5
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
16 Jul 2026, 21:50 UTC792 views5 reactionsread 6 August 2026 ትዝታ🤌🏾
ማንን በምን እናስታውሳለን?. . . የእንቅስቃሴዎች፣ የጠረኖች የቀለሞች፣ የድምፆች፣ የግዑዛን ቅርጾች ውልብታ ጣፋጭ ወይም መራራ ትዝታን ይቀሰቅስብናል. . . ትዝታ ከየት እንደሚነሣ በውል እንደማናውቀው ነፋስ ነው. . . ሲደርስብን እንደ ስጥ እንበተናለን፣ እንተራመሳለን፣ እንረበሻለን። ለትዝታዎቻችን ያለን ስሜት እንደምናስታውሰው ነገር ይወሰናል. . . ምናልባት እንፈግጋለን፣ እንኳሻለን፣ እንተክዛለን፣ እንናፍቃለን፣ እናለቅሳለን፣ እንቆጣለን፣ እንመረራለን።
፣
፣
ያማረ ትላንት ለሌለው ሰው ትዝታ ምንድን ነው. . .? የሚያጥወለውል፣ እንቅልፍ የሚያሳጣ፣ ልብን የሚያከብድ፣ ሀዘን ላይ የሚጥል በሽታ አይደለምን. . .???
…
❤5
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
15 Jul 2026, 12:41 UTC193 views7 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @Noahtoaels_Idea
ማንም አልቀደመህም እሺ ማንም!
ወደዋላ አልቀረህም ገና ነህ ያንን ባዶ ቤት ውስጥ አንተ እና አምላክህ ብቻ ያሰባችሁትን ህልምህን ትደርስበታለህ እሺ
❤5👍1🔥1
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
14 Jul 2026, 17:00 UTC829 views5 reactionsread 6 August 2026 💭
.
.
ግራ ገባኝ፣. . . እኔ ነኝ የጠፋውት ወይስ...
መንገዱ ነው የጠፋብኝ???
❤4🔥1
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
12 Jul 2026, 11:08 UTC216 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @Noahtoaels_Idea
ልብ ብላችሁ አስተውላችሁ ከሆነ ትርጉም ያለው ህይወት መኖር ስትጀምሩ፣ ነገሮች ሲስተካከልላችሁ፣ ወደ ስኬት ስትጓዙ አስቁሞ የሚያደንቃችሁ ብዙ ሰው የለም
ልክ መንሸራተት ስትጀምሩ፣ ነገሮች ሲበላሹባችሁ፣ መንገዳገድ ላይ ስትሆኑ .... ሁሉም አተኩሮ የሚያየው እናንተን ነው
ለአመታት ደክማችሁ የገነባችሁትን ሬስቶራንት ወይም ካፌ ወይም ቡቲክ .... አንድም ቀን ዝር ሳይል ከርሞ በሆነ ምክንያት የተዘጋ ጊዜ ይደውልላችኋል .....
"ውይ ንግድ ቤትህ መዘጋቱን ሰማሁ .... ምን ገጠመህ ባክህ?" እያለ ቁስላችሁን በእንጨት ያከዋል
ከአመታት ፅናትህ እና ትግልህ በላይ ውድቀትህ ጉዳዩ ይሆናል
እድገት ጊዜ ይፈልጋል
እድገት ቀስ በቀስ በማማጥ የሚሆን ነገር …
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
10 Jul 2026, 14:50 UTC254 views3 reactionsread 6 August 2026 📌ማህተም 🖋️
📌ደረሰኝ 📄
📌የሆስፒታል ካርዶች 🏥
📌ሰርተፊኬት 📜
📌ቲሸርት, ኮፍያ & Mug 👕☕
📌Logo Design 🎨
📌የጥሪ ካርዶች 📇
📌ባነር 🚩
📌ስቲከር 🏷️
📌print, copy & scan 🖨️
📌እና የተለያዩ የሕትመት አገልግሎቶችን ከእኛ ጋር ያግኙ✌️
ለበለጠ መረጃ👉 @redu_2414
t.me/redu_advert
❤3
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
8 Jul 2026, 11:12 UTC214 views8 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @Noahtoaels_IdeaPhoto
መቼም! መቼም! ቢሆን እንድትጸልዩ የሚገፋችሁን ስሜት ችላ እንዳትሉት።😇
❤8
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
3 Jul 2026, 17:43 UTC204 views7 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @Noahtoaels_Idea
እማሆይ ነጫጭ ልብሳቸውን ከቢጫ ቆባቸው ጋር አድርገው ሰርክ እየዋሉ የሚያድሩበት ደብር ማታውን የመገበርያ ስንዴ ሲለቅሙ አምሽተው ስለነበር ጠዋት በመቅደሱ እንቅልፍ ቢጤ ተጫጫናቸውና ጥግ ላይ መቋሚያቸውን ደገፍ ብለው እንቅልፍ ሸለብ አደረጋቸው በመሀል ታድያ ያ የተለመደው ቅዠታቸው አባኗቸው ሲነቁ ካህኑ "በፍርሀተ እግዚአብሔር ወበሀይማኖት ወበፍቅር ቅረቡ" እያሉ ነበርና ደንገጥ ብለው ወደፊት ቀረብ አሉ ጥር በመሆኑ የሙሽራ መአት ተሰብስበዋል ልባቸው ደንገጥ ደንገጥ ሲልባቸው ቀና ብለው አንዱን ሙሽራ ተመለከቱት የቀድሞ ወዳጃቸው ነው ከሁለት አመት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ሲገናኙ እንዲህ ነበር የሆነው "አተወኝም አደል" በችኮላና የወንድነት ስሜት በሚፈታተነው ድምፅ…
❤4😢3
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
28 Jun 2026, 16:18 UTC239 views6 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @Noahtoaels_Idea
¹³እስቲ የእግዚአብሔርን አሠራር አስተውል፤ እግዚአብሔር ያላቃናውን ማን ሊያቃናው ይችላል? ¹⁴ጊዜው መልካም ሲሆን ደስ ይበልህ፤ ጊዜውም ክፉ ሲሆን አስተውል
፤ ይህንንም ያንንም ያደረገ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ሰው የወደፊቱን ማንኛውንም ሁናቴውን ሊያውቅ አይችልም።😇
ጽሐፈ መክብብ፦7፥13-14
❤5🥰1
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @whispers_of_thought. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.