6 Aug 2026, 18:37 UTC132 views4 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @whispers_of_thoughtPhoto
'44'
አንድ ሰሞን ያፈቅሮት የነበረ ሰው፣ ዛሬ ዛሬ ስምዖት ሲጠራበት ይዘገንነው ይሆናል። ለመወደድ ጊዜ እንዳገኘው ሁሉ ለመጥላትም ጊዜ ያገኛል። እርሶም ከወደዶው ወደ አልወደደዎ፣ ከጠላዎት ወደ አልጠላዎት ይገለበጣሉ። ጊዜ ኃያል ነው። የሰዎችን ስሜትና ማንነት ይለውጣል። በነበሩበት አይቀሩም። የማይገነዘቡት ለውጥ አካል ነው። ቢገደሩም ፈቀቅ ይላሉ። የሰውን እጅ ባያዩም የጊዜን ጠምዛዥ እጆች አንጋጠው ያያሉ። ስፍራ ያስለቅቆታል። ግራ ዘመሞች ቀኝ ይዘምማሉ፣ ቀኝ ዘመሞች ግራ ይዘምማሉ። ጊዜ መስታወት ነው። ሁሉንም ያሳይዎታል። መሐል ሰፋሪዎችም የእግዜርም የሰይጣንም ናቸው።
ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬ ላንቺ
❤4
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
5 Aug 2026, 15:06 UTC201 views3 reactionsread 7 August 2026 ሄራን -5-
•••በሚቀጥለው ቀን ቀደም ብየ ጠበቅኳት።ሳትመጣ ቀረች።ቀጠሮ አክባሪ አለመሆኗን ሰበብ አድርጌ ተበሳጨሁ።ሶስተኛ ቀንም እዛው ተገኘሁ።ብቅ አላለችም።አራተኛ ቀን-አምስተኛ ቀን-ተመላልሼ ላገኛት ሞከርኩ።የለችም•••
•••ስድስት ቁጥርን ስለማልወዳት በስድስተኛው ቀን ብወጣም እንደማላገኛት ገምቼ ቤቴ ተኛሁ።ይቺ ጣፋጭ እብድ የሆነ ነገሯን እኔ ውስጥ አስቀምጣዋለች።አሁንም አሁንም ትዝ እያለችኝ መተኛት ሲያቅተኝ ደፍሬ ለስድስተኛ ቀን ልፈልጋት ወጣሁ።መኪናዬን ላስነሳት ብሞክርም እንቢ ስላለችኝ ታክሲ ይዤ እዛው ቦታ ተገኘሁ•••
•••ከተወሰነ ጥበቃ በኋላ ፒጃማዋን የውስጥ ሱሪዋ ውስጥ ወትፋ በውስጥእንደ እብድ ስትሮጥ አገኘኋት።ስሟን አላቀውም።ቤቷን …
❤3
Signed ቀዳማዊ ዮሓቶኤል
5 Aug 2026, 05:31 UTC195 viewsread 7 August 2026 መፅሃፍ ማንበብ ይወዳሉ?
እንግዲያውስ ትክክለኛው ቦታ ላይ ነዎት!
ህይወትን የሚቀይሩ አስተማሪ ታሪኮች እና የማይረሱ ገፀ-ባህሪያት ይጠብቁዎታል።
አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Fiction_123
Signed baby ye tsega lej
4 Aug 2026, 17:08 UTC208 views5 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @tenqesha43
Reposting‼️
A struggle is a struggle
.
ሽንኩርት ሲከትፍ ቢላዋ የቆረጠዉ እና እንጨት ሲፈልጥ እጁ የተቆረጠ ሰዉ ሁለቱም “ምን ሆነህ ነዉ?” ቢባሉ “እጄ ተቆርጦ ነዉ” ይላሉ፥
.
ባለ ሽንኩርቱም፡ ባለ መጥረቢያዉም ይደማሉ፣ ይቆስላሉ፡ ቁስላቸዉን ያስታምማሉ፥
A struggle is a struggle
©️
❤5
Signed Su🤍
1 Aug 2026, 11:11 UTC412 views7 reactionsread 7 August 2026 ሄራን -4-
"ሙሉ ሴት ስሆን ሚስጥራቶች ሁሉ ሲገለጡልኝ የአባቴ ቅጥ ያጣ ሴሰኝነት የእናቴ የእባብ መንገድ ፍንትው ብሎ ሲታየኝ አብሬያቸው ለመኖር እስከሚያንገሸግሸኝ ድረስ ጠላኋቸው።ከነሱ መፈጠሬን ረገምኩት።መሄጃ ቢኖረኝ አይናቸውን ለማየት አልፈልግም ነበር"
•••እንድትቀጥል በአይኔ ተለማመጥኳት•••
"በህይወት በጣም ቀፋፊው ነገር ሰውን መጥላት ነው።በተለይ ቤተሰብህን ስትጠላ ህይወት ከባድ ትሆንብሃለች።ድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ ስገባ አባቴ በድንገት ታመመና በደቂቃዎች ውስጥ ቅጣቱን ወደሚያገኝበት ቦታ ሄደ።እናቴ ፊቷን እየነጨች ለያዥ ለገናዥ አስቸግራ በሀዘን የተጠበሰች ልታስመስል ስትጋጋጥ ሳያት ታዘብኳት።ከዚያ በኋላ ነው የአለም ፍፃሜ የሆነብኝ"
"ምን ተፈጠረ…
❤7
Signed ቀዳማዊ ዮሓቶኤል
30 Jul 2026, 15:59 UTC321 views4 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @tenqesha43
ትንሽ ብቻ እኮ ነው የቀረኝ
.
.
ስለዚህ ጠብቁኝ አንድ ሁለት አመት…ቢበዛ አስር አመት
አትኑሩ ጥላቹኝ ጠብቁኝ…ትንሽ ብቻ ጠብቁኝ….
❤3🤔1
Signed Su🤍
30 Jul 2026, 11:30 UTC412 views6 reactionsread 7 August 2026 2
ወደ ባሩ ገብቼ እሱ የሚቀመጥበትን ወንበር ስመለከት ብቻውን አደለም አንዲት ሴት ከፊትለፊቱ ተቀምጣለች ጀርባውን ሰቶኝ ስለተቀመጠ የሚታየኝ የእሷ መልክ ነው ቆንጆ ናት የፊቷ ቅላት ከጥቁር እረጅም ፀጉሯ ጋር ሲታይ ያስደነግጣል ከቀሚሷ ጥብቅ ማለት የተነሳ ጡቶቿ ውጥር ብለው በከፊል ይታያሉ ከታች ሆዷ አካባቢ ትንሽ ክብ ቦርጭ አለቻት መቀመጫዋ ሰፋ ይላል እግሯን አጣምራ መቀመጧ ከቀሚሷ እጥረት ጋር ተዳምሮ ቧቷን አጋልጦታል "ይቺማ እንኳን ወንድ ሴትም ታሻፍዳለች ሴትም እ" በራሴ ወሬ ደንግጬ አማተብኩ ትንሽ እንዳወሩ እራሱን ይዞ ቆመ ልጂቷ ደንግጣ ቦርሳዋን እንኳን ሳትይዝ ጥላው ሄደች ወድያው ራሱን ሳተ ተረባርበን ወደ ሆስፒታል ወሰድነውና ያገዙኝ ሰዎች እ…
❤6
Signed ቤተ ልሔም
30 Jul 2026, 05:09 UTC370 views2 reactionsread 7 August 2026 ሄራን -3-
"ወደ ጥልቁ መጥለቅ የሚል መፅሀፍ ጽፌ ነበር።ምን ዋጋ አለው ነገር አለሙ ሁላ ሲደበላለቅብኝ ሳይታተም፣ሳይነበብ እንዲሁ ኮፒውን የጡት ማስያዣየ ውስጥ ይዤው ስንከራተት በስብሶ ቀረ"
•••በጣም ርቧት ነበር መሰለኝ እየተስገበገበች ነው የምትመገበው።በእያንዳንዷ ጉርሻዋ መሀል አይኖቿ ይረጥባሉ።ከራሷ ጋር ትታገላለች።የሆነ ድቅን እያለ የሚያባባት ትውስታ ውስጥ ገብታለች።ስሜቷን በሳቋ ለመደበቅ አሁንም አሁንም ፈገግ ለማለት ትሞክራለች•••
"ምነው አትበላም እንዴ?"
"እየበላሁ ነው"
"አይንህ ግን የተሰካው እዚህ ጋር ነው" ጡቶቿን በአይበሉባዋ ደግፋ"ከዚ ጋር ንቀላ"
"ወደ ጥልቁ መጥለቅ ያልሽው ፅሁፍሽን?ይዘሽዋል?"
"የለም!"ልብሷን ዝቅ አድርጋ ደ…
❤2
Signed ቀዳማዊ ዮሓቶኤል
29 Jul 2026, 17:52 UTC339 views8 reactionsread 7 August 2026 ምንም ቢሆን የሰውን ሓቅ፣ የሰውን እውነት፣ የሰውን እንባ ለራሳችሁ አታትርፉ።
❤8
Signed ቀዳማዊ ዮሓቶኤል
29 Jul 2026, 10:22 UTC393 views6 reactionsread 7 August 2026 1
እስከዛሬ እከሌ ውብ ነው እከሊትን በደንብ ነው የማውቃት ቆይ እሱን ላፍቅረው እሷን ላፍቅራት እያለ አማርጦ ያፈቀረ አላየንም መርጦ ማፍቀርም የለም በህልሜም በእውንም አስቤው የማላቀው አይነት ሰው ነው ምናልባት ደንዳና ሰውነቱ እና በአይኖቹ መካከል ያሉት ሶስት መስመሮች ስበውኝ ይሆን? ጠጪ ነው ለዛ ያለው ሰካራም ሴት አይቀርብም አያናግርም ምሽት ላይ መጠጥ ቤት ሄዶ ከቀማመሰ በኋላ በአይኑ ረጋ ያለች ናት ብሎ ያሰባትን ይጠራታል ላናግረው ሞክሬ መልሱ ግን "የደረቀውን ቁስሌን ልጠሽ ልታደሚ ነው!!" ነበር ከዛ ግን ስለሱ ሳጠያይቅ ሳይጠጣ ሴት እንደማያናግር ነገሩኝ ምን ይሁን ማን ይሁን ሳላውቅ ልቤ ደነገጠለት በሚል ሲመሽልኝ ጠብቄ ከድሮ ቀ…
❤6
Signed ቤተ ልሔም
28 Jul 2026, 17:34 UTC399 views6 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @whispers_of_thought
አዋላጅና አዋቂ ሰው ያየውን ሁሉ አይናገርም።
ያወቁትን ሁሉ መናገር እውቀት አይደለም የእውቀት ማነስ ምልክት ቢሆን እንጂ. . . አንዳድ እውቀቶች ለአንተ አዲስ ሲሆን ለምትነግረው ሰው ያረጀ ሊሆን ይችላል።
አእምሮህ የመዘገበውን ሁሉ አፍህ አይናገር አንዳዱን እራስህ ጋር አብስለህ ለራስህ ተጠቀምበት።
❤6
Signed ዘ ተ ሐ ር ዩ
28 Jul 2026, 16:04 UTC445 viewsread 7 August 2026 Posted without readable text
Signed ︎ ︎ ︎ ︎ ︎
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Noahtoaels_Idea. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.