29 Aug 2026, 14:59 UTC≈3,440 views16 reactionsread 3 September 2026 Photo
የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶስት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዛምቢያ የሚያደርጉት ጉብኝት፤ አሜሪካ ከየሀገራቱ ጋር ያላትን “ቁልፍ” የሁለትዮሽ ግንኙነቶች የማጠናከር እንዲሁም የጸጥታ እና የኢኮኖሚ አጋርነቶችን የማሳደግ ዓላማ ያለው ነው ተብሏል።
ጋርሺያ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ረዳት ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በነገው ዕለት ሶስተኛ ወር ይሞላቸዋል።
በአሜሪካ ባህር ኃይል ለ28 ዓመታት ያገለገሉት ጋርሺያ፤ ለአንድ ዓመት ክፍት ሆኖ የቆየውን የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ከ…
❤13👎3
28 Aug 2026, 12:42 UTC≈3,880 views14 reactionsread 3 September 2026 Forwarded from @ethioelectionsPhoto
🗳️ አሃዛዊ ትንታኔ፤ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ድምፅ ቁጥር ምን ይነግረናል?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገውን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ዝርዝር ውጤት መሠረት በማድረግ፣ “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ከመራጮች ድምፅ ብዛትና ስርጭት ጀርባ ያሉ ቁልፍ እውነታዎችን በአሃዛዊ ትንታኔ እና በምስላዊ መግለጫ አስደግፋ ትንታኔዋን ይዛ ቀርባለች።
የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎች እና የግል ዕጩዎች ካሸነፏቸው 48 መቀመጫዎች መካከል ስንቱን ብልፅግና ያልተወዳደረባቸው ናቸው? ስንቱንስ ከብልፅግና ጋር ተወዳድረው አሸነፉ?
ገዢው ፓርቲ በአብላጫ ድምፅ (FPTP) የምርጫ ሥርዓት መሆኑ ቀርቶ የተመጣጣኝ ውክልና ሥርዓት ቢሆን ኖሮ፣ ገዢው ፓርቲ ካገኛቸ…
❤11👎3
26 Aug 2026, 09:11 UTC≈5,140 views20 reactionsread 3 September 2026 Photo
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን አተገባበር የሚከታተል “ገለልተኛ እና ህጋዊ” አካል አንዲቋቋም ጥያቄ አቀረበ።
የፌደራል መንግስት ምክረ ሃሳቦቹን ለመተግበር “ከተገቢው በላይ ጊዜ እንዳይወስድ” እና አፈጻጸሙን “በፍጥነት” እንዲከናወን እንዲያደርግም ፓርቲው አሳስቧል።
ኢዜማ ማሳሰቢያውን እና ጥያቄውን ያቀረበው፤ ለ38 ቀናት ሲካሄድ የቆየውን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተጠናቀቀውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤን አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 20፤ 2018 በሰጠው መግለጫ ነው።
ፓርቲው በዚሁ መግለጫው ሀገራዊ የምክክር ሀሳቡ “ከተጠነሰሰበት ቀን” ጀምሮ “በከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት፣ በንቃት …
👎11❤5👍3👏1
23 Aug 2026, 09:04 UTC≈6,380 views26 reactionsread 3 September 2026 Photo
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት “በአብዛኛው ደስተኞች ነን” ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከተፈታኝ ተማሪዎች መካከል 87.2 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳልፋቸው ውጤት ማምጣት ሳይችሉ በቀሩበት እና 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ካስታወቁ በኋላ ነው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ የትምህርት ሚኒስትርነት ኃላፊነት ከተረከቡ ወዲህ ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ያሳወቁት ትላንት ቅዳሜ ነሐሴ 16፤ 2018 ዓ.ም ነው።
ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ በበይነ መረብ፣ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ደግሞ በወረቀት አማካኝነት የተሰጠውን …
❤18😁4👎3🤷1
21 Aug 2026, 06:34 UTC≈6,610 views20 reactionsread 3 September 2026 Photo
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ውዝግብ እና አለመግባባት በፈጠረው የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ላይ አስማሚ ሃሳብ እንዲያዘጋጅ የተቋቋመው አቀራራቢ ኮሚቴ፤ የደረሰበትን ውጤት በዛሬው ዕለት ለተመካካሪዎች እንዲያቀርብ መወሰኑን የጉባኤው ተሳታፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ።
ኮሚቴው አስማሚ ሃሳቡን የሚያዘጋጀው፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ደረጃዎች የተከፋፈሉ ቡድኖች ያቀረቧቸውን ሃሳቦች ከቃለ ጉባኤዎች ላይ ከመረመረ በኋላ ነው ተብሏል።
በስምንት ዋነኛ አጀንዳዎች ተከፍሎ ላለፉት 35 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፤ የአዲስ አበባ ከተማን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው በፌደራል ከተሞች ዕጣ ፈንታ ላይ እንዲመካከሩ በተመደቡ ቡድኖች አማካኝነት …
❤13👎6⚡1
20 Aug 2026, 11:31 UTC≈6,050 views20 reactionsread 3 September 2026 Photo
በቀጣዮቹ ቀናት ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ፤ በስምንት ዋነኛ መወያያ አጀንዳዎች ስር በአጠቃላይ 476 ምክረ ሃሳቦች መቅረባቸው ይፋ ተደረገ።
የቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ከተጠቃለሉ እና ከተጣጠሙ በኋላ የተዘጋጀውን አንድ ወጥ ሰነድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነገ አርብ አሊያም ከነገ ወዲያ ቅዳሜ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል።
በ90 ንዑሳን አጀንዳዎች እና በ225 መሪ ጥያቄዎች ላይ ተመስርተው የተዘጋጁት 476 ምክረ ሃሳቦች መቅረባቸው ይፋ የተደረገው፤ በትላንትናው ዕለት በነበረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ውሎ ላይ ነው።
በዚሁ የጉባኤ ውሎ ከየስራ ቡድኑ የተወከሉ 120 ተመካካሪዎችን ያካተተው የአጀንዳ አቀናጅ ቡድን፤ የተቀናጁ …
❤8😁8👍3💔1
18 Aug 2026, 12:25 UTC≈5,880 views19 reactionsread 3 September 2026 Photo
ሰላሳ አራተኛ ቀኑን በያዘው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ በአጀንዳዎች ላይ ውሳኔ እየተሰጠ ያለው “የድምጽ አሰጣጥ ስርዓትን” በተከተለ አግባብ አለመሆኑን ሶስት የጉባኤው ተሳታፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
በጉባኤው ላይ በማመካከር እና በታዛቢነት እየተሳተፉ ያሉ ሁለት ግለሰቦችም ይህንኑ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው ሰነድ በአጀንዳዎች ላይ ውሳኔ የሚደረሰው በየደረጃው ያሉ ተሳታፊዎች ከ70 እስከ 75 በመቶ ድጋፍ ሲሰጡ እንደሆነ ያስቀምጣል።
ኮሚሽኑ የዘረጋው ይህ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት ግን እስካሁን በየደረጃው ባሉ የቡድን ምክክሮች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየተመካከሩ የሚገ…
❤14👎3👍2
15 Aug 2026, 07:55 UTC≈7,180 views20 reactionsread 3 September 2026 Forwarded from @ethioelectionsPhoto
የኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት ችግሩ ምንድን ነው? የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በተመጣጣኝ ውክልና ቢሰላ ኖሮ ምን የትኞቹ ፓርቲዎች ያተርፉ ወይም ያጎድሉ ነበር?
በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ ቁጥር ሁለት ስር “የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት” አንኳር መነጋገሪያ ሆኖ ቀርቧል።
“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት የመራጮች ድምፅ መሠረት በማድረግ፣ አሁን ያለው የአብላጫ ድምፅ (First Past the Post - FPTP) ሥርዓት በተመጣጣኝ ውክልና (Proportional Representation - PR) ቢተካ ኖሮ በፓርላማ መቀመጫዎች ላይ ምን ዓይነት ለውጥ ያመጣ እንደ…
❤17🤪2💯1
7 Aug 2026, 15:44 UTC≈9,700 views21 reactionsread 3 September 2026 Photo
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ባለፈው ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት አቶ አበበ አካሉ እና አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ ላይ ፍርድ ቤት የ12 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ፣ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ችሎቱ ለዛሬ ቀጥሮ ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከማስተላለፉ አስቀድሞ፤ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ማመልከቻው ያካተተውን እና ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋር ያደረጓቸውን ቃለ ምልልሶች ሊንኮች በትላንትናው ዕለት እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ መ…
❤14👍4😁2👎1
6 Aug 2026, 10:08 UTC≈8,650 views22 reactionsread 3 September 2026 Photo
የ“አዲስ ስታንዳርድ” የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር፤ ባለፈው ቅዳሜ “በጸጥታ አባላት” ተይዞ ከአንድ ቀን በኋላ መለቀቁን አሳታሚ ድርጅቱ አስታወቀ።
ይህ ድርጊት በተፈጸመ በማግስቱ “የጸጥታ እና የደህንነት አባላት” ወደ “አዲስ ስታንዳርድ” ቢሮ በመግባት፤ መገናኛ ብዙሃኑ ለስራ የሚገለገልባቸውን ንብረቶች ይዘው መሄዳቸውንም ድርጅቱ ገልጿል።
የመገናኛ ብዙሃኑ አሳታሚ ጃኬን ፐብሊሺንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 30፤ 2018 ባወጣው መግለጫ ነው።
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በመገናኛ ብዙሃኑ ላይ የደረሱ ክስተቶችን በዝርዝር የያዘው መግለጫው፤ ከዋና አዘጋጁ እስር እና ከንብረ…
😢10❤9👍3
5 Aug 2026, 12:43 UTC≈8,680 views37 reactionsread 3 September 2026 Photo
ከትላንት በስቲያ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሁለት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት እና የፓርቲው ጠበቃ፤ “የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል” የሚል ውንጀላ ቀረበባቸው።
ፖለቲከኞቹ እና ጠበቃው ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት (ህወሓት)፣ “ከሌሎች ጸረ- ሰላም ኃይሎች” እና “ጽምዶ” ተብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር “በመቀናጀት” በአዲስ አበባ ከተማ አባላትን “በመመልመል” እና “በማደራጀት” ተጠርጥረዋል።
የፌደራል ፖሊስ እነዚህን ውንጀላዎች ያቀረበው፤ በአቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እና አቶ አበራ ንጉስ ላይ ነው።
የኢሕአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይስሀቅ እና የህግ ባለሙያው አቶ አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፤ ከት…
🤣15❤12👎5👍3😁1😡1
31 Jul 2026, 12:20 UTC≈9,650 views23 reactionsread 3 September 2026 Photo
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፤ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየሄደ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጸ።
እስካሁን በጉባኤው የተጠናቀሩ አጀንዳዎች፤ ከሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ 500 ተመካካሪዎችን ለሚይዙ 8 ቡድኖች እንደሚቀርቡ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ሐምሌ 8፤ 2018 በይፋ የተከፈተው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፤ አጠቃላይ ሂደቱ ይወስዳል ተብሎ የተገመተው ጊዜ ሶስት ሳምንት ነበር።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የጉባኤውን መጀመሪያ ቀን ለማብሰር ባለፈው ሰኔ ወር በሰጠው መግለጫ ላይም፤ ይህንኑ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።
ሆኖም ጉባኤው ሲጀ…
😁14❤9
Showing the 12 most recent of 27 posts we hold for @EthiopiaInsiderNews. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.