7 Aug 2026, 07:52 UTC66 views3 reactionsread 7 August 2026 እንኳን አደረሳቹሁ !
ጾመ ፍልሰታ
#ጾም_በሐዲስ_ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚ…
❤3
21 May 2026, 06:05 UTC406 views3 reactionsread 7 August 2026 ✝️ ጌታችን ለምን ዐረገ ?
1- ሰው በመሆኑ ተለወጠ ፍጡር ሆኖ ቀረ የሚሉ አሉና ወረደ በተባለው ሰው መሆኑን እንደተገለጸው ፤ ዐረገ በመባሉ ደግሞ ሰው አምላክ ሆነ የሚለውን ለመግለጽ ጌታችን ዐረገ::
2 - ቅዱሳን ጻድቃን ኋላ ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንደሚያገኙ ለማስረዳት 0ረገ። " ዐርገ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሓን / የጻድቃንን ዕርገታቸውን ( የሚወርስዋትን መንግሥተ ሰማያት ) እንዳለች ለማሳወቅ ዐረገ" እንዲል (መቅድመ ወንጌል )
✝️ ጌታችን ለምን በ40 ኛው ቀን ዐረገ ?
-> ጌታችን ያረገው ሞትን በሥልጣኑ ድል አድርጎ በተነሳ በ40 ኛው ቀን ነው (የሐዋ 1፥ 3 ) ። ለምን 40 ቀን እስኪሞላ ጠበቀ ከ 40 በታች ወይም በላይ …
❤2🥰1
20 May 2026, 08:59 UTC347 views2 reactionsread 7 August 2026 Photo
✥ ትጒህ በጸሎት ✥
-> አቡነ ተክለሃይማኖት እየረዱ (ረድ ሆነው ) ሰባት ሰባት ጊዜ ዳዊትን ያደርሱ ነበር (ማር ይስሐቅ ገፅ 77 / ገድለ ተክለሃይማኖት )
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው፤ በ1197 ዓ.ም ታኅሣሥ 24 ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ በወላጅ አባታቸው በካህኑ …
❤2
13 Apr 2026, 06:35 UTC532 views11 reactionsread 7 August 2026 👉ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ👈
⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡
👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
⚡⚡⚡ማክሰኞ⚡⚡⚡
👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
⚡⚡⚡ረቡዕ⚡⚡⚡
👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም…
❤8🙏3
10 Apr 2026, 09:13 UTC517 views9 reactionsread 7 August 2026 #በግብረ_ሕማማት_ውስጥ_የሚገኙ_እንግዳ_ ቃላት_እና_ትርጉማቸው
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
#ኪርያላይሶን፦
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
#ናይናን፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ …
❤7🕊2
9 Apr 2026, 18:47 UTC436 views4 reactionsread 7 August 2026 File
የዕለተ አርብ(ስቅለት) የምንሰግድበት ፅሁፍ።
ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ካሎት በ @fenote_Abew_bot ያስቀምጡልን።
ቤተሰብ ይሁኑ
👉TELEGRAM https://t.me/fenote_abew
👉FACEBOOK https://www.facebook.com/profile.php?id=100040602775882
👉 YOUTUBE https://www.youtube.com/@finoteabew
👉TIK TOK https://www.tiktok.com/@fenoteabew_zetewahido?_t=8mB9Wj5mAPV&_r=1
❤3🥰1
8 Apr 2026, 07:25 UTC460 views4 reactionsread 7 August 2026 5 ድረገጾች ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች
በአሁኑ ሰዓት በየቤታችሁ ለተቀመጣችሁ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ፥ ይህ ወቅት ከጾም እና ከጸሎት ባለፈ ጥልቅ የተመስጦ ጊዜ መሆን አለበት። ተመስጦው የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መስታወት ተጠቅሞ ራስን ለመመልከት፥ ሕይወታችን በመገምገም አካሄዳችንን የምናቃናበት ሊሆንም ይገባዋል። ይህንን በማድረግ ሒደት ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርትን መከታተል ሊካተት ይገባዋልና፥ የተወሰኑ የኢንተርኔት ምንጮችን ላቀብላችሁ ወደድኹ።
1. ደበሎ -
ይህ ደበሎ የተሰኘ በኢንተርኔት የተዘረጋ የአብነት ትምህርት ቤት ነው። የድረ-ገጹ ባለቤቶች በሚገባ የሠሩት ገጽ ነው። ዲቁና መቀበል ለሚፈልጉ የግብረ ዲቁና ትምህርቶች በድምጽ ተጭነዋል።…
❤2👍2
22 Mar 2026, 09:54 UTC757 views6 reactionsread 7 August 2026 ✥ገብር ኄር✥
"መንግሥተ ሰማያት ነጋዴ ናት "
-> መንግሥት ሰማያት ነጋዴ ናት ትርፍን ትፈልጋለች ስለዚህ በመጽሐፍ መንግሥት ሰማያት ብላቴኖቹን ጠርቶ ወጥተው ወርደው ያተርፉበት ዘገድ ገንዘቡን የሰጣቸውን ነጋዴ ትመስላለችና ይላል። (ማቴ ፳፭፥፲፭)
-> ሹመትም ውርደቱም ፣ መጽደቅ መኮነንም በዋጋ (በጸጋ) ሳይሆን በትርፍ ነው። 5 እና 2 መክሊት የተሰጣቸው አገልጋዮች የተሾሙት በትርፋቸው እንጂ ቀድሞ የተሰጣቸውን መክሊት በማቆየታቸው አይደለም ፥ 1 መክሊት የተሰጠውም ባሪያ የተኮነነው የተሰጠውን መክሊት በማጥፋቱ አይደለም ባለማትረፉ እንጂ መክሊቱንስ አስቀምጦ ጌታው በመጣ ጊዜ መልሶለት ነበር በተሰጠው ባለማትረፉ ግን ቀድሞ የተሰጠውን መክሊት ሳያጠፋ …
❤5🥰1
14 Mar 2026, 18:52 UTC615 views3 reactionsread 7 August 2026 ✥✥✥ በዐለ ደብረዘይት ✥✥✥
ትርጉሙ፦ ደበረ ዘይት ትርጉሙ የወይራ መብቀያ፣ በወይራ ደን የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው። ወይም «ደብር» ማለት «ተራራ» ማለት ሲሆን «ዘይት» ማለት ደግሞ «ወይራ» ማለት ነው። በተገናኝ «ደብረ ዘይት» ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የወይራ ተራራ ማለት ይሆናል።
- ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በመካከል የቄድሮን ሸለቆ ብቻ ነው ያለው። ከግርጌው ጌቴ ሴማኒ የተባለው የአትክልት ስፍራ ይገኛል። የጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተያዘበትና በኋላም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋዋ ያረፈበት ወይም የድንግል መካነ መቃብር በዚህ ተራራ ግርጌ ይገኛል። …
❤2🥰1
7 Mar 2026, 17:30 UTC626 views5 reactionsread 7 August 2026 #መጻጒዕ
-> የ0ቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት መጻጕዕ ይባላል።
-> ፀግ0 ፤መጸጕዕ ፦ በቁሙ ጎባጣ በጀርባው ላይ እንደ ሻኛ ያለው ደረቱ ከጉልበቱ የተጠጋ ሕመምተኛ በሽተኛ ማለት ነው።
-> በዚህ ሣምንተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሳ መዝሙር ይዘመርበታል፡:
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጌትነቱ ምልክት በሕዝቡ ያሉ ድውያንን ሁሉ ይፈውስ ነበር፡። የተአምራቱም ዜና በሶርያ በአራቱ ማዕዘን ደረሰ ተብሎ በተነገረው መሠረት ቅዱስ ማቴዎስ 4፥23-25 አንደጻፈው ቀጥለን እናያለን በማቴ 8 ፥1-4 ከተራራ በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት ለምጻም ቀርቦ ጌታ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰው…
❤4🥰1
15 Feb 2026, 10:53 UTC827 views4 reactionsread 7 August 2026 +++አበው ስለ ጾም እንዲህ አስተማሩ!+++
+ ‹‹አንድ ንጉሥ የጠላቶቹን ከተማ በቀላሉ መያዝ ከፈለገ ፤ “የከተማይቱን ውኃ እና ምግብ አቅርቦት ያቋርጠዋል” ፤ ጠላቶቹ በረኃብ እየሞቱ ራሳቸውን ለእርሱ አሳልፈው ይሠጡታልና፡፡ የሥጋም ፈተና እንዲሁ ነው ፤ አንድ ሰው የሚጾም ከሆነ የነፍሱ ጠላቶች ተርበው ይደክማሉ፡፡›› (ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር) [1]
+ ‹‹ጾም የሥራ መጀመሪያ ናት ፤ የጽሙዳን ክብራቸው ናት ፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ናት ፤ የንጽሕና መገለጫ ናት ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ ናት ፤ የጸሎት ምክንያት ናት ፤ የዕንባ መገኛ ናት ፤ አርምሞን የምታስተምር ናት ፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ ታነቃቃለች፡፡›› (ማር ይስሐቅ) [2]
+ የድኆች ወዳጅ የተ…
❤3🥰1
14 Feb 2026, 17:21 UTC695 views9 reactionsread 7 August 2026 ✥ ዘወረደ ✥
-> የ0ቢይ ጾም የመጀመሪያው እሁድ (ሳምንት ) ዘወረደ ይባላል።
->ጌታችን እኛን ለማዳን ከሰማይ መውረዱን የሚነገርበት ሳምንት በመሆኑ ዘወረደ ተብሏል።
-> ከሰማይ ወረደ ማለት እርሱ የሌለበት ኖሮ ካለበት ወደዚህ መጣ ማለት አይደለም እርሱስ ጽርሐ አርያም ምጥቀቱ በርባኖስ ጥልቀቱ ፥ አድማስ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይነገርበት በዓለም ሙሉዕ ነውና ዓለማትን ቢወስን እንጂ ዓለማት እርሱን አይወስኑትም ።
-> የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ሳይለይ ከ0ይናችን ብሌን ጋር እንደሚዋሓድ ወልደም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በምልዓቱ መወሰን ሳይኖርበት በሥጋ ማርያም መገለጹን ሰው መሆኑን ያስረዳል ::
-> ከሰማይ ወረደ ሲባል ስንሰማ መረዳት የሚገባን…
❤7🥰2
Showing the 12 most recent of 21 posts we hold for @retiet_haliyo. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.