23 Aug 2026, 06:58 UTC≈2,230 views27 reactionsread 3 September 2026 File
ይላል አንደበቴ
ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው
ትናንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ
ትልሃለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ
አዝ
የትናንት ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው
ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው
ወደ እረፍቴ ወጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ
ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ (2)
አዝ
በጥልቁ በረሃ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ
መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ
በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ
ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ (2)
አዝ
የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል
ለእኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል
ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ
የጌታዬ ሃሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ (2)
አዝ
ትናንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ
የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ
በ…
❤27
19 Aug 2026, 01:09 UTC≈3,780 views41 reactionsread 3 September 2026 #ደብረ_ታቦር
ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው።
በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ።
ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤ…
❤32🕊6👍3
10 Aug 2026, 17:42 UTC≈4,570 views44 reactionsread 3 September 2026 #ተወዳጁ_ልጅሽ_እንዲመግበኝ_ትለምኝልኝ_ዘንድ_እማጸንሻለሁ
እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። …
❤41👍3
26 Jul 2026, 06:00 UTC≈6,120 views55 reactionsread 3 September 2026 #ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ (#ሐምሌ_19)
ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው።
ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው።
ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ …
❤49👍3🕊3
13 Jul 2026, 03:29 UTC≈6,220 views43 reactionsread 3 September 2026 #ቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ (ሐምሌ 5)
ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።
#ቅዱስ_ጴጥሮስ
ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19
ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣን ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ …
❤39👍2🕊2
7 Jul 2026, 06:25 UTC≈6,060 views39 reactionsread 3 September 2026 እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ከዕለቱ_በረከት
✝ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ✝
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "#ዘካርያስ ካህኑና #ቅድስት_ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
¤የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
¤እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው …
❤28🕊6👍5
4 Jul 2026, 05:50 UTC≈4,410 views27 reactionsread 3 September 2026 በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደ…
❤24👍3
3 Jul 2026, 10:25 UTC≈4,200 views19 reactionsread 3 September 2026 +++ ልሸፈንላችሁ? +++
ሙሴ ከሲና ተራራ ወርዶ ከሕዝቡ ጋር ሲገናኝ የፊቱን ማንጸባረቅ አይተው "ተሸፈንልን" ያሉት ሕዝቡ ናቸው። እርሱ "ከእግዚአብሔር ጋር ስነጋገር ቆይቼ እኮ አሁን መውረዴ ነው? ምነው የፊቴ ብርሃን አስቸገራችሁ? ልሸፈንላችሁ እንዴ?" አላለም። እንዲያውም ቅዱስ መጽሐፍ "ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር" ነው የሚለው።(ዘጸ 34፥29) ለቅዱሳን እግዚአብሔር በፊታቸው የሚሥለው የክብር ብርሃን እነርሱን ለሚመለከታቸው እንጂ ለራሳቸው አይታወቃቸውም። እውነተኞቹ ቅዱሳን "ተሸፈኑልን" የሚባሉ እንጂ "ልሸፈንላችሁ" የሚሉ አይደሉም።
ጥቂት በጎ ሥራ ሠርተህ ጻድቅ…
❤19
30 Jun 2026, 06:49 UTC≈5,330 views31 reactionsread 3 September 2026 #ሰውን_የሚጥለው_መመካቱ_ነው
ወንድሜ ሆይ በሥራህ ሁሉ የታመንህ ሁን አገልጋይ ባልንጅሮችህን ውደዳቸው። ንጹሑን አረጋዊ መቼም መች አክብረው።
ወንድሜ ሆይ በታላላቆች መሃል አትቀመጥ። ተቀመጥ እስኪሉህ ድረስ ቁም እንጅ በሽማግሌዎች መካከል አትቀመጥ፤ በዝቀተኛው ማዕርግ ተቀመጥ እንጅ።
ወንድሜ ሆይ ቁጡ ወይም አንጎራጓሪ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ሐኬተኛ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ምንም ተግባር ለመፈጸም ወዲያና ወዲህ አትናወጽ። እንዳትዋረድ በሊቅ በአዋቂ መሃል አትናገር።
ልጄ ሆይ በጽድቅህ አትመካ፤ ራስህን አታመስግን፤ ሰይጣን ትምክሕትን እንዳያመጣብህ ራስህን በፈቃድህ አዋርድ እንጅ። በትዕቢትና ትምክሕት ሰዶምና ገሞራ ወደቁ። ከእግዚአብሔር መንገድም ተሰናከሉ። …
❤28❤🔥3
27 Jun 2026, 05:40 UTC≈6,830 views46 reactionsread 3 September 2026 #ሰኔ_21
#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)
ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው።
ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች።
ይኸውም ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ።
ሐዋርያትም እን…
❤46
26 Jun 2026, 06:05 UTC≈4,660 views24 reactionsread 3 September 2026 አምላክ ሆይ፥ ለአንተ እሰግዳለሁ! ቸሩ ሆይ፥ አንተን አመሰግናለሁ! ቅዱስ ሆይ፥ አንተን እማልዳለሁ! መፍቀሬ ሰብእ ሆይ፥ በፊትህ እንበረከካለሁ!
አንተ የፈጣሬ ኵሉ የእግዚአብሔር አብ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለህ የባሕርይ ልጁ ነህና ክርስቶስ ሆይ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ!
ንጹሃ ባሕርይ ሆይ፥ ለእኔ ለማይገባኝ ለኃጥኡ ስትል፥ አዎ ነፍሴን ከኃጢአት ቀንበር ነጻ ታደርጋት ዘንድ ራስህን በመልዕልተ መስቀል ላይ ሞተሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ!
አምላክ ሆይ፥ ለዚህ ኹሉ ፍቅርህ ምን እከፍልሃለሁ? መፍቀሬ ሰብእ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! መሐሪ ወመስተሳሕል ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! ተዓጋሢ ሆይ፥ ክብር ለአንተ ይኹን! በኃጢአት በበደል የወደቀውን ሰው (ንስሐ ገብቶ…
❤22👍2
26 Jun 2026, 04:02 UTC≈3,290 views3 reactionsread 3 September 2026 ማስታወቂያ
መምህር ይትባረክ ጋሻው ከፍተኛ የባህል ፈውስ መድህኒት አዋቂ እና ቀማሚ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦ በውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
0917468918
0917468918
1 👉ለመፍትሄ ሀብት
2 👉ለህማም
3 👉ለመስተፋቅር
4 👉ቡዳ ለበላው
5 👉ለገበያ
6 👉የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 👉ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 👉ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 👉ለዓቃቤ ርዕስ
10👉ለመክስት
11 👉ለቀለም(ለትምህርት)
12 👉ሰላቢ የማያስጠጋ
13 👉ለመፍትሔ ስራይ
14 👉ጋኔን ለያዘው ሰው
15 👉ለሁሉ ሠናይ
16 👉ለቁራኛ
17 👉ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ …
❤3
Showing the 12 most recent of 23 posts we hold for @dr_zebene_lemma. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.